Tuesday, May 31, 2016

በእርስ በእርስ ጦርነት ድል ሀያ አምስት አመት ፉከራ

በእርስ በርስ ጦርነት ከሁለቱም ወገን የሚሞተው የአንድ ሀገር ልጅ ነው፡፡ አባትና ልጅ፤ወንድምና ወንድም ከዛና ከዚህ ተሰልፈው የሚገዳደሉበት አጋጣሚም ይኖራል፡፡ ይህም  በ17 አመቱ የርስ በርስ ጦርነት በግልጽ ታይቷል፡፡  ወያኔዎች ለድል የበቁት የኢትዮጵያን ሰራዊት ብቻ ሳይሆን ደርግን ተቃውመው ብረት ያነሱ ነገር ግን ከዋሉ ካደሩ ለህውኃት ህልውና አስጊ ይሆናሉ ያሉዋቸውን ድርጅቶች ጭምር ( ለምሳሌም ኢህአፓ ኢዲዩ ) ተዋግተው፤ከዚህም አልፎ በህውኃትም ውስጥ የተለየ አስተሳሰብ ያራመዱ ወይንም ለሥልጣን ያሰጋሉ የተባሉትን እያሰቃዩና እየገደሉ በመሆኑ መገዳደሉ በአንድ ሀገር ልጆች መካከል ከመሆን አልፎ በቤተሰብ መካከል ጭምር እንደነበር አሌ አይባልም፡፡ ለዚህ ደግሞ ሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ በኢህአፓነቱ በወያኔ እንደተገደለ የሚነገረውን የአቶ በረከት ስምኦን ወንድም መጥቀስ ይቻላል፡፡
በጦርነቱ ተጠቂ የሚሆነው ከሁለቱም ወገን ታጥቆ ለውጊያ የተሰለፈው ብቻ አይደለም፤ በውጊያው መካከል ሰላማዊ ዜጎች ሴት ወንድ ሕጻን አዛውንት ሳያለይ ለጉዳት ይጋለጣሉ፤የሀገር ሀብት ይወድማልና  ይህ ሁሉ የሚያሳዝን እንጂ የሚያስፈነድቅ አይሆንም፡፡ ስለሆነም ሰዋዊ አስተሳሰብ የተላበሰ ሀይል በርስ በርስ ጦርነት አሸናፊ ሆኖ ሲወጣ  የነበረውን አገዛዝ ለመለወጥ ከጦርነት ውጪ ሌላ አማራጭ ባለመኖሩ  ወደንና ፈቅደን ሳይሆን ተገደን በገባንበት የርስ በርስ ጦርነት የገደልንም እኛ የሞትንም እኛ በመሆናችን ጦርነቱ ባደረሰው የሕይወትም ሆነ የንብረት ውድመት ከልብ እናዝናለን፡፡ይህ መሰል ሁኔታ ዳግም በሀገራችን አንዳይፈጠርም ለሰብአዊ መብቶች መከበር ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን መሆንና ለህግ የበላይነት መረጋገጥ አጥብቀን በመስራት የጠፋውን እንክሳለን ማለት ነው የሚጠበቅበት፡፡
ወያኔዎች ግን  ግንቦት ሀያ ሲመጣ በየአመቱ ለቀናት አንዳንዴም ለሳምንታት  ሲተኩሱና ሲገሉ፤ ጋራ ሲቧጥጡና ሲማርኩ ወዘተ የሚያሳዩ ፊልሞቻቸውን እያሳዩን የሚያሰሙት  የጀብዱ ዲስኩር፤ የሚያወርዱት የድል አድራጊነት ቀረረቶና ፉከራ የርስ በርስ ጦርነት አሸናፊ ሳይሆኑ ድንበር ተሻግሮ ሉዐላዊነት ደፍሮ የመጣን ወራሪ ድል ነስተው የመለሱ ነው የሚያስመስላቸው፡፡
ነገሩን ይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው በአሸናፊነት ስሜት ሲታበዩና በጀግንነት ሲፎክሩ የምናይ የምንሰማቸው በአብዛኛው ከደደቢት እስከ ምኒልክ ቤተ መንግሥት በነበረው ትግል ድንጋይ ተንተርሰው ወዲ አኪር በልተው የታገሉት ሳይሆኑ አንድ ቀን ጠብ-መንጃ ነክተው የማያውቁት መሆናቸው ነው፡፡ እንደውም አንዳንዶቹ የድል አጥቢያ አርበኞች የወያኔን ዓላማ ተቀብለው ሳይሆን አያያዙን አይተህ ወደ ሚያደላው በማለት ከመጣው ተጠግቶ መኖርንና እያዘረፉ መዝረፍን የተካኑ አስመሳዮች ናቸው፡፡ እነዚህ ወያኔ ከሥልጣን ቢወርድ ሀጁን  እያወገዙ መጪውን በማወደስ መስሎ ለማደር የሚቀድማቸው የለም፡
ወያኔዎች ዛሬም ከሀያ ዓምስት ዓመታት በኋላ ራሳቸውን ከደርግ ጋር እያነጻጸሩ መሻላቸውን ለማሳየት መጣራቸውና በአሸናፊነት መፎከራቸው ሰራነው የሚሉት የኢትዮጵያን ሕዝብ ቀልብ የሚማርክ ውጤት ስለሌላቸውም ነው፡፡
ይህም ሆኖ ለንጽጽር ከመረጡት ደርግ ጋር በህሊና ሚዛን በገለልተኛንት ስሜት ብናነጻጽራቸው የሚሻሉበት ጥሩ ነገር የመኖሩን ያህል የሚመሳሰሉበትም፣የሚበልጡበትም ከዚህ አልፎ የሚያንሱበትም  ብዙ መጥፎ ተግባር አለ፡፡
ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብትን በወረቀት በማስፈር ይበልጣሉ፡፡ በአፈናው ግን አይተናነሱም፡፡ ሰው በመግደሉም ቢሆን ከደርግ ጋር የቁጥር ሂሳብ ይገቡ ካልሆነ በስተቀር አይተናነሱም፡፡ እንደውም ደደቤቲ ጀምረው የገደሉት ከተቆጠር እንደሚበልጡ አያጠራጥርም፡፡ በአገዳደል ግን ይለያያሉ፣ ደርግ ገድሎ በፍየል ወጠጤ ቀረርቶ በታጀበ መግለጫ ይፋ ያደርጋል፡፡ወያኔዎች ገድለው ሌላ ሰብብ ይፈጥራሉ፤አስክሬን ይደብቃሉ፤ሲጋለጡም የቁጥር ክርክር ይገጥማሉ፡፡ተቃውሞ ከበረታባቸውም ይቅርታ በማለት ለማለዘብ ይጥራሉ፤
በቀደሙት ሥርዓቶች የብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች እስር ቤት በነበረችው ኢትዮጵያ በግንቦት ሃያ ድል ብሄር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብት ተጎናጽፈዋል ነጻነታቸውን ተቀዳጅተዋል ብለው ይደሰኩራሉ፡፡ ነገር ግን  በየክልሉ አስተዳዳሪ የሆኑት ድርጅቶች የህውኃት ሞግዚቶች አንጂ የህዝብ ወካዮች አለመሆናቸው ይጠቀስና  በብዙ አካባቢዎች የተነሱና በኃይል ታፍናው የሚገኙ የራስ አስተዳደር መብት ጥያቄዎች በማስረጃት ይቀርቡና ዲስኩሩን ፍሬ ቢስ ያደርጉታል፡፡
በኢኮኖሚ እድገት ከደርግ መሻላቸውን ሲናገሩ ሕዝቡ የዛሬና የትናንት ኑሮውን እያነጻጻረ ፤በገጠመው የኑሮ ውድነት እየተማረረ አረ የት ጋር እነማን ዘንድ ነው ይሄ እድገት የምትሉት በማለት ይጠይቃል፡፡
ትምህርት ቤት ኮሌጅ  አስፋፋን ብለው ከደርግ ጋር ሲፎካከሩ የትምህርት ጥራቱ ይሳለቅባቸዋል፡፡
ደርግን የመናገር ነጻነት ጠር አድርገው ራሳቸውን ለመኮፈስ ሲዳዳቸው በየእስር ቤቱ በሚገኙት ጋዜጠኞች  ይሳጣሉ፤ በክልል ከተሞች ቀርቶ አዲስ አበባ ላይ  እንኳን የሚታዩት  የህትመት ውጤቶች ከቁጥር የማይገቡ በመሆናቸው ይጋለጣሉ፡፡ ራዲዮና ቴሌቭዥኑ አልበቃ ብሎአቸው የኢንተርኔት የግንኙነት መንገዶችን ለመቆጣጠር በሚያፈሱት ገንዘብ ይሞገታሉ፡፡
የነጻ ገበያ ኢኮኖሚ በማራመድ መሻላቸውን ሲናገሩ ቴሌን የማይነጥፍ ጥገት ብለው ሙጥኝ ማለታቸው ይታሰብና፤የወያኔ የንግድ ድርጅቶች ብዛትና የሚሰሩት ይጠቀስና የሰሞኑ የሜቴክ ዝርፊያም በማስረጃት ይቀርብና የት ጋር ነው ነጻ ገበያ ይባላሉ፡፡
ደርግን የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ብለው እያወግዙ ለቁጥር አንጂ ለተግባር አንዳይኖሩ ያደረጉዋቸውን ፓርቲዎች በማስረጃት በመጠቅሰ መድበለ ፓርቲ ሥርዓት እንደሚያራምዱ ሲናገሩ  የአንድ ፓርቲ ገዢነታቸውን ፓርላማው ያጋልጣቸዋል፡፡ ምርጫ አጭበርባሪነታቸው በማስረጃ ይቀርብባቸዋል፡፡ሌላም ሌላም መጥቀስ ይቻላል፡፡ ስለሆነም ወያኔዎች  ሀያ አምስት ኣመት ሙሉ ራሳቸውን ከደርግ ጋር እያነጻጸሩ መኮፈስን ፣ የበርሀ ፊልማቸውን እያሳዩ  ጉሮ ወሸባ ማለትን  ተግባራቸው አድርገውታል፡፡ በሥልጣን ላይ እስካሉም ከዚህ ድርጊታቸው የሚላቀቁ አይመስልም፡፡
ወያኔዎችን ሀያ አምስት ዓመት ሙሉ የሚያስፎክራቸው አምስት ሆነው ኋላ ቀር መሳሪያ ታጥቀው በጀመሩት ትግል የገበሬ ታጋይ ይዘው የሰለጠነና ዘመናዊ  መሳሪያ የታጠቀውን የኢትዮጵያ ሰራዊት ማሸነፋቸው ነው፡፡ ለአሸናፊነት ለመብቃታቸው በምክንያትነት የሚጠቀሱ( ለምሳሌ በቅርቡ የተጋለጠው የእንግሊዟ ንግስት ደብቅ ርዳታ) እንዳሉ ሆነው የተባለው እውነት ነው፡፡ ትንሽ የነበረው ትልቁን ለማሸነፍ በቅቶ እሱ በተራው ትልቅ ሲሆን ግን ትንሽ ሆኜ ትልቁን ያሸነፍኩ እኔ ጀግናው የሚለው አስተሳሰቡ ላይ ቸክሎ መቆም የለበትም፡፡ እንደዛ ካደረገ ባሸነፈበት መንገድ መሸነፍን  እየጠበቀ  ነው፡፡ ነገር ግን ትልቅ የነበረው  በእኔ ትንሽ በነበርኩት  ሊሸነፍ የቻለው ለምንድን  ነው ብሎ ማሰብ ግን ዛሬ ትንሽ ነው ተብለው በሚናቁት ላለመሸነፍ መፍትሄ ለመፈለግ ያስችላል፡፡ ወያኔዎች ግን የተያያዙት ደርግን በማሸነፋቸው መኩራት ፣በማንም የማይደፈሩ አድርገው በማሰብ መፎከርና የደደቢት ትልማችንን ተግባራዊ ከማድረግ የሚያቆመን አይኖርም በማለት የጀመሩትን መቀጠል ነው፡፡
የወያኔዎችን ድርጊት አሳሳቢ የሚያደርገው በአሸናፊነት መፎከራቸው በማን አለብኝነት መኩራራታቸውና ከደደቢት ህልማቸው ንቅንቅ  አለማለታቸው ብቻው ሳይሆን ፡ከውድቀታቸው በፊት በሚነገራቸው ተመክረው፣  ከሚያደርሱትና ከሚደርስባቸው ተምረው የማይመለሱ መሆናቸው ነው፡፡ እነርሱ ሥልጣናቸውን ከሚያጡ ኢትዮጵያ ብትፈራርስ የሚመርጡ በመሆናቸው ውድቀታቸው  ሀገርንና ሕዝብን ለጉዳት  ይዳርጋል፡፡ ለዚህም ነው ለለውጥ የሚታገሉ ኃይሎች ወያኔን ከሥልጣን ማውረዱን ብቻ ሳይሆን የእሱ መውረድ ሊያደርስ የሚችለው አደጋ አነስተኛ አንዲሆን ለማድረግ ማሰብና መስራት የሚኖርባቸው፡፡
በእያንዳንዱ ርምጃቸውም ገደልን ብለው የሚፎክሩ፤ ማረክን ብለው የሚያቅራሩ፤ ድል አደረግን ብለው የሚኩራሩ መሆን የለባቸውም፤ ይህን ካደረጉ  ከወያኔ አልተሻሉምና ድል ቢቀናቸው አዲስ ንጉሥ አንጂ ለውጥ መቼ መጣ የሚለው ዜማ ለእነርሱም የሚዘፈን ይሆናል፡፡

