Sunday, December 11, 2016

በኢትዮጵያ እየተቀጣጠለ ለሚገኘው ሕዝባዊ ኣመጽ ጠቃሚ የሆኑ የሽምቅ ውጊያ መሰረታዊ መርሆችና ስልቶች (ከኣርበኞች ግንቦት 7 የጥናትና የምርምር ዘርፍ የተዘጋጀ)

ከኣርበኞች ግንቦት 7 የጥናትና የምርምር ዘርፍ የተዘጋጀ


ኢትዮጵያ ሕዝብ ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የበላይነት ስር ከሚገኘው ፋሽስታዊና ኣምባገነናዊ ሥርዓት ጋር የሚደርገውን ትግል ከዳር አስከዳር ለማቀጣጠልና የኣገዛዙን የመጨቆኛ ተቋማት ኣሽመድምዶ ለማንበርከክ በርካታ የትግል ስልቶችን መጠቀም፣ ማጠናከርና ተግባራዊ ማደረግ የግድ ይላል። ከእነዚህም የህዛባዊ ተቃውሞ የትግል ስልቶች መካከል ዋናዎቹ – ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ ሕዝባዊ አመጽ፣ ሕዝባዊ ኣሻጥር፣ ሕዝባዊ ስለላና፣ ሕዝባዊ የስነ-ልቦና ጦርነትና ፕሮፖጋንዳ ይገኙበታል።Patriotic Ginbot 7 fighters attacked TPLF around Humera
ዛሬ በሰሜን ጎንደርና በሌሎች ኣካባቢዎች የተጠናክረውን የፀረ-ወያኔ ሕዝባዊ ኣመጽ ማጠናከርና አጣዳፊ የሆኑ በርካታ የትግል ተግባራትን በየደረጃው መከወን ጊዜ የማይሰጠው ነው። ከነዚህም ኣንዱ የኣርበኝነት ትግል በማድረግ ላይ የሚገኙ የነፃነት ኃይሎች ሕዝባዊ አመጹን ዳር ለማድረስ ይውል ዘንድ ጠቃሚ ያልናቸውን መሠረታዊ የጎሪላ/ሽምቅ ውጊያ መርሆዎችና ስልቶች በመጭመቅ በዚህ ጥናት ተካተዋል። ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ውስጥ በየአካባቢው ለተደራጁና ወደፊትም ለሚደራጁ የሕዝባዊ አመጽ ኃይሎች በህቡዕም በይፋም በማሰራጨት፡ አመጹ ዘመን ያልሻራቸው መርሆዎችና ስልቶችን በጥቅም ላይ በማዋል ትግሉን ለማጠናከር ግባኣት በመሆን ኣስተዋጾ ያደርጋል የሚል እምነት ኣለን። የጥናት ቡድኑ በሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ በሕዝባዊ ኣሻጥር፣ በሕዝባዊ ስለላና ፣በሕዝባዊ የሰነ ልቦና ጦርነትና  ፕሮፖጋንዳ የትግል ስልቶች ዙሪያ ተከታታይ ጥናቶችን በማቅረብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ሥርዓት ጋር ለሚያደርገው ሁለገብ ትግል ማጠናከሪያ የግንዛቤ ግባት አንዲሆኑ ተመሳሳይና ተከታታይ ጥናቶችን በህቡዕና በይፋ ለተድራጁ ታጋይ ኃይሎችና ለሕዝቡ ያሰራጫል።

የጎሬላ/የሽምቅ ውጊያ

የጐሬላ ውጊያ ስልት በጦር መሳሪያና በወታደራዊ ትጥቅ አደረጃጀቱ ከፍተኛ ጉልበት ያለውን የጠላት ኃይል መምቻና ማዳከሚያ መሣሪያና ጥበብ ነው። የጐሬላ ውጊያ ያለ ፖለቲካዊ ግብ ዋጋ የለውም፤ ፖለቲካዊ ዓላማዎቹም የሕዝብን ፍላጐትና ምኞት የተከተለ ካልሆነ የሕዝብን ትብብርና ድጋፍ ማግኘት አይቻልም።  የጐሬላ ውጊያ በሕዝብና ለሕዝብ የቆመ ነው። ስለዚህ አንድ የጎሬላ ተዋጊ ኃይል ውጤታማ እንዲሆን ከተፈለገ የሕዝቡን ድጋፍ ማግኘት ይኖርበታል። ከሕዝብ ጋር የተጣላ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ አደርጋለሁ ብሎ የተነሳ ድርጅት ህልውናውን አስጠብቆ ለመዝለቅ ያለው እድል በጣም ጠባብ ነው። በመሆኑም ለአንድ ድርጅት የማኅበረሰቡ ድጋፍ መኖር የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጉዳይ ነው።
ስለዚህ የማኅበረሰቡን ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን ተግቶ ለመሥራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሮ ለተግባራዊነት መንቀሳቀስ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ድርጅት ዋነኛው የቤት ሥራው ነው።

በጐሬላ/የሽምቅ ውጊያ የሚወሰዱ ስልቶች፦

  1. ዋነኛ የጎሬላ ስልት ድንገተኛ በሆነ መንገድ ጠላትን መትቶ መሰወር ላይ የተመረኮዘ ነው።
  2. ጠላት ባላሰበበትና በማይጠብቅበት ቦታ መርጦ ማጥቃት
  3. የጠላት ጥንካሬ ያለበትን ቦታ ማስወገድ
  4. የጠላትን ክፍተት (ቀዳዳ) በማጥናት ማጥቃት
  5. ጠላትን በፍጥነት አጥቅቶ መሰወር
  6. የጠላትን ስስ ጎኖች መርጦ ማጥቃት
  7. የጠላትን አነስተኛ የሆኑ ተነጣይ ክፍሎችን መርጦ ማጥቃት
  8. አንድ የጐሬላ ተዋጊ ኃይል ከጠላት ጋር ፊት ለፊት የሚደረግን ውጊያ አያካሄድም።
  9. አነስተኛ የጠላትን ኃይል እየመረጡ መተንኮስና መምታት
  10. ጠላት ድካም ወይም ዝለት በሚሰማው ጊዜ አድብቶ መምታት
  11. ጠላት በሚደርስበት ጥቃት ሲያፈገፍግ ወይም ሊያመልጥ ሲሞክር ተከታትሎና ተረባርቦ መደምሰስ። በእንደዚህ ዓይነት እንቅስቃሴ ወቅት በጠላት ወጥመድ ውስጥ እንዳንገባ መጠንቀቅ ይኖርብናል።
  12. በተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ አነስተኛ ጥቃቶችን በመፍጠር የጠላትን ኃይል መበታተን። የተበተነውን የጠላት ኃይል አነስተኛውን እየመረጡ በተናጥል ማጥቃት። በአብዛኛው ጊዜ ጥቃት የሚሰነዘረው በጠላት ጀርባ ወይም ጎን በኩል ብዙም ጥበቃ በማይደረግበት የሳሳ ቦታን ፈልጎ የሚደረግ ነው። የጠላትን ጥንካሬውን ማስወገድና ደካማ ጐኖቹን ማጥቃት (ጠላት በጣም በደከመበት ቦታ ላይ መምታት)፣
  13. ጠላት ወደ ምንፈልገው የውጊያ ቅርፅ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ መደምሰስ። ማንኛውንም ውጊያ ስናካሄድ እኛ በፈለግነው መንገድ እንጂ ጠላት በሚፈልገው መንገድ መሆን የለበትም። በመሆኑም ጠላት እኛ ባዘጋጀነው የውጊያ ወጥመድ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ መምታት ይቻላል።

የጐሬላ ተዋጊ ኃይሎች የሚወስዱት እርምጃ አይነት፦

  1. በመላው ኢትዮጵያ በቀበሌ፣ በወረዳ፣ በዞን፣ በክልል የሚገኙና በሕዝብ ላይ ግፍ የሚፍጽሙ የወያኔን የኣስተዳደርና የደህንነት የፖሊስ ጣቢያዎች፡ የሚሊሽያ መዋቅሮችን ማጥቃት ፣ መበጣጠስ፣ በሕዝብ ላይ ግፍና ጥቃት የሚፈጽሙትን ግለሰቦች መምታት፣ ማሰወገድ፣
  2. ስለጠላትና አካባቢ ሁኔታ የሚገልጽ ማንኛውም መረጃ መሰብሰብ፣
  3. የወያኔ ሠራዊት የተነጣይ አነስተኛ ክፍሎችን በወራራና ኣድብቶና አጥንቶ በደፈጣ ማጥቃት፣ መደምሰስ፣
  4. የወያኔን የግንኙነት መስመሮችን በደፈጣና በድንገተኛ ወረራ ማጥቃት፣
  5. የወያኔን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ሸምቆና አድፍጦ መምታት፣ ማውደም፡ ስንቅና ትጥቅ መማረክ፣
  6. በዋና መንገድ ላይ የሚጓዙ የወያኔ መሆናቸው የተረጋገጠ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎችን በሽመቃና በደፈጣ ማቃጠል፣
  7. የወያኔ ኣገዛዝ ንብረት መሆናቸው የተረጋገጡ ተቋማት ማቃጠል፣ ማውደም፣
  8. በታቀደ መንገድ ከወያኔ ወታደራዊ ኃይሎች ግምዣ ቤቶች ላይ መሳሪያ ለመግፈፍ የሚያስችል ተግባራትን መፈጸም፣
  9. ወያኔ የሚጠቀምበትን መሰረተ ልማቶች ማውደም፣
  10. ለወያኔ ኣገዛዝ እንቅስቃሴ የሚረዱ ዒላማዎችን ማቃጠል፡ ከጥቅም ውጭ ማድረግ፣ ማውደም፣
  11. ለጠላት የኢኮኖሚ ዋልታ የሆኑ ዒላማዎችን ማቃጠል፣ ማውደም፣
የወያኔን የሕዝብ መጨቆኛ ኃይሎችን ለማስተጓጐል፣ ለማሰናከል፣ ለመበታተንና ለማውደም የምንችለው የእኛን ኃይሎች በአነስተኛ ቡድን እያደራጀን በተለያዩ ቦታዎች ማንቀሳቀስ ስንችል ነው።
የጐሬላ ውጊያ እንደዚህ በተለያዩ ቦታዎች የተደራጁ ኃይሎች በሚወስዱት እርምጃ የጠላትን ኃይል የመበታተን አቅምን ይፈጥራል።
የጠላት የተበታተን ኃይል በተናጥል ለማጥቃት እንዲያመች በአነስተኛ ቡድን መንቀሳቀስ የሚችሉና በርካታ ቦታዎችን የሚሸፍኑ የጎሬላ ተዋጊዎችን ማደራጀት ያስፈልጋል።  እነዚህ ኃይሎች በተለያዩ ቦታዎች የሚንቀሳቀሱትን የጠላት ኃይል በተናጥል በመምታት ጠላት የማዳከም ተግባራትን ይፈጽማሉ።
አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች የሚንቀሳቀሱ የጎሬላ ተዋጊዎች አንድ ላይ በማሰባሰብ ሰፋ ያለ ግዳጆችን እንዲወጡ በማድረግ ተመልሰው ወደነበሩበት የእንቅስቃሴ ሂደት ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ ይቻላል። የጎሬላ ተዋጊዎች እራሳቸውን ከአካባቢው ሁኔታ ጋር እያዋሃዱና የጠላት እንቅስቃሴ መሠረት አድርገው ነው ማንኛውንም እንቅስቃሴ የሚያደርጉት። ጠላት ፈጽሞ የጎሬላ ተዋጊዎች የት እንደሆኑ ማወቅ የለበትም።
የጎሬላ ተዋጊዎች ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ስለሚንቀሳቀሱ ጠላት የነሱን ዱካ ለማግኘት ያስቸግረዋል።
በመሆኑም የጎሬላ ተዋጊዎች ሁልጊዜ እራሳቸውን በእንቅስቃሴ ውስጥ ማግኘት ይኖርባቸዋል።  ጠላት እዚህ ጋር ናቸው ብሎ ሊገምት በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ መገኘት ይኖርባቸዋል።
የጐሬላ ውጊያ በባህሪው የጠላትን ኃይል መቶ በመሮጥ /Hit and Run/ ላይ የተመሰረተ ነው። እንደ መርህ የጐሬላ ተዋጊው ኃይል ወደ ጠላትም ሆነ ወደ ኋላ ወረዳ ወይም ነፃ መሬት በሚንቀሳቀስበት ጊዜ በሄደበት መንገድ አይመለስም፣ በተመለሰበት መንገድም እንደገና አይሄድም፤በዋለበት ቦታም አያድርም፣ባደረበት ቦታም አይውልም።
ይሄም ጠላት ጨርሶ የጎሬላ ተዋጊውን ዱካ እንዳያገኝ ያደርገዋል። የጎሬላ ተዋጊውም እራሱ ከጠላት እይታ በሚገባ እንዲሰውር ያደርገዋል።

የጎሬላ ውጊያ በምናካሄድበት ጊዜ መጨበጥ የሚገባን አስተምህሮ

መረጃ
ወደ ውጊያ ከመግባታችን በፊት በቅድሚያ ሶስት ነገሮችን በቅድሚያ በጥልቀት ማወቅ (Foreknowledege) ይኖርብናል እነሱም፦
  1. ስለ ወገን (የራስህን የአጐራባች ክፍሎችን ጥንካሬዎችና ድክመቶች) ማወቅ፣
  2. ስለጠላት (የጠላትን ጠንካራና ደካማ ጐኖች) ማወቅ እና
  3. ስለ መሬት (አካባቢያዊ ሁኔታዎችን፦ስለመሬትና አየር ሁኔታ) ማወቅ ናቸው።
ከላይ የተጠቀሱትን 3 ነገሮች በጥልቀት የምንረዳበት ሁኔታ መፍጠር ከቻልን የምናደርገውን ውጊያ በብቃት ማሸነፍ የምንችልበትን ሁኔታ መፍጠር እንችላለን።
ስለራሳችን አቅም፣ ጥንካሬና ድክመት ማወቅ ከቻልን ባለን አቅም ልክ ምን መሥራት እንደምንችል ስለምንረዳ ከአቅማችን በላይ ከሆነ ኃይል ጋር በግብታዊነት ወይም በስሜት በመነሳት ውጊያ ውስጥ እንዳንገባ ያደርገናል።
ሁልጊዜ እንቅስቃሴዎችን ወይም ግዳጆችን መፈጸም የሚኖርብን ባለን አቅም ልክ ላይ ተመስርተን መሆን ይገባዋል። ይሄም በመጀመሪያ ያለን እውነተኛ አቅም ምንድነው ብለን በመጠየቅ ጥንካሬያችንና ድክመቶቻችን በመለየት ድክመቶቻችንን በመቅረፍ ጠንካራ ሆነን እንድንወጣ ያደርገናል።
ስለ ጠላት በቂ የሆነ መረጃ ማግኘት የምንፈጽማቸውን ግዳጆች ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማከናወን ይረዳናል። በመሆኑም መረጃዎችን የሚያቀርቡልን ሰዎች በማሰማራት ስለጠላት በቂ የሆነ መረጃዎችና ግንዛቤዎች እንዲኖሩን ማድረግ ያስፈልጋል። ካለ መረጃ የሚደረግ ምንም አይነት እንቅስቃሴ መኖር የለበትም። ስለዚህ የጠላትን መረጃዎች ማግኘት የሚያስችል ተግባራትን መፈጸም ያስፈልጋል።
አካባቢን እንዲሁ በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል። ግዳጆችን ለመፈጸም የአካባቢው ሁኔታ አመችነትን ለመረዳት ቀድመን ስለ አካባቢው በቂ ግንዛቤ እንዲኖረን ማድረግ ያስፈልጋል። የውሃ ነጥቦች የት እንደሆኑ፤ ለመደበቂያ አመቺ የሆኑ ቦታዎች የትኞቹ መሆናቸውን፤ የተለያዩ እንቅስቃሴ ለማድረግ አመቺ የሆኑ አካባቢዎችንና ለደፈጣ አመቺ የሆኑ ቦታዎችን ለመለየት አካባቢን መልካ ምድርን የኣካባቢዊንን ወንዞች ተራሮችና ሚዳዎች አንደ እጃችን መዳፍ ማወቅ ያስፈልጋል።

ድንገተኝነት

በጠላት ላይ ድንገተኝነትን የምንወስደው በማንኛውም ጊዜ ጠላት ሳያስበው በድንገት ቅድሚያ የምንወስዳቸውን ርምጃዎች ሁሉ ያጠቃልላል። ድንገተኛ ማጥቃት ማለት ጠላት ሳያውቅና ለአፀፋ ምላሽ ጊዜ ሳንሰጠው የውጊያ የበላይነት ለማግኘት የሚደረግበት ሂደት ነው።
በውጊያ የበላይነት ለማግኘት ድንገተኛ ምት በጠላት ላይ ማሳረፍ ጠላት የመልሶ ማጥቃት ርምጃ እንዳይወስድብን ያደርገዋዋል። ጠላት የመልስ ምት ሊያደርግ የሚችልበትን እድል አለመስጠት የድንገተኛ ማጥቃት ዋና ጠቃሚ ጉዳይ ነው። በዚህ አይነት የማጥቃት ሂደት ጊዜ ከፍተኛ የምት ኃይልና ፍጥነት ወሳኙን ድርሻ ይይዛሉ።
በፍጥነት መንቀሳቀስ ወይም ፈጣን መነቃነቅን መፍጠር ጠላትን ለማሸነፍ ከሚረዱ ቁልፍ መገለጫዎች አንዱ ነው። የጠላት ዝግጁ
አለመሆንን ለእኛ ጥቅም በሚሰጥ መንገድ ለማዋልና ለመጠቀም ወደ ጠላት አቅጣጫ ባልተጠበቀ የጉዞ መንገዶች ተጓጉዞና ጠላት ጥንቃቄ ባላደረገባቸው የውጊያ ቀጠናዎች ላይ በድንገት ደርሶ ለመምታት የሚያስችል የተዋጊው ኃይል ፈጣን ተነቃናቂነትን መፍጠር ያስፈልጋል።

አቅርቦት (supply)

ማንኛውንም አይነት ስኬታማ ውጊያ  ለማድረግ ከተፈለገ የሎጀስቲክ አቅርቦትን በሚገባው ቦታ ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ያለ ስንቅና ትጥቅ ዝግጅት አንድን ውጊያ ማከናወን አይቻልም። እንደ አንድ የጎሬላ ተዋጊ የትጥቅ አቅርቦትን በዘለቄታዊ ሁኔታ ማሟላት የሚችለው ከጠላት ላይ በመግፈፍ ነው።

ግንኙነት

ግንኙነትቶች በአጠቃላይ በሁለት ወይም ከእዛ በላይ በሆኑ ሰዎች ወይም አካሎች መሀል የሚደረጉ የመረጃ ልውውጦችን የሚያመለክት ነው።መረጃው የግድ መተላለፍና መቀበል ወይም መረዳትን የሚጠይቅ ነው። በአንድ ተዋጊ ኃይል ውስጥ የሚደረግ ግንኙነት ማለት ማንኛውንም አይነት መንገድና ዘዴ በመጠቀም ከአንድ ሰው ወይም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ወይም ወሬዎችን ለሚመለከተው ሰው ወይም አካል ማሰራጨት ማለትነው። ይህ ግንኙነት ምስጥራዊነትን የተላበሰ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል።