Prof. Berhanu Nega “The fight with TPLF is in the heartland, not along the border”


 Prof. Berhanu Nega in Washington D.C. May 29, 2016
(ESAT News)— Chairman of the Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy, Prof. Berhanu Nega reiterated that armed operations by his Movement is not along the border with Eritrea as the regime in Addis Ababa would like the people to believe, but is inside the heartland as has been seen in the recent fight with regime forces in Arbaminch, south Ethiopia.
Addressing Ethiopians in North America at a meeting held in Washington DC on Sunday, the Chairman of Patriotic Ginbot 7, an armed coalition fighting the tyrannical regime in Ethiopia said the recent attack against regime forces in Arbaminch has proven the regime’s rhetoric wrong – that the armed group would launch an attack from the country’s border with Eritrea.
An attack by the Patriotic Ginbot 7 forces early this month killed at least 20 regime soldiers while 50 others sustained serious injuries.
Prof. Berhanu meanwhile called on Ethiopians in the diaspora to get organized and stay vigilant so as not to fall into the regime’s trap, which would otherwise destroy the fabric of Ethiopian civic and religious institutions in the diaspora.
He said Ethiopians abroad should work to bring officials of the corrupt regime to justice whenever and wherever they see them. He encouraged Ethiopians abroad to use alternative ways when they send money to their country as remittances are a significant source of foreign currency to the corrupt regime. He also urged Ethiopians to establish democratic institutions wherever they are and strengthen the culture of democracy.