ደፈጣ

ደፈጣ ማለት አንድ የጎሬላ ተዋጊ በአንድ ለማጥቃት አመቺ በሆነ ቦታ ላይ እራሱና ደብቆ የጠላት ኃይል በሚመጣበት ጊዜ ድንገተኛ በሆነ መንገድ የተኩስ ውርጅብኝ በመፈጸም የሚያኬድ የጥቃት አይነት ነው።  በዚህ የጥቃት ሂደት የጠላትን ኃይል ወይም ንብረት የሆነውን ማንኛውንም ነገሮች ደምስሶ ወይም አውድሞ በፍጥነትና ቅልጥፍና መሰወር ነው።
በደፈጣ የሚደረግ ማጥቃት ጠላትን ለከፍተኛ ውዥንብር ስለሚዳርገው የጠላትን የመልሶ ማጥቃት አቅምን በከፍተኛ ሁኔታ ይሰብረዋል። በዚህም የወገን ኃይል ከፍተኛ የሆነ ድልን የሚጎናጸፍበት እድል ይፈጥርለታል።
ደፈጣ በምናካሄድበት ጊዜ መውሰድ የሚገባን ግንዛቤ
  1. የወገን ሀይሎች ተስማሚ የቦታ አያያዝ፦
ውጤታማ ደፈጣ ለማከናወን የጎሬላ ተዋጊዎች ጥሩ የተኩስ ሽፋን ሊሰጡ የሚችሉበትና ጥሩ መደበቂያ ያለበትን ቦታ መርጠው መያዝ ይኖርባቸዋል። ይህም ጠላት በቀላሉ ውጤታማ የሆነ መልሶ ማጥቃት እንዳያደርግ ያግደዋል።
  1. የመግደያ ወረዳ አቀማመጥ፦
የመግደያ መሬት ማለት ደፈጣው በሚደረግበት ቦታ ላይ አጠቃላይ ተኩሱ ትኩረት የሚያደርግበት አካባቢ ወይም ቦታ ነው። የተመረጠው የመግደያ መሬት ጠላት ከጎሬላው ተዋጊ የሚሰነዘርበትን ጥቃት ሊከልል ወይም ሊመክት ወይም ሊደብቃቸው የማይችልባቸው ቦታዎች መሆን ይኖርበታል። ጠላት ከሚደርስበት ጥቃት ማምለጥ የማይችልበት የመሬት አቀማመጥ ያለበት “የሞት ወረዳ” /DEAD ZONES/” ነው። የመግደያ ወረዳ በወገን የተኩስ መስመሮች በሚገባ የተሸፈነ ሊሆን ይገባል። የወገን ኃይል የያዛቸውን ቦታዎች ከመልቀቁ በፊት ማንኛውም ጠላት አቅም ስለሚኖረው ለያዘው አቅም ሁሉ በተኩስ ቁጥጥር ስር ሊሆንና ሊተኰስበት ይገባል። በእንደዚህ ዓይነት ቦታዎች የገባን ጠላት ሙሉ በሙሉ ከመደምሰስ ውጪ ሌላ አማራጭ ሊኖር ይገባል።
  1. የተኩስ ትክክለኛ ወይም ተገቢ ጊዜ ላይ አጀማመር፦
የደፈጣውን ተኩስ ለመጀመር ከአዛዡ የሚወርድ ትእዛዝ ይጠበቃል። ደፈጣው ሊጀመር አካባቢ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፣ስለእዚህ እያንዳንዱ ሰው በዒላማው ላይ ያነጣጥርና ለመተኮስ ዝግጁ ይሆናል፤ ትእዛዝ አንዴ ከተሰጠ በኋላ ሁሉም ሰው ከፍተኛ ሁኔታ ወደ መግደያ ወረዳ ይተኩሳል፤ ሁሉም የጠላት ሀይሎች-ተሽከርካሪዎችና ሠራዊት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ እስኪረጋገጥ ድረስ ወይም አዛዡ ተኩስ እንዲቆም ወይም የተኩሱ አቅጣጫ እንዲለወጥ ትእዛዝ እስኪሰጥ ድረስ በጠላት ላይ መተኮሱ ይቀጥላል። ጠላት ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ወይንም ከባድ ጉዳት ደርሶበት መሽመድመዱ እንደተረጋገጠ በፍጥነትና ቅልጥፍና በተሞላው መንገድ የጎሬላ ተዋጊዎቹ ከአካባቢው መሰወር ይኖርባቸዋል።

ጥብቅ ስነ ስርአት/ ዲሲፕሊን መኖር

የጎሬላ ውጊያ ውጤታማነት በጥብቅ ስነ ስርዓት መታነጽ ላይ ይወሰናል። ስለዚህ አባላቱ ምንም አይነት የስነ ስርዓት ግድፈት ሊታይባቸው አይገባም።  በስነ ስርዓት ያልታነጸ ሰው እራሱ እና ድርጅቱ ላይ አደጋ የመጋበዙ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ችላ የሚባል ተግባር አይደለም።
የጎሬላ ውጊያ እና ይህን ተግባራት የሚወጡ አባላት የሚኖራቸው ጥብቅ የሆነ ስነ ስርዓት ተነጣጥለው የሚታዩ አይደሉም። የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። በመሆኑም አባላት ከፍተኛ ዲሲፕሊን ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።

ቅድሚያ የመውሰድ ተነሳሽነት

አንድ ለነጻነት የሚታገል ኃይል ቅድሚያ የመውሰድ ተነሳሺነቱን ካጣ የሚፈልገውን የሚያደርግበት ወይም እንቅስቃሴውን የሚመራበት ነፃነት ያጣል ማለት ነው።
ይሄም እንቅስቃሴውን ደካማ ወይም የተጓተተ እንዲሆን ያደርገዋል። በመጨረሻም ለውድቀትና ለሽንፈት የሚዳረግበት ሁኔታ አይቀሬ ያደርገዋል። ጨርሶውኑም እንዲጠፋ ምክንያት ይሆናል።
ጠላትህን በሚገባ ማወቅ አለብህ። መረጃ ለማግኘት የመጀመሪያ ሁን፤ ውሳኔ ለመውሰድ የመጀመሪያ ሁን፤ እርምጃ ለመውሰድ የመጀመሪያ ሁን። ጠላት ላይ የበላይነትን ለመጎናጸፍ የሚቻለው ከላይ የተቀመጡትን ተግባራት ለመወጣት የሚያስችል አቅም ሲፈጠር ነው።  ጠላትን በመከላከል ተግባር ላይ ብቻ ተወስኖ እንዲቀርና በኋላም እንዲደመስስ ማድረግ የሚቻለው የወገን ኃይል ቅድሚያ የመውሰድ ተነሳሽነቱ ከፍተኛ መሆን ላይ ባለው ጥንካሬ ነው።
ቅድሚያ የመውሰድ ተነሳሽነት ያለው ኃይል በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ውስጥ እራሱን ያገኛል። ይህም የጠላት እንቅስቃሴ በወገን የማድረግ አቅም ብቻ ተወስኖ እንዲቀር ያደርገዋል።

የጠላት/የወያኔ ሠራዊት ኣደረጃጀትን ዶክትሪን

የወያኔ ሠራዊት ኣደረጃጀት  በከፊል መደበኛ በከፊል ፀረ ሽምቅ ስልጠና የወሰደ የፀረ ሽምቅ የጦር ስልቶችን የሚጠቀም ነው።
  • ወያኔ የሚከተለው የፀረ ጎሬላ/ሽምቅ መሰረታዊ ዶርክትሪን/መርሆ/ፍልስፍና ኣለው።
ይህም፥ ኣንድ ሽምቅ ተዋጊ ኃይል – በኃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰስ ኣለበት የሚል ነው። የተወሰደ ጊዜ ተስወዶ፣ የፈለገው ኃይል ወስዶ፣ መስዋዕትነት ተደርጎ፣ በየትኛውም አካባቡው የሚገኝ የሽምቅ ኃይል መደምስ ወይንም መማረክ አለበት የሚል ነው። በአንጭጩ ኣስቀረው፤ አስኪያድግ ጊዜና ፋታ ኣትስጠው የሚል ነው።
  • ኣንድ የሽምቅ ተዋጊ ህይል ባለበት ቦታ ሁሉ ፀረ-ሽምቅ ኃይል በኣካባቢው ይመደባል፤ ሥራው ሸማቂውን ማሳደድ ፥ ፋታ ማሳጣት፣ መምታት፣ መደምሰስ ወይንም መማረክ ኣለበት የሚል ነው። ኣንድም ሸማቂ ፣ የቆሰለ ሸማቂም ቢሆን በሕይወት መኖር የለበትም፤ መደምሰስ ወይንም መማረክ ኣለበት በሚል የወያኔ ዶክትሪን ያስቀምጠዋል። ወያኔ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ 10,000, 20,000 ሠራዊት ለሞትና ለምርኮ ቢዳርግ ከቁብም ኣይቆጥረውም። ሠራዊቱን የእሳት ራት ከማድረግ ምንም ኣያግደውም።