Saturday, May 21, 2016

መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ያላት የሰው ድሀ ሀገር ኢትዮጵያ

በ1982 ዓም  ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆነ አይደለም የት ላይ አንዳለች አንኳን መናገር የማይቻልበት ወቅት .ከአንድ ባልንጀራየ ጋር እየሄድን እኔ ከማላውቀው የእርሱ ጓደኛ ጋር መንገድ አገናኘን፡፡ እናም ሰላምታ ተለዋውጠው  ታዲያስ አንዲት ነህ እንዴት ናችሁ ሲለው  ምን እባክህ ሰውም አለን ሰውም የለንም  ሲል መለሰለት፡፡
ሁለቱ ተለያይተው እኛ መንገድ እንደጀመርን ምንድን ነው ያለው ስል ባልንጀራየን ጠየኩት፡፡ እባክህ እሱ አመሉ ነው፡ ከርሱ ጋር ስናወራ ጓደኞቹ ሁሉ አንደተቸገርን ነው፤ በቀጥታ መናገር አይሆንለትም አለኝ፡፡ ምንድን ነው ስራው ስል ጥያቄ አከልኩ ስራው ወታደራዊ ካድሬ ፣ትውልዱ ጎንደሬ፣ፖለቲካውን በጎንደር አማርኛ እየመሰጠረ ነው የሚያስቸግረን  በማለት ባላንጀራየም እንደመራቀቅ እያደረገው መለሰልኝ፡፡ ሰው አለን ሰው የለንም  የሚለውን አባባል ምንነት ለመረዳት ከባልንጀራየ ጋር ብዙ አውርተንበታል፤ብቻየንም ብዙ ግዜ አውጥቼ አውርጄዋለሁ፡፡
ይህ በሆነ  አስር ዓመት ግድም ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም በጦቢያ መጽሄት ላይ ኢትዮጵያ የሰው ድሀ ካልሆነች ታዲያ የምን ድሀ ልትሆን ነው የሚል ጽሁፍ አስነበቡን፡፡ ይህም ከሆነ አስር ዓመት ግድም (አጋጣሚው ሊገርም ይችላል)   ፕ/ር መስፍንን አግኝቻቸው  ከላይ የጠቀስኩትን ጽሁፋቸውን አስታውሼ ከ90 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ያላት፣ በተለያዩ የዓለም ሀገራት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተሰማርተው የሚሰሩ አንቱ የተባሉ ልጆች ያሏት በማለት ብዙ ነገር ዘረዘርኩና እንዴት የሰው ድሀ ትባላለች ስል ጠየኳቸው ፡፡ በጥሞና አዳምጠው በርጋታ የሰጡኝ ማብራሪያ ረዥምና አጥጋቢ ነበር፡፡ ከግዜው ርዝመት አንጻር ማስታወስ ቢገደኝም አንኳር ነጥቡ እነዚህ የምትላቸው ሰዎች ለራሳቸው ኖረው ሊሆን ይችላል፤ ላስተማራቸው ሀገርና ሕዝብ ምን ሰርተዋል? ከአገዛዝ አላቀውታል? ከድህነት አውጥተውታል? ሰው በሚፈለግበት ግዜና ቦታ ካልተገኘ መኖሩ ብቻ ለሀገር ምን ይጠቅማል የሚል ነበር፡፡
የርሳቸውን ማብራሪያ እያዳመጥኩ አስር ዓመት ያህል ወደ ኋላ ተመልሼ ሰው አለን ሰው የለንም ያለውን የወዳጄን ወዳጅ አስታወስኩት፡፡ የአባባሉ ምንነትና እንደዛ ለማለት ያበቃውም ምክንያት በፕ/ር ንግግር ውስጥ ግልጽ ብሎ ታየኝ፡፡ በቁጥር ብዙ ሰው አለ፤ በቁም ነገር መድረክ በተግባሩ መስክ ግን  ..ማለቱ ነበር የሰው ድሀ ማለት ይህ አይደል ታዲያ፡፡
ብቸኛው ፓርቲ ኢሰፓ ከሲቭልም ሆነ ወታደራዊ ማዕረጋቸው የሚቀድመውን ጓድ መጠሪያቸው ያደረጉ ብዙ እጅግ ብዙ አባላት ነበሩት፡፡ነገር ግን አባሉ በቁጥር በዝቶ  ቁም ነገር ያለው ግን አንሶ  አይደለም ሀገሪቱን ሲያንቆለጳጵሱዋቸው የነበሩትን መሪ ከስደት፤ ፓርቲውን ከሞት፤ ራሳቸውን ከውርደት መታደግ ሳይችሉ ቀሩ፡፡
ኢሰፓ ያልነበሩ እንደውም ኢሰፓን ተቃውመው መንግስቱን አውግዘው ሲታገሉ የነበሩ ባይታገሉም ሥርዓቱን ይቃወሙ ዴሞክራሲን ይመኙ የነበሩ በቁጥር ብዙ  ነበሩ፡፡ ግና ቁም ነገራቸው ሚዛን የሚደፋ የተግባር ሰውነታቸው እስከመስዋዕትነት የደረሰ ጥቂቶች ሆኑና ኢትዮፕያ ሰው እያላት የሰው ድሀ ሆነችና  ከወታደራዊ አገዛዝ ወደ ተጋዳላዮች አገዛዝ ለመሸጋገር በቃች፡፡
ዘመነ ወያኔንም ስናይ ከመነሻው ጀምሮ ወያኔን የሚቃወመው፣ ስለ ለውጥ  የሚደሰኩረው፣  ስለ ዴሞክራሲ  የሚሰብከው፣ ወዘተ ቁጥሩ የትየለሌ ነው፡፡ ግና ከቁም ነገሩ መድረክ ከተግባሩ ስፍራ የሚገኙት ጥቂት በጣም ጥቂት ሆኑና ወያኔ ማን አለኝ ከልካይ እያለ የሻውን እየፈጸመ ሀያ አራት ዓመታት ለመግዛት ቻለ፡፡ ሌላው ቀርቶ በቅርቡ ኢሳትና ቪዥን ኢትዮጵያ በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡትን  በተለያየ የሙያና የእውቀት ዘርፍ ከጫፍ የደረሱ ምሁራንን የተመለከተ  የእነርሱ መሰሎች ሀገር ኢትዮጵያ እንዲህ በአገዛዝ ስትማቅቅ፤፣ከዴሞክራሲ ጋር ሆድና ጀርባ ሆና ስትኖር፣ ሕዝቡ በየግዜው በረሀብ አለንጋ ሲገረፍ ሰው እያላት ሰው ያጣች ሀገር አያሰኝም ትላላችሁ!
የኢትዮጵያ የሰው ድሀነት በወያኔም ውስጥ በገሀድ ይታያል፡፡ በተለያየ መንገድ የድርጅቱ አባልም ደጋፊም የሆኑ አባልና ደጋፊም ባይሆኑ ደግሞ የማይቃወሙ በተለያየ የእውቀትና የሙያ መስክ ላይ የሚገኙ በውጪም በውስጥ ብዙ ዜጎች አሉ፡፡ነገር ግን እነርሱም ቁጥራቸው እንጂ ቁም ነገራቸው የሚታይ ባለመሆኑ ድርጅታቸው በሀገርና  በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ጥፋት ማሰቆም ቀርቶ አንድ መለስ ያለእኔ ማን አለ ብለው ፓርቲም መንግሥትም ግለሰብም ሆነው ናውዘው ለሞት ሲበቁ ሊታደጉዋቸው አልቻሉም፡፡
ይህም ብቻ አይደለም ከአስር ዓመት በፊት ከአምስት ሚሊዮን በላይ አባላት አሉኝ ያለ ድርጅት በቁጥር እንጂ በቁም ነገር (ከሱ ፍላጎት አንጻር) ሚዛን የሚደፋ ሰው አጥቶ ከቦታ ቦታ የሚያገላብጣቸው የተወሰኑ ሰዎችን ነው፡፡ ሴቶችማ ለቁጥርም የሉ፡፡የአሁኑ አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ አንዴ ጀነራል አንዴ አቶ እየተባሉ ስንት ቦታ አንደተገለባበጡ ማስታወሱ ብቻ ለዚህ በቂ ይመስለኛል፡፡
የትውልድ ድርሻውንና የዜግነት ግዴታውን ቅንጣት ሳይከውን በሥልጣኔ ስም ሰይጥኖ ወደ ላይ አንጋጦ ትናትን የማውገዝ ድፍረት በተላበሰው ትውልድ የሚነቀፉ የሚዘለፉት አባቶቻችን በቁጥር ጥቂት ሆነው ከነዛው መካከል ግን የቁም ነገር ሰዎች ብዙም ብርቱም የነበሩ በመሆናቸው ነበር በዙሪያችን ያሉ ሀገሮች በቅኝ ግዛት ሲማቅቁ ኢትዮጵያ በነጻነት የዘለቀችው፤ ዳር ድንበሯን አስከብራ የባህር በሯን አስጠብቃ ለመኖር የቻለችው፡፡ለዓለም ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተምሳሌት ሆና የኖረችው፡፡
ዛሬ ግን አንደ ቁጥራችን ብዛት ከቁም ነገር ያፋቱን፣ ከተግባር ያራቁን ችግሮቻችን በዝተው እኛ የሚናቁት የሚወገዙና የሚኮነኑት አባት እናቶቻችን የቆዩንን ሀገር፣  ዳር ድንበር፣ የባህር በር፣ወዘተ ማስከበርና መጠበቅ ሳንችል ቀረን፡፡  ከወያኔ አገዛዝ ተላቀን የምናወራለትን ዴሞክራሲ እውን ለማድረግ  መስኩ ላይ መገኘት አቃተን፡፡ በእውቀት የበለጸጉ በሙያ የተካኑ በልምድ የዳበሩ አያሌ ልጆቿ  በመላው ዓለም በተለይም በምእራቡ የዓለም ክፍል ተሰማርተው እውቀት ጉልበታቸውን ለሌላ ሀገር እየሸጡ የተደላደለ ኑሮ መኖር ቢቻላቸውም  እውቀታቸውም ሆነ ሙያቸው፣ ልምዳቸውም ሆነ ጉልበታቸው፣ ለሀገራቸው የሚፈይድ አልሆነም፡፡ አንዲህም ሆነና እናት ሀገር ኢትዮጵያ መቶ ሚሊዮን የሚሆን ሰው እያላት  የሰው ድሀ ሆና  አገዛዝ እንደተፈራረቀባት፣ ዴሞክራሲ አንደናፈቃት፣ ረሀብ ልጇን እንዳሰቃየባት ትኖራለች፡፡ ዛሬ እየሆነ ካለው በላይ  የነገው ተስፋ የለሽነት  ይብስ ይከፋል፡፡
መቼ ይሆን! ኢትዮጵያ ልጆቿ  ቁጥራችን ብቻ ሳይሆን ቁም ነገራችንም በዝቶ ሰው እያላት የሌላት የሰው ድሀ ከመሆን የምትወጣው? መቼ ይሆን! በዘር፣ በሀይማኖት፣ በአመለካከት ልዩነት ተለያይተው የመቶ ሚሊዮኖች እናት ግን የሰው ድሀ ያደረጉዋት ልጇቿ ከምንም ነገር በፊት እናታችን ብለው እውቀታቸውን አቀናጅተው ሀይላቸውን አስተባብረው  ነጻነት የሚያቀዳጇት? መቼ ይሆን! ልጆቿ ከራስ በላይ ነፋስ አስተሳሰብ ተላቀው፣ ከመጠላለፍ አዙሪት ወጥተው፣ ከቁልቁለት ጉዞ የሚያቃኑዋትና  የነበረ ዝናና ክብሯን መልሰው የሚያቀዳጁዋት? አረ መቼ ይሆን!ልጆቿ  ዴሞክራሲ እየተረገዘ የሚጨነገፍበትን ሲወለድም   በአጭር የሚቀርበትን በሽታ ተርደተው መድሀኒትም አግኝተውለት ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማድረግ የሚበቁት ? አረ መቼ ይሆን! ልጆቿ የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ሀገር የሰው ድሀ የሆነችው እነርሱ ተለያይተው በመቆማቸው፤ በስልጣን ጥም በመታወራቸው፤ ከእኔ በላይ በሚል አስተሳሰብ በመታጠራቸው፣ለራስ እንጂ ለመጪው ትውልድ የማይጨነቁ በመሆናቸው ወዘተ መሆኑን ተረድተው ከየራሳቸው ታርቀው፣ ርስ በርሳቸው ፍቅር መስርተው፣ አንደ ብዛታቸው ቁም ነገራቸውም ለሀገርና ለወገን ሲበጅ የሚታየው መ? መቼ አረ መቼ !
ተዋቂው የብእር ሰው ሎሬት ጸጋየ ገብረ መድህን  ይድረስ ከእኛ ለእኛ በሚለው ተከታታይ ግጥም ውስጥ እንዲህ ብሎ ነበር፡፡
ይድረስ ወገን ከእኛ ለኛ “እሳት አንሆን ወይ አበባ”
የነገን ራዕይ አንዳናይ ፣በሐቅ እንቅ ስንባባ
መክሊታችንም ባከነች፣ዕድሜአችንን ስናነባ፡፡
ፍቅር ፈርተን፣ሰላም ፈርተን
አንድታችንን ጠልተን ፣ተስፋችንን አጨልመን
የነፍስን አንደበት ዘጋን፣
የልጆቻንን ተስፋ ፣እምቡጥ ሕልማቸውን በላን፡፡
ሳይነጋ እየጨለመ ነው፣ተው ወንድሜ እንተማመን፣
ዓለም ባበደበት ዘመን፣የብረት ምሽግ ነው ወገን፡፡
ኢትዮጵያ ዘለዓለሚቷ፣አንድነት ነው መድኃኒቷ
ሕብረት ነው መፍትሔው ስልቷ፡፡