ስለዚህ  የሕዝባዊ ኣመጹ ኣካል የሆኑ  የነጻነት ኃይሎች መከተል የሚገባቸው ዶክትሪን/መርሆዎች

  1. ከምንም በላይ ራስን መጠበቅ፡ ህልውናን መጠበቅ (survival) ላይ የተመሰረተ መሆን ያለበት- ባልታሰበ የጠላት ከበባ ላለመያዝ ከፍተኛ ጥንቃቄ አንደ ብረት የጠነከረ ዲስፕሊና ከፍተኛ የመረጃ ብቃት አንዲኖርው ማድረግ የግድ ይላል። አካባቢውን በአይነ ቁራኛ መጠበቅ፤ ቅኝት ማድረግ፣ ንቁ ሆኖ ራስን ከጠላት ጥቃት መጠበቅ፣ አካባቢህን አንደ እጅህ መዳፍ ማወቅ የግድ ይላል። ከጠላት ጋር የሚደረጉ ፍልሚያዎች ከጀብደኘት የራቁ ብልሀትን፣ ስልትን፣ መርጃን ከደፋርነትና ጀግነነት ጋር ያጣመሩ መሆን ኣለባቸው። ከግዙፍ የጠላት ኃይል ጋር ፊት ለፊት ኣለመግጠም። በኣቅምና በብዛት ካኣንተ በላይ የሆነ ጠላት መሸሽ ብልሀት አንጂ ፍርሃት ኣይደለም።
  2. የአቅም ቁጠባ  – ብዙ ዒላማዎች ላይ ከመሯሯጥ ወሳኝ በሆኑ ጥቂት ዒላማዎች ላይ ማነጣጠርና ማጥቃት።
  3. ድንገተኛ ጥቃት –  ጠላት ባልጠበቀው ቦታና ሰዓት በሰውም ሆነ በጦር መሣሪያ ንብረት ላይ ጥቃት ማድረስ
  4. እልህና ቁርጠኝነት –  አርበኛው የሚወስዳቸው ማናቸውም አይነት ጥቃቶች ጠላትን ዳግም እንዳያንሰራራ አድርጎ መደቆስ
  5. የአላማ ጽናት –  ጠላት ምንም አይነት የአጸፋ እርምጃ ቢወስድም አርበኛው ሳይዘናጋና ልቡ ሳይከፈል ተልዕኮውን መፈጸም
      ዋና ዋናዎቹ  ናቸው።
  • በሕዝብ የታቀፈና የተደገፈ የአርበኞች ትግል አሸናፊነቱ ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ነው። ይህን ዕውነት በተመለከተ ኢትዮጲያ ብዙ ታሪክ አላት። በተለይም በአምስት ዓመቱ የፋሺስት ኢጣሊያ ዘመን አርበኞቻችን ያሳዩት ተጋድሎና ፅናት፣ የሃገር ፍቅርና የሕዝብ ድጋፍ ትልቁ ምሳሌ ነው። ራስ ኣበበ ኣረጋይ በሸዋ፣ ራስ ኣሞራው ውብነህ በጎንደር፣ ፊታውራሪ በላይ ዘለቀ በጎጃም፣ ደጃዝማች በቀለ ወያ እና ደጃዝማችህ ግረሱ ዱኪ በደቡብ ኢትዮጵያ፣  ኮ/ል ኣብዲሳ ኣጋ፣ ልጅ ሀይለማርያም ማሞ፣  ጀ/ል ጃጋማ ኬሎ ፣ ራስ መስፍን ስለሺ፡  ቢትወደድ ኣዳነ፣ ከሴቶች አነ ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ፡ በፋሽስት ጣልያን የወራራ ዘመን የኣርበኝነት የሽምቅ ውጊያ የኣርበኝነት ተጋድሎ ካደረጉ ኣርበኞች ጥቂቶቹ ናቸው።
  • በከባድ መሳሪያና በጦር ኃይል ብዛት የታገዘን ጠላት ፊት ለፊት መጋፈጥ የእሳት እራት መሆን ነው፤ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ነው።
  • የሽምቅ ተዋጊው ሁልጊዜም ቢሆን ራሱ በሚመቸውና በሚወስነው ቦታና ሰአት ብቻ መዋጋት ይኖርበታል። መቼ ማጥቃትና መቼ ማፈግፈግ እንዳለበት የሚወስነው እሱ ብቻ ነው።
  • ስለ ጠላት እንቅስቃሴ በቂ መረጃ አስቀድሞ መሰብሰብ የግድ ይላል። የጠላት የሰው ኃይል ብዛት፣ የመሳሪያ አይነት፣ የቅድመ ዝግጅትና እቅድ መረጃዎች በጁ ካሉ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች እጅግ ጠቃሚዎች ናቸው።
  • በስርአት የታነጸና ጥሩ ልምምድ ያለው ትንሽ የሽምቅ ጦር ብዛት ያለውን የጠላት ጦር ማሸነፍ እንደሚችል ታሪክ በተደጋጋሚ አሳይቷል። በቻይና በጃፓን ኢምፔሪያሊስም ላይ፤ በኣፍጋንሲታን በሩስያ ላይ፤ በቪየትናም በኣሜሪካ ላይ በሕዝብ የተደገፉ በብዛትም በመሳሪያ ብዛትናኣ ጥራት ኣናሳ የሆኑ ሽምቅ ተዋጊዎች ድል ኣድርገዋል።
  • የአላማ ግልጽነት፤ የመንፈስና የሞራል ጽናት፣ አንዲሁም ስትራቴጂካዊ ብልሀትና ብልጠት ለድል ኣድራጊነት ትልቅና ወሳኝ ድርሻ ኣላቸው።
  • በቂ የውጊያ ልምምድና በራሳቸው መቆም የሚችሉ ተዋጊዎች ጽናት፣ ቆራጥነትና በመረጃና በእቅድ የሚሰሩ ጠንካራ መሪዎች መኖራቸው ሌላው ውስኝ ግብዓቶች ናቸው።
  • የሽምቅ ውጊያ ከመደበኛ ጦርነት የሚለየው በመሳሪያም ሆነ በሠራዊት ብዛት ታግዞ ጠላት ላይ አንድ ትልቅ ጥቃት ማድረስ ሳይሆን አሳቻ ጊዜና ቦታ እየመረጠ ተደጋጋሚና ትንንሽ የደፈጣ የወረራ ጥቃቶች ማድረሱ ላይ ነው።
  • ጠላትን ድንገት ማጥቃት፣ ማቁሰልና ማዳከም አይነተኛ ባህሪዎቹ ናቸው። ኣንድ ሽምቅ ተዋጊ ድንገት ያጠቃል፣ ያፈገፍጋል፣ ይበተናል ደግሞ ተመልሶ ተደራጅቶ ያጠቃል።
  • የሽምቅ ተዋጊ አርበኛ አወቃቀር እንደልብ የሚደራጅና ሲያስፈልግም የሚበተን መሆን አለበት።
  • ከተማን መቆጣጠርና ትላልቅ የኢኮኖሚ አውታሮችን መያዝ ወይንም ገዢ መሬቶችን መቆጣጠር፣ ተቶጣጥሮም አነዚህን መከላከል የሱ ሥራ አይደለም።
የሽምቅ አርበኛው ዋና አላማዎቹ የሚከተሉት ናቸው።
  1. ተከታታይነት ያላቸው ትናንሽ ጥቃቶች በበርካታ ኣካባቢዎች ማካሄድ፣ ጠላትን እንቅልፍ መንሳት፣ ማበሳጨትና ሞራሉን ማዳከም፡
  2. ጥቃቱን ተደጋጋሚና በሁሉም አቅጣጫ ማድረግ፡ ጠላት ሁሉንም ኣቅጣጫ ለመከላከል፡ የሠራዊት ክምችቱ እንዲበታተን፣ አንዲለጠጥ፣ ኣንዱ የጠላት ኃይል ለሌላው የጠላት ኃይል አንዳይደርስ፣ ኣቅሙና ጉልበቱ አንዲበታተን፣ እንዲከፋፈል  ማስገደድ፤
  3. ቀልጣፋ የሆነ የማፈግፈግ ስልት መጠቀም፣ እንደገናም ደግሞ ማጥቃትና እሱ ራሱ የሸማቂው ቡድን የወጠነው ዕቅድ ካልሆነ በቀር የጠላትን ጦር ቀጠና መልቀቅ።
  4. በፍጹም በጀብደኝነት አለመጋፈጥ፤ መረጃን፣ የጎሬላ ስልቶችን፣ ጥበብን፣ ብልጠትና ብልሀትን መሠረት ኣድርጎ መንቀሳቀስ።
  • በማያቋርጥ ተለማጭና ተለዋዋጭ እንቅስቃሴ ላይ በመሆኑ የሽምቅ ተዋጊው በቀላሉ የጠላት ኢላማ ውስጥ አይወድቅም። አስፈላጊውን ጥቃት ከፈጸመ በኋላ ይሰወራል።
  • አርበኛው ሊፈጽመው ያሰበው ጥቃት ግልጽ የሆነ ሌሎች አርበኛ ባልደረቦቹ የተረዱትና በሚገባ የተዘጋጁበት መሆኑ በጣም ኣሰፈጊና መሰረታዊ ነው። ይህንን ለማድረግ ደግሞ በቂ የሆነ መረጃ ሊኖር ይገባል።
  • አርበኛው ስለጠላት ሊኖረው የሚገባው ሁለንተናዊ መረጃ  እጅግ ወሳኝ ነው።
  • በጥሩ መረጃና በጥሩ ሞራል የሚንቀሳቀስ አርበኛ ግዳጁን ከመፈጸም የሚያግደው ምንም አይነት ኃይል አይኖርም።
  • ይህ ትግል ረዥምና የሚያስከፍለውም መስዕዋትነት ከፍተኛ ቢሆንም እንኳ በዓላማ ጽናትና በመንፈስ ብርታት የታነፀን አርበኛ ካለመው ግብ ከመድረስ አያግደውም፤ ያሸንፋል እንጂ በፍጹም አይሸነፍም።
  • በየቀኑ የሚቀዳጀቸውን ትናንሽ ድሎች እያበረከተ ከፍ ወዳለ ደረጃ ማድረስና የሕዝቡንም ንቃትና ድጋፍ ማሳደግ የሽምቅ ተዋጊው ዋነኛ አላማ መሆን ይኖርበታል።የአርበኛውና የሕዝቡ መደጋገፍ ወደ ማያጠራጥር የድል ጎዳና ያደርሳል።
  • የጠላትን ጦር እንቅስቃሴና ግንኙነት በመግታት ትላልቅ ከተሞች ውስጥ ብቻ አፍኖ ይዞ በገጠሩና ትናንሽ ቀበሌዎች ውስጥ አርበኛው የራሱን የተቀውሞ ጎራ ማጠናከርና ብሎም በየፊናቸው የሚንቀሳቀሱትን ሌሎች አርበኞች ወደ አንድ ስብስብ ማምጣት ይኖርበታል።
  • የአርበኛው ቀዳሚ ስትራቴጂ ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባስቦ ጠላት ባላሰበው ሰአትና ቦታ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ነው። ይህን ሲያደርግም የጠላት ጦር  መልሶ ለማጥቃት የሚችልበትን  አቅም ሙሉ በሙሉ በማሳጣት መሆን ይኖርበታል።