Saturday, May 7, 2016

Ethiopia: Where Economic Progress and Human Rights Clash


Ethiopian government control of the national media
(Citizens for Global Solutions)— When you think of Ethiopia, images of starving children probably come to mind. But the East African nation has come a long way since the 1984-1985 famine, which claimed over one million lives. Economic growth has increased around 10 percent annually for the past decade, putting it in line with the government’s goal of becoming a “middle-income” nation by 2025.
The country’s “pro-poor” polices are transforming the nation and creating a path to prosperity and stability. Western governments—including the United States and Canada—consider Ethiopia an “island of stability” surrounded by the struggling states of Sudan, Somalia, South Sudan, and Eritrea.
Yet for all its economic success, the Ethiopian government casts a long shadow on human rights.
Last year, a violent crackdown on protesters in Oromia resulted in upwards of 200 deaths, according to Human Rights Watch. The anti-government demonstrations, which were set off by plans to expand the capital Addis Ababa into the region, have been fueled by frustrations over political and economic marginalization. Protesters say the military and police responded with public beatings, unlawful arrests, and even killings.
Eyewitness testimonies, mostly reported via social media and by activists, have been difficult to verify. Restrictions on travel have made independent investigations next to impossible. Journalists can’t travel without permission and are typically assigned a government minder when they do.
Ethiopia’s devastating drought has only pushed human rights concerns further to the margins as the country pleads for foreign aid. And even that narrative is tightly controlled by the government.
CBC Foreign Correspondent Margaret Evans writes of her visit, “Local officials assigned to accompany us on our recent trip were reluctant to allow us to see any real signs of suffering in the face of the drought.”
Restricting access may be due in part to the government’s desire to project an image of strength after decades of being portrayed as a charity case.
“There appears to be a tendency by some in the international humanitarian system to change the message in such a way that what the rest of the world hears from Ethiopia is a shrill cry of an SOS for immediate intervention,” Ethiopia’s communications minister, Getachew Reda, told CBC.
But government control of the national media is far more problematic. Today, Ethiopia is “one of the leading jailers of journalists on the continent,” according to Human Rights Watch.
Ethiopia deserves to be lauded for its economic progress, but unless it begins protecting human rights, millions will be locked out of participating in its development. It will take more than a steady growth rate for the nation to truly become the shining star of East Africa.

Ethiopia: Activist charged after anti-govt Facebook posts

(Agence France Presse)— ADDIS ABABA, Ethiopia: The ex-spokesman for Ethiopia’s main opposition Blue Party has been charged with inciting violence and being a “ring leader” of a banned rebel group after he criticized the government on Facebook.Yonatan Tesfaye charged after anti-govt Facebook posts
Yonatan Tesfaye, who has been jailed since December 2015, in one message accused the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) of using “force against the people instead of using peaceful discussion with the public.”
He was referring to the authorities’ response to protests that have rocked the Oromia region in Africa’s second-most populous nation.
Home to some 27 million people, Oromia encircles Addis Ababa and stretches over large parts of the rest of the country.
It has its own language, Oromo, distinct from Amharic, the language of Ethiopia’s government.
The demonstrations began in November against a government plan to expand the boundaries of Addis Ababa into Oromia.
According to court records, Tesfaye was charged Wednesday with 11 counts including inciting violence “to disrupt the social, economic and political stability of the country.”
He is also accused of being a “ring leader of the far-left Oromo Liberation Front (OLF) to inflame demonstrations,” the court records said.
OLF is a banned separatist movement opposed to the Ethiopian government which police routinely blame for “terrorist” acts.
Authorities consider Tesfaye’s writings as a call to rise up against the government and given the country’s tough anti-terror law he could face up to 15 years behind bars if convicted.
Tesfaye was until recently the Blue Party’s spokesman and comes from a generation of young activists determined to challenge the authoritarian regime that has ruled the nation for 25 years.
“When people become popular and give a voice to the voiceless, (the government) charge them with fabricated charges and put them in jail,” Blue Party head Yilkal Getnet told AFP.
“This is what happened to Yonatan,” he added.
Since the overthrow of a Marxist junta in 1991, Ethiopia’s political and economic situation has stabilized, although rights groups have criticized the government for suppressing opposition.

Thursday, May 5, 2016

የሕዝብ ማእበልና ሱናሚ በመስቀል አደባባይ


የፊታችን ቅዳሜና እሁድ  የሚውሉት ሚያዝያ  29 እና 30   ከአስር ዓመት በፊት በ1997 ዓም በተመሳሳይ ቀናት ነበር የዋሉት፡፡  እነዛ ሁለት ቀናት  በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሥፍራ ይዘው የሚኖሩ ትእይንቶች የታዩባቸው  ነበሩ፡፡ በተለይ ሚያዝያ ሰላሳ በዚህ ትውልድ ዳግም  ይታያል ተብሎ ለመገመት የማይቻል ትእይንት ነው አሳይቶን  ያለፈው፡፡Statement from 9 Ethiopian coalition parties
የምርጫ 97 ዋንኛ ተፎካካሪ የነበረው የአራት ፓርቲዎች ጥምረት  ቅንጅት ከድምጽ መስጫው ግንቦት 7/97 እለት አስቀድሞ በሚውለው እሁድ የምርጫ ዘመቻ ማጠናቀቂያ ሕዝባዊ ትእይንት በመስቀል አደባባይ እንደሚያደርግና የትዕይንቱ መሪ ቃልም ለዴሞክራሲ እናዚም/እንዘምር  የሚል አንደሆነ ቀደም ብሎ አስታወቀ፡፡ ይህን አንደሰማ ኢህአዴግም ለሚያዝያ 29 ቅዳሜ ፕሮግራም አንዳለው ገለጸ፡፡
የኢህአዴግ ትዕይንት ሕዝብ፤
የፖለቲካ ፉክክር አንድም አስቀድሞ አቅዶ በሚፈጸም ተግባር በልጦ መገኘት፣ ሁለትም የተፎካካሪዎችን እንቅስቃሴ እግር በእግር እየተከተሉ የሚሰሩትን በማየትና የሚናገሩትን በመቅለም አጸፋዊ ተግባር መከወን እንደመሆኑ የቅንጅት የምርጫ ዘመቻ ማጠቃለያ  ትእይንተ ሕዝብ ፕሮግራም እንደተሰማ ወይኔ በጥድፊያ  ተዘጋጅቶ ለሚያዝያ 29 በመስቀል አደባባይ ጥሪ አደረገ፡፡ በእለቱም በየቀበሌው የተለመደውን የካድሬ ስራ ሰርቶ፤ ንብ የታተመችበትን ካናቴራ አድሎ፣ ራቅ ላሉ ቀበሌዎችም የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አቅርቦ ሰዉን መስቀል አደባባይ አወጣው ወይንም አስወጣው፡፡ በዚህ ሁኔታ አደባባዩ በሕዝብ ተጥለቀለቀ፡፡ አቶ መለስም አይተውት የማያውቁትን የህዝብ ብዛት በአደባባይ ሲያዩ  እንዴትና በምን ሁኔታ እንደወጣ ሳይረዱ በጥይት መከላከያ መስተዋት ጀርባ ሆነው ባሰሙት ንግግር ስሜት ፈንቅሎአቸው ይህ የህዝብ ማእበል ምንም ማጭበርበር ሳያስፈልገው ምርጫውን ማሸነፍ ይችላል አሉ፡፡ በዚህም  ድርጅታቸው በምርጫ ተወዳድሮ ለማሸነፍ ሳይሆን አጭበርብሮ ለማለፍ የተዘጋጀ መሆኑን አጋላጡ፡፡ መሪዎች በአደባባይ የሚያደርጉት ንግግር ተጽፎ የሚሰጣቸው እንዲህ በስሜት ተገፍተው አደጋ የሚያመጣ ነገር እንዳይናገሩ ይመስለኛል፡፡ አቶ መለስ የተነፈሱትን ማናፈስ ስራቸው የሆኑት የመገናኛ ብዙኃንም በመስቀል አደባባይ የህዝብ ማእበል ታየ በማለት እያጋነኑ አቀረቡት፡፡
ይህ በመስቀል አደባባይ የታየውና ማዕበል ተብሎ የተገለጸው የህዝብ ቁጥር ኢህዴጋዊያንን ሲያስፈነድቅ( ለአንድ ቀንም ቢሆን)  በአንጻሩ ለቅንጅት አመራሮች ብቻ ሳይሆን ለአባላቱና ለደጋፊዎቹም ትልቅ ጭንቀት ፈጠረ፡፡ የጭንቀቱ ምክንያትም በማግስቱ ሚያዝያ ሰላሳ ቢያንስ ተመጣጣኝ የሆነ የህዝብ ቁጠር ይገኝ ይሆን የሚለው ነበር ፡፡
የቅንጅት ትዕይንተ ሕዝብ
እሁድ ሚያዝያ ሰላሳ ጠዋት ቀይ መስቀል፣ በመስቀል አደባባይ ዝግጅት ነበረው፡፡ የቅንጅት ጥሪ ደግሞ ከሰአት በኋላ ነው፡፡  አምስት ሰአት ተኩል አካባቢ መስቀል አደባባይ ስንደርስ  ቀይ መስቀሎች ጓዛቸውን እየጠቀለሉ ሲሆን አደባባዩ በሰው እየተሞላ ነበር፡፡ ሰአት ገና ነው ብለው ወደ አደባባዩ የደረሱት ቅንጅቶች ከጥሪው ቀድሞ የሰዉን መጉረፍ ሲመለከቱ መድረክ የማዘጋጀቱንና   የድምጽ መሳሪያ የመዘርጋቱን ሥራ ማጣደፍ ጀመሩ፡፤ ፌዴራል ፖለሶች ደግሞ ጎን ለጎን ተያይዘው በመቆም ሰዉ ወደ መኪና መንገዱ እንዳይገባ ለማደረግ አጥር ሰሩ፡፡ ነገር ግን የሰዉ ቁጥር ሲጨምር ሲያፈገፍጉ በዚህ መልኩ እየተገፉ ሄደው መጨረሻ ክቡር ትሪቡኑ ስር በሚገኘው ምሽጋቸው ውስጥ ተጠቃለው ለመግባት ተገደዱ፡፡  መንገዱ ሙሉ በመሉ በህዝብ ተሟላ፡፡
ወደ መስቀል አደባባይ የሚያደርሱት ስድስቱም መንገዶች በህዝብ ተጨናነቁ፤ከፒያሳ አቅጣጫ የሚመጣው ከፖስታ ቤት፤ከሜክሲኮ አቅጣጫ የሚመጣው ከቡናና ሻይ፤ ከሳሪስ የሚመጣው ከአራተኛ ክፍለ ጦር፤ ከቦሌ የሚመጣው ከፍላሚንጎ፤ ከመገናኛ አቅጣጫ የሚመጣው ከባምብሲ፤ከአራት ኪሉ የሚመጣው ከታላቁ ቤተ መንግሥት ማለፍ አልቻለም፡፡ የቅንጅቶች መድረክ በሕዝብ ተውጣ እንኳን ከሩቅ ከቅርብም የማትታይ ሆነች፡፡ ከመድረክ የሚነገረውም የሚሰማው  በመድረኩ ዙሪያ  ላሉት ብቻ ሆነ፡፡
ማእበል ለመባል ከበቃው በኢህአዴግ ትእይንተ ሕዝብ ላይ ከተገኘው የህዝብ ብዛት ይህኛው በሁለት ምን አልባትም በሶስት እጥፍ የሚበልጥ በመሆኑ ሱናሚ ተባለ፡፡ በወቅቱ በወያኔ  አደገኛ ቦዘኔ ከመባል አልፎ ህግ ወጥቶ እየታደነ ይታሰር የነበረው ወጣት አደገኛ ቦዘኔ ራሱ ወያኔ፤ ወጣቱ ስራ አጥ አንጂ ቦዘኔ አይደለም በማለት በየምርጫ ቅስቀሳ መድረኮች ሲያሰማው የነበረውን መፈክር በአደባባዩ ከማሰማት አልፎ አደገኛ ቦዘኔ ያለመሆኑን ያሳየበትን ተግባር ፈጸመ፡፡ በአደባባዩ የተተከሉ የጌጥ መብራቶች ስስ ከመሆናቸው የተነሳ በቀላላ ሊሰበሩ የሚችሉ ቢሆኑም ወጣቱ ባደረገው ጥንቃቄና መከላከል በዛ የህዝብ መጨናነቅ ውስጥ አንድም ጉዳት ሳይደርስ ቀረ፡፡ የእጅ ስልኮች ወድቀው ተገኝተው ወደ መድረክ ተላለፉ፡፡ ሰልፉ ከተበተነ በኋላ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ሲሳፈሩ ራሳቸው ስርአት አስከብረው አንድ ሰው ሳይከፍል አንዳይሳፈር ገንዘብ ያልያዘ ካለ ያልያዛ አንዲከፍልለት እያደረጉ ወጣቶች ኢትዮጵያዊ ጨዋነታቸውንና ህግና ሥርዓት አክባሪነታቸውን በተግባር አሳዩ፡፡ ትናንት ለእንጀራችን ዛሬ ለእምነታችን፤ ትናንት ለካናቴራ ዛሬ ለባንዲራ ወዘተ የሚሉ መፈክሮችም በየቦታው ተሰሙ፡፡ እነዚህ  ኢህአዴጋዉያንን በእጅጉ ያበሳጩ እንደነበሩ ለማተዘብ ተችሏል፡፡