ማጠቃለያ

ኣርበኞች የራሳቸውን  ህልውና ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ፡ በመረጃና በአቅድ ላይ ተመስርተው የሚከተሉትን መተግበር፦
  1. በመላው ኢትዮጵያ በቀበሌ፣ በወረዳ፣ በዞን፣ በክልል የሚገኙና በሕዝብ ላይ ግፍ የሚፍጽሙ የወያኔን የኣስተዳድርና የደህንነት የፖሊስ ጣቢያዎች፡ የሚሊሽያ መዋቅሮችን ማጥቃት ፣ መበጣጠስ፣ በሕዝብ ላይ ግፍና ጥቃት የሚፈጽሙትን ግለሰቦች መምታት፣ ማሰወገድ፣
  2. በመላው ኢትዮጵያ በጠላት ስስና ደካማ ጎኖች፤ በትናንሽ ተነጣይ የጠላት የጦር ክፍሎች ላይ የደፈጣና የወረራ ጥቃቶች፡
  3. በኣራቱም የኢትዮጵያ ማእዘናትና ለወያኔ ግኙነትና ኣቅርቦት የሚያገልግሉና ዋና ዋና መንገደች ላይ በሚንቀሳቅሱ የጠላት መሆናችቸው በተረጋገጡ ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ዲፖ መኪናዎች ላይ በመረጃናላይ የተመሰረቱ የደፈጣ ጥቃቶች መሰንዘር፡
  4. የጠላት ወይንም የወያኔ ኢኮኖሚያዊ ተቋማት መሆናቸው በተረጋገጡ ላይ የማቃጠል፣ የማውደም አርምጃዎችን መውሰድ፡
  5. በኣናሳ የጠላት የጦር ሰፈሮችና የፖሊስ ጣቢያዎች ላይ፣ ወዘተ የደፈጣና የወረራ ድንገተኛ  ጥቃቶችን ተግባሪዊ ማደረግ፡
  6. በጠላት ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች ሁሉ ኣርበኛው በመረጣቸው ጊዜ፡ ቦታና ሁኔታዎች ተመስርቶ ጥቃቶችን በብዛትና በስፋት በበርካታ ኣካባቢዎች ማድረግ፡
  7. አነዚህ በተደረጉ መጠን የወያኔ ሠራዊት ሞራል ይብሱኑ አየተዳከመ ይሄዳል፣ ክመዳከምም ኣልፎ ሞራሉ ይላሽቃል፣ ይሰላቻል። የሚከዳው፣ የሕዝቡን ትግል የሚቀላቀለው፤ አንዲሁም በወያኔ ኣዛዦቹ ላይ የሚያምፀው ሠራዊት ቁጥር ይጨምራል።
  8. በተለይም በሁሉም ቦታዎች፣ ኣካባቢዎችና ዋና ዋና የግንኙነትና የኣቅርቦት መንገዶች ላይ የሚደረጉ ወረራና ደፈጣዎች ሲበራከቱ፣ የወያኔ ጦር ኃይሉን በየቦታው ለመበታተን ይገደዳል፣  ወይንም ጥቂት ዋና ዋና ከተሞች ላይ ኃይልኑን ኣከማችቶ አነዚህን ከሸማቂ ኣርበኞች ለመከላከል ይገደዳል።
  9. የጠላት ጠንካራ ጎኖቹ መሳሳት መመናመን ሲጀምሩ የጠላት መሪዎች በከፍተኛ ደረጃ ይሸበራሉ፤ ለማቀድ ለማሰብ ኣስቦ ለመንቅሳቅስ የማይችሉበት የሞራልና የስነልቦና ሁኔታ ውስጥ የሚገቡበት ሁኔታ ይፈጠራል። ይህ ደግሞ ሕዝብን የሚስቆጣ ትግሉን የሚያግዙና የሚያጠናክሩ በርካታ ትልልቅ ስህተቶች እንዲፈጽሙ ያደርጋቸዋል፡፡
  10. በዋና ዋና መንገዶች ላይ የጠላት የኣቅርቦትና የግንኑነት መንገዶችና መስመሮች ላይ የሚንቀሳቅሱ ተሽከርካሪዎች ከደፈጣ ጥቃቶች ለመከላከል ጠላት ኮንቮይ ወንም አጃባ ይጀምራል። ይህ ደግሞ በሠራዊቱ ላይ ብቻ ሳይሆን በወያኔ የኢኮኖሚያዊ ተቁዋሞች ላይ ከፍተኛ ውጥረትና  አጥረት  ይፈጥራል፡
  11. የጠላት የገንዝብ ኣቅሙ ሰራዊቱን ለመቀለብና ለማስታጠቅ ያለው ኣቅም ይመናመናሉ። በሁለንተናዊ መልኩ የጠላት ጠንካራ ጎንኖቹ ሁሉ መሳሳት፣ መዳከም፣ መመናመንና መፍረክረክም ይጀምራሉ። በ100  ቦታ ላይ በስለት ተወግቶ ደሙ ያለማቋረጥ እንደሚፈስና ለሞት እንደሚጋለጥ ሰው ይሆናል።
  12. ለሸማቂው ኣርበኛ የተመናመኑና የተበታተኑን አነዚህን የጠላት ሠራዊት ክፍሎች በብዛት ኣድቅቆ ለመምታት ለመደምሰስ ለማውደም የሚያስችለው ኣዳዲስ ሁኔታዎችን  ይፈጠርለታል።
  13. በዚህ ሂደት የሽምቅ ተዋጊ ኣርበኞች ሞራልና የውጊያ ልምድ በከፍተኛ ደረጃ መዳበር ይጀምራል። የሕዝብ ወገኖች በራስ የመተማመን፣ ሥርዓቱን በድፍረት የመታገል፤ ሕዝብም ለኣርበኛው የሚሰጠው ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል። ኣርበኛውን የሚቀላቀለው ኢትዮጵያዊ በከፍተኛ ቁጥርና  በስፋት ማግኘት ይጀምራል፣ ኃይሉ ይጠናከራል፤ ከሽምቅ ተዋጊነት ወደ ሞባይል ጦርነት/ማለት አንደ መደበኛ ጦር የመዋጋት ደረጃ የሚሸጋገርበት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ለድል መቃረብን የሚመልክት ኣንዱና ትልቁ መለኪያ ይሆናል ማለት ነው።
- See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/17274/#sthash.8B2uDtWZ.dpuf

Ethiopia Travel Warning: U.S. Department of State

The State Department continues to warn U.S. citizens of the risks of travel to Ethiopia due to the potential for civil unrest related to sporadic and unpredictable anti-government protests that began in November 2015. The U.S. Embassy’s ability to provide consular services in many parts of the country may be limited without warning due to the government’s restrictions on mobile and internet communications and the unpredictable nature of the current security situation. This replaces the Travel Warning of October 21, 2016.
Robles in Northern Ethiopia
Robles in Northern Ethiopia
The Government of Ethiopia declared a State of Emergency effective October 8, 2016 that includes provisions allowing for the arrest of individuals without a court order for activities they may otherwise consider routine, such as communication, consumption of media, attending gatherings, engaging with certain foreign governments or organizations, and violating curfews. Additionally, the Government of Ethiopia routinely does not inform the U.S. Embassy of detentions of U.S. citizens in Ethiopia. The full text of the decree implementing the State of Emergency is available on the U.S. Embassy’s website.
Internet, cellular data, and phone services have been periodically restricted or shut down without warning throughout the country, impeding the U.S. Embassy’s ability to communicate with U.S. citizens in Ethiopia. You should have alternate communication plans in place, and let your family and friends know this may be an issue while you are in Ethiopia. See the information below on how to register with the U.S. Embassy to receive security messages.
Avoid demonstrations and large gatherings, continuously assess your surroundings, and evaluate your personal level of safety. Remember that the government may use force and live fire in response to demonstrations, and that even gatherings intended to be peaceful can be met with a violent response or turn violent without warning. U.S. citizens in Ethiopia should monitor their security situation and have contingency plans in place in case you need to depart suddenly.
If you are living in or intending to travel to Ethiopia, please refer to the Safety and Security section of the Country Specific Information for Ethiopia for additional useful information.
Due to the unpredictability of communication in the country, the Department of State strongly advises U.S. citizens to register your mobile number with the U.S. Embassy to receive security information via text or SMS, in addition to enrolling in the Smart Traveler Enrollment Program (STEP).
- See more at: http://ecadforum.com/2016/12/07/ethiopia-travel-warning-u-s-department-of-state/#sthash.EJCFl7WV.dpuf