የቅንጅቶችም ጭንቀት  ለኢህአዴግ የወጣውን ያህል ህዝብ ይወጣልን ይሆን ከሚለው ይህ ሁሉ ሕዝብ በሰላም በየቤቱ ይገባ ይሆን  ወደሚል ተለወጠ፡፡ ቢያንስ በጥንቃቄና በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ወደየቤቱ እንዲሄድ መልእክት ለማስተላለፍ አለመቻሉ የቅንጅቶችን ጭንቀት እንዳበረታው በመድረኩ እቅራቢያ የነበርን ታዝበናል፡፡ ነገር ግን ፕሮግራሙ አንዳለቀ ከየት መጣ ያልተባለ ዝናም ድንገት ወረደና በተነን፡፡ ከፊሉ መጠለያ ፍለጋ ሲሯሯጥ በተለይ ወጣቱ በቡድን  በመሆን እያዜመ ዝናቡ ምንም ሳይመስለው ጉዞውን ቀጠለ፡፡ምሽት ላይ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የተለመደውን ተቃራኒ ዜና ሰሩ፡፡  ይህ ደግሞ ህዝቡን ይበልጥ አበሳጨው፡፡
የሀያ ዘጠኙ ትእይንተ ሕዝብና የተሰራው ፕሮፓጋንዳ በሰላሳ ሕዘቡ ነቅሎ አንዲወጣ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ ከሰፈሬ አንድ በእድሜ ጠና ያሉ ሰው ትእይንተ ሕዝቡ ላይ ተገኝተው አንደነበረ ሲያጫውቱኝ፤ የቅንጅቶችን ጥሪ አስቀድሜ  ብሰማም የመውጣት እቅድ አልነበረኝም፤ የቅዳሜውን ሰው ሳይ ግን አንዴት እንዲህ ይሆናል አልኩ፤ፕሮፓጋንዳቸው ደግሞ ይበልጥ አበሳጨኝና ለመውጣት ወሰንኩ፡፡ግን ከፖስታ ቤት ማለፍ አልቻልኩም፤ ባየሁት የህዝብ ብዛት ግን በጣም ነው የተደሰትኩት ነበር ያሉኝ፡፡
ዳግም ይታይ ይሆን!
ከዚህ  ማእበልና ሱናሜ ከተባለ ተእይንተ ህዝብ ወያኔ በሚገባ መማሩን ተግባሩ ይመሰክራል፡፡ ተቀዋሚው ግን የተማረ አይመስለኝም፡ወያኔ ቅዳሜ ያን ያህል ሕዝብ ወጥቶ አቶ መለስንም ምስጢር አስወጥቶ በማግስቱ በሁለት እጥፍ መውጣቱ በህዝብ ልብ ውስጥ አለመኖሩን  እንዲገነዘብ አስችሎታል፡፡ በህዝብ ካልተወደደና ተቀባይነት ከሌለው ደግሞ በህጋዊ አግባብ ፍላጎቱና ማሳካት፣ ወንበሩንም ማስጠበቅ አይቻለውም፡፡ ስለሆነም ህገ ወጥ ህጎችን ማውጣት፣ ማናቸውንም አንቅስቃሴዎች በጠመንጃ ጸጥ ማሰኘት፣ ፓርቲዎች  ከቢሮአቸው መግለጫ ማውጣት ያለፈ  እንቅስቃሴ አንዳይኖራቸው ማድረግ ወዘተ ስራው ሆነ፡፡
ወያኔ ያን መሰል የሕዝብ  እንቅስቃሴ ዳግም በኢትዮጵያ እንዳይኖር ለማድረግ ያስቻለውን ስራ ቢሰራ  ከታገለለት ዓላማና  ከሥልጣን ወይንም ሞት መርሁ አንጻር ተገቢ  ነው፡፡  ተቀዋሚዎች ግን ወያኔ ለሥልጣኔ አስጊ ብሎ የፈራው ይህ የህዝብ ተነሳሽነት አስፈላጊነቱን አምነው አንዲቀጥል ለማድረግ የሚያስችል ስራ ለመስራት አለመቻላቸው  ነው እንቆቅልሹ፡፡
በምርጫ 97 ለታየው  የህዝብ ተነሳሽነት የሚጠቀሱ እንደየሰው አስተሳሰብ የሚለያዩ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም  አንዱ ምክንያት አራት ፓርቲዎች  ቅንጅት ፈጥረው አንድ ሆነው መቅረባቸው እና በቅንጅት አመራር ውስጥ  ከዛ በፊት ብዙም በፖለቲካው መድረክ ያልታዩ ሰዎች ብቅ ማለታቸውና የህዝቡን አመኔታ ማግኘታቸው መሆኑ  ሁሉም ሰው የሚስማማበት  ይመስለኛል፡፡
በአንድ ዓላማ ተሳስሮ በልዩነት ተከባብሮ ህብረት ፈጥሮ በአንድ የትግል መስመር ላይ መቆም አንዲህ ተአምራዊ የህዝብ ተነሳሽነት አንደሚፈጥር በተግባር ታይቶ እያለ ለዚህ  መሳካት የየግል ፍላጎትን በመክላትና ድብቅ አጀንዳን በማስወገድ መስራት ሲገባ ፖለቲከኞቻችን ከራስ በላይ ማሰብ እየተሳናቸው  ትብብር ሊፈጥሩ ቀርቶ የጀመሩትንም እያፈረሱና እየበተኑ ለወያኔ እድሜ ማራዘሚያ መድሀኒት ይሆናሉ፡፡
የፖለቲከኞቻችን ችግር ከዚህም ይዘላል፡፡አለመተባበር ብቻ ሳይሆን መቀናናትም አለ፤ አንዱ የተሻለ መስራት ከቻለና የህዝብ አመኔታና ድጋፍ ካገኘ ሌላው እሱም ሰርቶ ለመታመን ከመጣር ይልቅ  ለሚሰራው እንቅፋት ይሆናል፡፡ቅንጅት ሚያዝያ 30/97 ያን ያህል ሰው አደባባይ ስለወጣለት በቅናት ያረሩ በተበለጥን ሰይጣናዊ ስሜት የተቃጠሉ ስሜታቸውን መቆጣጠር እየተሳናቸው ይህን የሚያጋልጡ ቃላት ከአፋቸው ሲያመልጡ እየሰማን ታዝበናል፡፡ ይህን ደግሞ ስም ግዜና ጋዜጦችን እየጠቀሱ ማስረጃ ማቅረብ ቢቻልም  ቢያንስ ለዛሬ ጠቀሜታ የለውምና ይቅር፡፡
በአጠቃላይ ሚያዝያ 29 እና 30/97 ያየነው ትእይንት ዳግም ሊታይ መቻሉ አጠራጣሪ ነው፡፡ ይህም የሆነው  ወያኔ ሕዝብን አደባባይ ቢያወጣ ወደ ተቃውሞ ተቀይሮ በራሱ ጥሪ ራሱ አንዳይወገዝ ተቃውሞ አንዳይደርስበትና በህዝቡም ዘንድ አዲስ መነሳሳት እንዳይፈጠር ስለሚሰጋ  ሲሆን በተቃውሞው ጎራ ደግሞ ያንን ለማድረግ የሚያስችል እቅም ያለው ፓርቲም ሆነ ህብረት ባለመኖሩ ነው፡፡