Sunday, November 13, 2016

ለአዋጁ አዋጅ


ኢትዮጵያውያን  ለሀያ አምስት ኣመታት ባካሄድነው ትግል  ከወያኔ አገዛዝ መላቀቅ አልቻልንም ፡፡ በዚሁ መንገድና ስልት ቀጥሎም ከወያኔ አገዛዝ መላቀቅ እንደማይቻል ከመቼውም ግዜ አሁን ግልጽ ሆኗል፡፡ ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነትና መንገድ ባካሄደው ትግልና እሱን ተከትሎ ወያኔ የወሰደው የአስቸኳይ ግዜ ርምጃ በግልጽ ያሳየንም ይህንኑ ነው፡፡ ስለሆነም እስካሁን በተከተልነው አሰራርና በተጓዝንበት መንገድ  ከወያኔ አገዛዝ ለመገላገል  አንደማይቻል በመረጋገጡ ባለተሄደበት መንገድ ለመሄድ ይቻል ዘንድ ከህዝቡም በኩል የአስቸኳይ ግዜ ማወጅ አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡በዚህ የምትስማሙ ከዚህ በታች በቀረበው  መነሻ ሀሳብ ላይ አስተያየት ስጡበት፡፡
አንቀጽ 1- የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አስፈላጊነት፤
ወያኔ የሥልጣን እድሜውን ለማራዘም ያስችለኛል ያለውን ግድያ እስራትን ሽብር ህጋዊ አድርጎ ለመቀጠል የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አውጥቷል፡፡  በዚህ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሽፋን በህዝብ ላይ እየፈጸማቸው ያለውን እኩይ ድርጊቶች ማስቆምና  ወደ ፊትም ሊፈጽማቸው ያሰባቸውን ማክሸፍ መቻል  ለዘላቂው ድል መንገድ ጠራጊ ርምጃ በመሆኑ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ይቻል  ዘንድ  የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መውጣት አስፈላጊ ሆኗል፡፡
አንቀጽ 2-የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ዓላማ፣
የዚህ አዋጅ ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ሉአላዊነትና በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባት የሚያምኑ ነገር ግን ተበታትነው የሚገኙ ኃይሎችን በመለየት በመካከላቸው ያለውን   የዓላማ ሳይሆን ከመሪዎች  ግላዊ ፍላጎት የሚመነጭ ልዩነት    በማስታረቅ የተባበረ ጠንካራ ኃይል ፈጥሮ የህዝቡንም ትግል አቀናጅቶ   የወያኔን የአገዛዝ ዘመን የሚያሳጥር ትግል ማድረግ ማስቻል ነው ፡፡
አንቀጽ 3 በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ወቅት  የሚከናወኑ ተግባራት
  1. የአደረጃጀት እንዴትነትም ሆነ የትግል ስልት ምንነት ትብብር ለመፍጠርም ሆነ ተደጋግፎ ወደ ድል ለማምራት አንቅፋት ሊሆን አይችልም፡፡ ስለሆነም ድርጅቶች ሁሉ በመሪዎቻቸው ኪስ ውስጥ የሚገኘውን የግል አጀንዳ አስቀምጠው ወያኔን ማስወገድን መነሻው፣ ዴሞክራሲያዊት ሀገር መመስረትን  መድረሻ ግቡ ያደረገ ትብብር መስርተው  በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተጠና የተቀናጀና የተጠናከረ ትግል ማቀጣጠል፡፡
  2. የየድርጅት ደጋፊዎች ከጠባብ የድርጅት ፍቅርና ከግለሰብ አምልኮ በመላቀቅ ትግላቸውንም ሆነ ድጋፋቸውን  ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባት ለሚደረገው ትግል በጋራ ማዋል፤
  3. ምሁራን እንደ እውቀት ዝንባሌያቸው በመሰባሰብ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚያሸጋገር መንገድ ማዘጋጀት፣
  4. ሁሉም ድርጅቶች ከወያኔ በኋላ ምን አይነት ኢትዮጵያን እንደሚሹ እንዴትስ እውን እንደሚሆን መክረውና ዘክረው በሰነድ የተዘጋጀ አቋማቸውን በግልጽ ማሳወቅ፡፡
  5. በሀገራዊም ሆነ በብሄር ከተደራጁት መካከል ከምር ወያኔን ለማስወገድ የሚታገሉ አለመኖራቸው ከፍሬአቸው እየታየ በመሆኑ  እነዚህን መለየት አንዲስተካከሉ መምከር ሳይሆን ሲቀር ትግሉ በእነርሱ አንዳይደናቀፍ ማጋለጥ፡
  6. ግልጽ ዓላማና የትግል ቁርጠኝነት አንግበው ከምር ለለውጥ የሚታገሉትን ለይቶ ማወቅና መርዳት፤
  7. ትግሉ በትብብርና በመደጋገፍ አንዳይካሄድ የሚያደርጉ የየድርጅት አመራሮችን  በመምከርም ሆነ በማስገደድ ከእስከዛሬው ድል አልባ መንገዳቸው አንዲወጡ መስራት እምቢ ካሉ ያለ ድጋፍ ህልውና ሊኖራቸው ስለማይችልና አጥፊዎችን መደገፍ ደግሞ የጥፋት ተባባሪ ስለሚያደርግ ድጋፍ መንሳት፣በግልጽ ማውገዝ፤
  8. በየሀገራቱ የነጻነት ትግሉ የዲፕሎማሲ ቡድን በማቋቋም ተከታታይነት ያለው ስራ መስራት፤
  9. ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራና በየግል ሊዘምረው የሚችል አንድ የትግል መዝሙር ማዘጋጀት፤
  10. ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በያለበት በወያኔ ጎራ የተሰለፉ ወገኖቹ የጥፋት ስራ ተባባሪ እንዳይሆኑ መስራት፤

አንቀጽ 4  በዚህ አዋጅ የተከለከሉ ተግባራት፤
  1. ህዝቡ በደሙ ባቀለመው የነጻነት ትግል መደራደር፤
  2. ህዝቡ የፈጠረውን አንድነት የሚቃረንና ልዩነትን የሚያንጸባርቅ የዘር ጥላቻ ቅስቀሳ ማካሄድ፤
  3. በጽሁፍ በንግግር በሌላም መንገድ የነጻነት ትግሉን ሊጎዳ የሚችል ተግባር መፈጸም
  4. የተፈጠሩ ትብብሮች ተጠናክረው አንዳይቀጥሉ ለማሰናክል መሞከር፤
  5. ያለበቂ ምክንያት የትብብር አባል አለመሆን ወይንም ድርጅቶች ወደ ትብብር እንዳይመጡ ማድረግ
  6. አንዱ ድርጅት ወይንም የድርጅት አባልና ደጋፊ በሌላው ድርጅት ላይ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨት የጎንዮሽ ትግል ማካሄድ
  7. ጸረ ኢትዮጵያ አቋም ለሚያራምዱ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች ተባባሪ መሆን፣ ድጋፍ መስጠት፤
  8. የወያኔን እድሜ ሊያራዝም የሚችል ተግባር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መፈጸም
አንቀጽ 5  የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ተፈጻሚ የሚሆንባቸው ቦታዎች
አዋጁ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት ቦታ ሁሉ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
አንቀጽ ስድስት የአዋጁ አፈጻጸም
ይህን አዋጅ ከሀገር ቤት ሆኖ ማስፈጽም የማይቻል በመሆኑ  አስፈጻሚው አካል በውጪ ሀገር ይሆናል፤
አዋጁን የሚያስፈጽመው በዚህ አዋጅ መሰረት የሚፈጠረው የፓርቲዎች ህብረት አመራር ይሆናል፤
አስፈጻሚው አካል ዝርዝር የተግባር አፈጻጸም መመሪያ ያወጣል፤
አንቀጽ ሰባት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ቆይታ፣
የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ እስከ ሽግግር ወቅት ድረስ ተግባራዊ ይሆናል፤
አንቀጽ ስምንት የአዋጁ ተፈጻሚነት ፤
ይህ አዋጅ   ከ    ጀምሮ      የጸና ይሆናል፡፡
ይህ አዋጅ የህዝቡን የነጻነት ትግል ከግብ ለማድረስ የሚያስችል ከነበረው የተለየ ዘዴም መንገድም ለመከተል አንዲያስችል በህዝቡ ስም የሚወጣና  ኢትዮያውያን ባሉበት ሁሉ ተግባራዊ የሚሆን እንደመሆኑ አፈጻጸሙ ነጻነቴን በሚልና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በሚናፍቅ ዜጋ በጎ ፈቃድ ተግባራዊ የሚሆን ነው፡፡
አስፈጻሚው ሀይል ከማስተባበር አቅጣጫ ከማሳየትና ከማቀናጀት ባለፈ አዋጁን ተፈጻሚ ለማድረግ የሚያስችለው አቅምም መንገድም አይኖረውም፡፡
አዳብሩት ወይንም ጣሉት
- See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/17207/#sthash.ZBARGIPh.dpuf

Ethiopia: Zone9 Blogger Befeqadu Hailu Re-Arrested

Ethiopian Security Re-Arrest Rights Activist, Zone9 Blogger Befeqadu Hailu

Addis Standard (Addis Ababa) — Security member of the command post established to oversee Ethiopia’s six-month State of Emergency have this morning re-arrested human rights activist and blogger Befeqadu Hailu, Addis Standard confirmed.Zone9 Blogger Befeqadu Hailu Re-Arrested
According to information, two security officers who have identified themselves as members of the command post have taken Befeqadu around 6:00 AM this morning. He is now detained at a police station known as 06 here in the capital Addis Abeba.
Befeqadu is a member of Zone9 blogging collective and was one of seven bloggers (one in absentia) and three independent journalists arrested in April. Three months after their arrest all ten of them were charged with Ethiopia’s infamous Anti-Terrorism Proclamation.
After a year and a half trail which was largely marked by several inconsistencies and prosecutor’s inability to provide concrete evidence, a federal court has cleared all of them in July 2015. However, upon appeals from the prosecutor Befeqadu and four of his co-defendants (Natnail Feleke, Atnaf Birhane, Abel Wabella & Soliyana Shimelis, the later in absentia) were re-appearing at the Federal Supreme Court. The hearing was adjourned for the fifth time until Tuesday Nov. 15.
Befeqadu was also facing another criminal charge for allegedly “inciting violence” to which he was released on bail. It is not clear if his re-arrest has anything to do with both cases.
Since Ethiopia declared a six-month state of emergency detentions of opposition party members, journalists and rights activists have increased significantly. Thousands of ordinary Ethiopians are also currently held in dire circumstances inside several detention camps throughout the country.

Stéphane Dion, Canada’s Minister of Foreign Affairs visits Ethiopia

Minister Dion visits Ethiopia and underscores support for engagement of all Ethiopians in an inclusive democratic process

Minister Dion visits Ethiopia
Addis Ababa, Ethiopia – Global Affairs Canada — The Honourable Stéphane Dion, Minister of Foreign Affairs, yesterday visited Addis Ababa to build on Canada’s relationship with Ethiopia, an important partner in the region. Ethiopia is the final stop of the Minister’s visit to Africa, which also included Nigeria and Kenya.
During his visit, the Minister reiterated his concerns over the deaths and violence arising from the recent unrest, particularly in the Oromia and Amhara regions, and underscored his support for all Ethiopians to engage in a peaceful and inclusive dialogue.
Minister Dion had a meeting with Prime Minister Hailemariam Desalegn, in which they discussed the current state of emergency and the critical importance of undertaking timely and meaningful reforms for the benefit of all Ethiopians—particularly its youth—in support of the country’s growth and prosperity.
The Minister also participated in an in-depth exchange with civil society representatives, highlighting the need for democratic space, pluralism and respect of fundamental freedoms for any political dialogue to be successful. Minister Dion carried those messages into his meetings with the Ethiopian government.
Minister Dion’s first visit to sub-Saharan Africa is an opportunity to highlight the importance Canada assigns to the region, focusing on peace and stability, security and the rule of law. The visit also underlines Canada’s commitment to promote inclusive and sustainable growth in Africa, which notably draws on the potential of the continent’s women and youth. The dynamism at play today across the continent is calling out for Canadian engagement and support for African governments as they channel that dynamism for the benefit of their people.

“During my meetings, I stressed that more can be done to engage Ethiopians in the democratic process and to encourage the government to undertake real and constructive reforms. Canada calls on the Ethiopian government to make genuine improvements for the benefit of all of its people.”

– Stéphane Dion, Minister of Foreign Affairs

Saturday, October 29, 2016

“መፍራትና መጠንቀቅ ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው ሀገር የሚያፈርሱትን ነው”

ከስራ አምስት አመት በፊት ነው ኤዴፓ በቅሎ ቤት በሚገኘው ጽ/ቤቱ  እለተ ግንቦት 20ን አስመልክቶ አንድ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ተገኝተናል፡፡ ከተናጋሪዎቹ አንዱ የነበሩት የወቅቱ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ ባደረጉት ንግገር ውስጥ  መፍራትና መጠንቅ ካለብን ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው እኛኑ መስለውና ተመሳስለው ሀገር የሚያፈርሱትን በመካከላችን የሚገኙትን ነው የሚለው አረፍተ ነገር  በአእምሮየ ተቀርጾ አብሮኝ ይኖራል ፡፡
ከሰፊው ኢትዮጵያዊ ማእድ ይልቅ በትንሽ ገበታ መብላት አስመኝቶአቸው ይህንኑ ያሳካልናል ባሉት መንገድ የሚደነቃቀፉትም ሆኑ ዛሬ እየሞተ ካለው ወገናቸው ሞት ይልቅ የዛሬ መቶ አመት ተፈጸመ የሚሉት በፈጠራ ድርሰት የተቀባባ በደል የሚያማቸውና  በዛን ዘመን ተፈጸመ ለሚሉት ዛሬ ማንን አንደሚበቀሉ ባይታወቅም ለበቀል ያሰፈሰፉ፣ ለመለየት የሚጣደፉ ሌሎችም ሰበብ ምክንያት እየፈጠሩ ኢትዮጵዊነትን የሚያኮስሱና ከቻሉም ሊያጠፉ የሚከጅሉ ወያኔን ጨምሮ በንግግራቸውም በተግባራቸውም ይታወቃሉና ሀገር የማፍረስ አደጋቸው አምብዛም ነው፡፡
የእነዚህ አደጋ ሊከፋም ሊሰፋም የሚችለው ኢትዮጵያን የሚለው ወገን እነዚህን ወገኖች በደንብ ለይቶ አውቆና ተጠንቅቆ ተባብሮና ተጠናክሮ ህልማቸው እንዳይሳካ መስራት ካልቻለ ብቻ ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ቅዱስ አስተሳሰብ የራቃቸው ወጎኖች በቆጥር ትንሽ፣ ራእያቸው ጠባብ፣ ፍላጎታቸው ከራስ ጥቅም መሻት ያልዘለለና አንወክለዋለን የሚሉትን የህብረተሰብ ክፍል አንኳን የማያማክል በመሆኑ ኢትዮጵያን የሚለው ወገን ካልተዘናጋና እሱም ርስ በርሱ መስማማት ተስኖት ምቹ ሁኔታ ካልፈጠራለቸው በስተቀረ በምንም መልኩ ህልማቸው ሊሳካ ቀርቶ ስጋት ሊሆኑ አይችሉም፡፡
በወያኔ አብዮት ማግስት በተፈጠረ የፖለቲካ ስካር አሁን ከምንሰማቸው የባሱ ነገሮች በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ሳይቀር ሲነገሩ ሰምተናል፤ተጽፎ አንብበናል፡፡ ግና ስካሩ ሲበርድ እንኳን ንግግሩ ተናጋሪዎቹ በቦታቸው አልተገኙም፡፡ እናም አንድ ነገር በተከሰተ ቁጥር ፍላጎታቸው የሚሳካ የሚመስላቸው ቅዠታሞች በየመድረኩ ቅዠታቸውን ቢናገሩና መሰሎቻቸው ቢያጨበጭቡላቸው እነርሱንም ሆነ ተከታዮቻቸውን ይበልጥ አንድናውቃቸውና ቀይ መስመር ውስጥ አንድናስቀምጣቸው ይረዳናል አንጂ ስጋት ሊሆኑን አይችሉም፡፡ እንደውም አንዲህ አይነቶቹን ሌሎቹንም ሰዎች ይበልጥ አንዲታወቁ በየመድረኩ እየጋበዙ ማናገር ነው፡፡ አበው ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንዲሉ የፖለቲከኛ ሆድ ያባውን የሚያወጣው ጭብጨባ ነውና   የውስጣቸውን አንድም ሳያስቀሩ አንዲናገሩ በጭብጨባ ማሰከር ነው፡፡ ከዛ በደንብ እናውቃቸዋለን ባወቅናቸው መጠንም አንጠነቀቃቸዋለን እንጠብቃቸዋለን ፡፡ ሰው የሚያስቸግረው ማንነቱና ምንነቱ እስኪታወቅ ነው ይባል የለ!
ይልቅ በንቃት መከታተል ቃል ከተግባር እየመዘንን መለየት ያለብን ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ ከአስራ አምስት ዓመት በፊት አንደተናገሩት ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው ሀገር ለማፍረስ ወስጥ ውስጡን የሚያደቡትን፡፡ እንደዚህ አይነቶቹ ሰዎች ወገኔ ተበደለ፣ ሀገሬ ተጠቃ፣ ብለው እንባ ለማንባት የሚገዳቸው አይደሉም፡፡ሰንደቅ ዓላማ ለብሶ ለመፎከር ወያኔን ጥንብ ርኩሱን እያወጡ ለመስደብ ወደር አይገኝላቸውም፡፡
ይህን አድራታቸውን እያየንና እየሰማን ከእነርሱ ወዲያ ሀገር ወዳድ ለአሳር ከእነርሱ በላይ ታጋይ ከየት ሊገኝ ወዘተ በማለት አድናቆታችንን እየገለጽን ከሆኑት አይደለም ፈጽሞ ሊሆኑት ከሚችሉት በላይ እያሞገስንና እያወደሰን እውነተኛ ማንነታቸውን ለመደበቅ  ከሚለብሱት ሰንደቅ ዓላማ በላይ ከፍተኛ ሽፋን አንሰጣቸዋለን፡፡እናም ሳናውቅ እየተከተልናቸው ብቻ ሳይሆን እየደገፍናቸው ሀገር ለማፍረሰ ይህም ባይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ከአገዛዝ አንዳይላቀቅ ለሚፈጽሙት ድብቅ ዓላማቸው አባሪ ተባባሪ ስንሆን ኖረናል፣ አሁንም እንደዛው ያሉ ብዙዎች ይኖራሉ፡፡
እስቲ ዛሬ በዚህ ወሳኝ ወቅት ሳንደባበቅ ደፈር ብለን ለመነጋገር እንሞክር፡፡ ሰንደቅ ዓላማ ለብሶ የሚፎክረው፣ በወያኔ ላይ የውግዘት የቃላት ናዳ የሚያወርደው፣ ወያኔ ዜጎችን በገደለ ቁጥር ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው ወዘተ ሁሉ በርግጥ ለሀገር ነጻነትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚታገል ቢሆን ኖሮ፤ ዛሬ በምንገኝበት ሁኔታና ደረጃ እንገኘ ነበር፡፡
በእውነት ሰንደቅ ኣላማ ለብሶ ኢትዮጵያዊነትን የሚዘምረው ሁሉ ሀያ አምት ዓመታት በህዝብ ላይ የተፈጸመው ይቅርና  በዚህ አንድ መት የተፈጸመው ግድያ እስራትና ማሰቃየት የሚያመው ቢሆን ኖሮ ተቀዋሚዎች አሁን በዚህ ወቅት በሚገኙበት ደረጃ ላይ መገኘት ነበረባቸው፡፡
ሰንድቅ ዓላማ ለብሰው  የምናያቸው ፖለቲከኞች በቃላት እየደለሉ በተግባር ግን  ከሚናገሩት ተቃራኒ ዓላማ የሚያራምዱ ካልሆኑ በአደባባይ ለሚናገሩት ለአንዲት ኢትዮጵያ ነጻነትና ሁሉንም በእኩልነት የሚያስተዳድር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመመስረት ይህን ያህል ፓርቲ/ድርጅት ያስፈልግ ነበር፡፡ በአንድ ብሄር ስም ሶስት አራት ድርጅት፣ ተመሳሳይ ሀገራዊ ፕሮግራም ጽፎ በሰዎች ምክንያት ሶስት አራት ፓርቲ መመስረት ይገባ ነበረ፣ ይህን አድርገው ደግሞ  መልሰው የእኛ አንድ አለመሆን ነው የወያኔን እድሜ ያራዘመው በማለት ያደነቁሩናል፡፡ በዚህም ፕሮፓጋንዳ ራሳቸውን ተባብሮ የመስራት ፈላጊ አድርገው በሌሎች ላይ ጣት ለመቀሰር ቅድሚያውን የሚወስዱትና በድፍረት የሚናገሩት እነዚሁ በዶ/ር አድማሱ ገለጻ ሰንደቅ ኣላማ ለብሰው ሀገር የሚያፈርሱ የተባሉቱ ናቸው፡፡
ያላችሁት በዝታችኋል፣ በተናጠልም መጠናከር ተስኖአችኋል የምትነግሩን የምታምኑበትን ከሆነ ኮከባችሁ የሚገጥም እየተመራረጣችሁ ተባበሩ ተብሎ ልመናም ጫናም ተደርጎ  ህብረት ፈጠርን ቅንጅት መሰረትን ይሉና  የዚህም መሪ ተዋናይ እነርሱ አንደሆኑ አድርገው ከተግባሩ ፕሮፓጋንዳውን አግዝፈው ይነግሩንና ውለው ሳያድሩ ወደ እምነታቸው ተመልሰው የተገናኘውን ሲያላያዩ የተባበረውን ሲፈርሱ ይገኛሉ፡፡እነርሱ ያልገቡበት ህብረት ከተፈጠረም ከዳር ሆነው ውግዘታቸው ትችታቸው ሲብስም ውንጀላቸው አያድርስ ነው፡፡ ደጋፊዎቻቸውም የሚነገራቸውን ለማስማት አንጂ የሚሰራውን ለማየት አይናቸውን አይገልጡምና እገሌን ያላከተተ ህብረት አነ እገሌ የሌሉበት ቅንጅት ወዘተ በማለት መሪዎቻቸውን ተከትለው የቃላት አረራቸውን ይተኩሳሉ፡፡ ተረዳድተውም ለማደናቀፍ ይሰራሉ፡፡
በአንድ በኩል  ብዙዎችን ወደ ጥቂቶች ለመቀነስ ሲደከም በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንዶች አንድ ፓርቲ የነበሩት  አንደ አሜባ ራሳቸውን እያባዙ አንዳንዶች ደግሞ እኛስ ከማን እናንሳለን በሚል ስሜት በሚመስል አዲስ ፓርቲ እየፈጠሩ ልዩነቱን ያሰፉታል ችግሩን ያባብሱታል፡፡ ትግሉ ወደ ፊት ከወያኔ ጋር መሆኑ ይቀርና ሰበብ ምክንያት እየተፈጠረ የጎንዮሽ ይሆናል፡፡
ወያኔ ተንገዳግዶ ላለመውደቅ የመጨረሻ አማራጭ ያለውን  የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ባወጀበት በዚህ ወቅት በተቃውሞ ጎራ የተሰለፉት ወገኖች ሁሉም ለሀገር ነጻነትና ለዴሞክራሲዊ ሥርዓት ከሆነ ትግላቸው  ወያኔ ከተንገዳገደበት መልሶ እንዳይቃና እነርሱም ትግላቸውን ማቀናጀት ካልሆነም የጎንዮሹን ትግል ማቆም የሚያስችል ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ/ስምምነት ማውጣት በቻሉ ነበር፡፡ ግን ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው ሀገር ለማፍረስ የሚሰሩ፣የነጻነት ታጋይ መስለው ለወያኔ እድሜ መርዘም የሚጥሩ፣የዴሞክራሲ ናፋቂ መስለው ከራስ በላይ የማያስቡ አሉና በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻቸንን ሞት በየመድረኩ እየደሰኮሩ እነርሱ ግን ከነበሩበት አንድ ርምጃ ወደ ፊት መራመድ አልቻሉም፡፡
ኢትዮጵውያን ከወያኔ አገዛዝ እንዳንላቀቅ  የሚያደርጉን ከዚህም አልፎ እኔ ከሌለሁ ኢትዮጵያ ትበታተናለች የሚለው የወያኔ ማስፈራሪያ እውን የመሆን አጋጣሚ እንዲያገኝ የሚሰሩ፣ ኢትዮጵያ ትበታተን ብለው በአደባባይ የሚነግሩን ሳይሆኑ ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው ሳይታወቅና ሳይነቃባቸው ሀገር የማፍረስ ተግባር ላይ የተሰማሩት ናቸው፡፡ ስለሆነም ከፍሬያቸው ታውቁዋቸዋላችሁ ተብሎ አንደተጻፈው  ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው በመታየታቸው ወይንም  በማራኪ ቃላቶቻቸውና በአዞ እንባቸው ሳንታለል በተግባራቸው እንመዝናቸው አንለያቸው አንወቃቸው፡፡ ሳናውቃቸው የእኩይ ተግባራቸው ተባባሪ በመሆን ከኋላ ጸጸትና የአብሮ ተጠያቂነት ለመዳን መፍራትም መጠንቀቅም ያለብን በአደባባይ ወጥተው ቅዠታቸውን የሚነግሩንን ሳይሆን ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው ከእነርሱ በላይ ሀገር ወዳድ ታጋይ የሚባልላቸውን ነው፡፡

Ethiopian Unrest Hits Country’s Tourism Industry

Ethiopia’s tourism sector is suffering. The impact of a year of violent protests and state of emergency has led to a decline in tourists visiting the country. Ethiopia had been showing signs of becoming a popular new tourism destination in recent years, attracting people not only for its historical sights, but also for its reputation as one of the safest African countries.
Soldiers intimidating festival participants in the town of Bishoftu.
Rock churches in the historical town of Lalibela, in northern Ethiopia, attract thousands of tourists each year. But the six-month state of emergency declared three weeks ago by the government to deal with months of protests is scaring away tourists.
Belayneh Mengesha is a Lalibela tour guide who was born and raised in the town. He says October is usually the start of the high season but not this year.
“Unfortunately, because of this problems happening in some parts of the country, some just have already cancelled their trips to Ethiopia,” said Mengesha.
Belayneh also says tourism is a source of income, directly or indirectly, for many citizens of Lalibela. Meaning that any decrease of visitors affects the entire community, even though Lalibela has not been hit by the protests and demonstrations.
Oromo and Amahar demonstrators took to the streets to protest the land disputes with the government.
Bram van Loonsbroek flies air balloons over the Oromia region and had to cancel several flights after the state of emergency was declared. He says customers are concerned about their safety and want to stay away from ares with unrest.
“We don’t have anything to do with potential land discussion. Because we land, we pack the balloon and we are back again,” said Loonsbroek. “We do give some landing fee to the farmers. And that’s what we try to do to comfort the passengers to explain simply how we work.”
Ethiopia has seen the number of tourists steadily increase in the last decade. But any development disturbing the reputation of a tourist destination takes a long time to rebuild. The ongoing protests in Ethiopia resulted in clashes with security forces and hundreds of deaths.
Stephen Richer is of Skål International, a global association promoting tourism. He says because it can be so easy for rumors and misinformation to spread, authorities need to be transparent and clearly communicate the situation so visitors can make good decisions.
“So for example, the Ebola was in West Africa and how people stopped going to South Africa, because they didn’t know the facts,” said Richer. “So there is a messaging challenge here, which is, start telling people right away what is accurate. Don’t sugarcoat it.”
Several tour operators say they have about 50 percent less business than last year and some actually welcome the state of emergency in the hope that the protests will quickly stop and tourists will return.

Monday, October 10, 2016

UN rights office calls for independent inquiry following numerous deaths at an Ethiopian festival

(UN News Centre) – Expressing concern at increasing unrest in several Ethiopian towns following deaths of a number of people in unclear circumstances in the country’s Bishoftu town, the United Nations human rights arm has called on protesters to exercise restraint and on security forces to conduct themselves in line with international human rights laws and standards.Our town of Bishoftu has been turned into a scene of blood bath.
“The protests have apparently been fuelled in part by a lack of trust in the authorities’ account of events, as well as wildly differing information about the death toll and the conduct of security forces,” Rupert Colville, a spokesperson for the Office of the UN High Commissioner for Human Rights (OHCHR) told journalists at a regular press briefing at the UN Office at Geneva (UNOG).
“There is clearly a need for an independent investigation into what exactly transpired last Sunday and to ensure accountability for this and several other incidents since last November involving protests that have ended violently,” he added.
According to OHCHR, last Sunday, a number of people died after “falling in ditches or into the Arsede lake” while ostensibly fleeing security forces following a protest at the Irrecha religious festival in Bishoftu, located in the Oromia region, about 50 kilometres south-east of the Ethiopian capital, Addis Ababa. These incidents have caused increased unrest in several other towns in the region.
Furthermore, drawing attention to the cutting off access to mobile data services in parts of the country, including in Addis Ababa, the OHCHR spokesperson urged the Government to address the increasing tensions, including “by allowing independent observers to access the Oromia and Amhara regions to speak to all sides and assess the facts.”
He recalled that in August this year, High Commissioner Zeid Ra’ad Al Hussein had requested access to the regions to enable OHCHR to provide assistance in line with the African nation’s human rights obligations. “We again appeal to the Government to grant us access,” Mr. Colville underscored.
Also at the briefing, the OHCHR spokesperson expressed concern at reports of mass arrests in the Oromia and Amhara regions.
He further noted that two bloggers – Seyoum Teshoume and Natnael Feleke – the latter from the blogging collective Zone 9, were arrested this week, for reportedly “loudly discussing” the responsibility of the Government for the deaths at last Sunday’s festival in Oromia.
“We urge the Government to release those detained for exercising their rights to free expression and opinion,” said Mr. Colville, adding, “Silencing criticism will only deepen tensions.”

Ethiopia declares state of emergency amid protests

(BBC) — Ethiopia has declared a state of emergency following months of anti-government protests by members of the country’s two largest ethnic groups.
Hailemariam Desalegn
Hailemariam Desalegn
The Oromo and the Amhara make up about 60% of the population. They complain power is held by a tiny Tigrean elite.
Violence has intensified since last Sunday when at least 55 people were killed in clashes between police and protesters at an Oromo festival.
Hundreds have died in months of protests, human rights groups say.
Tens of thousands have also been detained, they say.
Declaring the state of emergency, Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn said in a televised address: “We put our citizens’ safety first. Besides, we want to put an end to the damage that is being carried out against infrastructure projects, education institutions, health centres, administration and justice buildings.”
The state of emergency will last for six months.
BBC World Service Africa editor Mary Harper says the violent protests are the most serious threat to Ethiopian stability in a quarter of a century.
The protesters have been attacking foreign companies, she says, threatening Ethiopia’s reputation as a growing economy, ripe for international investment.
The details of the state of emergency remain unclear, but she adds that protesters have already shown they will not back down when faced with force.
Many roads into and out of the capital, Addis Ababa, are blocked by protesters.
The protests are for manifold reason, and include:
  • Muslims unhappy at the imposition of government-approved leaders
  • Farmers displaced to make way for commercial agriculture
  • Amharic communities opposed to their inclusion in Tigre rather than the Amhara region
  • Discontent among groups in various parts of the vast Oromia region
In the most recent unrest in Oromia, at least 55 people were killed in a stampede triggered by clashes between police and demonstrators at the annual Ireecha celebrations – a traditional Oromo seasonal festival.
Police fired tear gas to disperse protesters angered at their handling of the event, witnesses told the BBC.
Protesters say violence by the security forces led to the stampede, but the PM denied security forces had opened fire.
Correspondents say that while the ruling coalition has some solid achievements to show for its 25 years in power, it has been unable to manage the transition from being a secretive revolutionary movement to running an open, democratic government.
Amharic domination, under Ethiopia’s former military government and emperors, was replaced by Tigrean leadership following the overthrow of long-serving ruler Mengistu Haile Mariam in 1991.