Getachew Shiferaw – The Price of Freedom of Expression in Ethiopia

Ethiopian Human Rights Project
Name of Detainee-  Getachew Shiferaw
Childhood and education- Getachew Shiferaw was born in Northern Gonder in Belessa district in 1984.  He went to Arbaya, Maksegnit and Fasildes Schools to complete his elementary and high school education.  He has got a Bachlor of arts in Political Science and International Relations form Addis Ababa University.
The Federal Police arrested Getachew Shiferaw.
Getachew Shiferaw
Career- After collage he has started his professional career inInformation Network Security Agency (INSA). After serving there for two years and eight months his job contract was terminated because of his political dissimilarity and post criticizing the former Prime Minister on social media. Then he joined the languishing media industry, started working in Mesenazeria Newspaper as an editor.
In this paper he wrote why he lost his first job. This specific article and other critical pieces made the newspaper vulnerable to government pressure. At last the paper went out of market. Then he continued writing on Piassa and Lifemagazines as a columnist. He was also contributing articles to Ethio-Mihdar Newpaper and Enqu magazines. When Blue Party has established Negere-Ethiopia newspaper, He became the Editor-In- Chief. Even though the newspaper went out of print market after 26 editions, he was actively managing the online version .
There faced lot of intimidation while he was working for Negere-Ethiopia.  From many of them “Why you wrote about the security and military apparatus of the country?”  “ Do you have a plan to dismantle the institutions of the country?” “ Why the Ethiopian satellite Television (ESAT) rebroadcast your news?” “Do you have a link with them?” Were some of the questions repeatedly asked by the intelligence officers interviewed him.
Detention- When he was arrested on 25th of Dec, 2015 the police has raided his home and found Newsletters released by Blue Party and Medrek pary (Legally registered opposition parties) which denounce the action of government on protesters in Oromia. These statements and his articles published in newspaper were the center of his current interrogation.  Getachew has spent more than four months in Maekelawi detention center, out of it he has been in dark room for two months and 18 days. He has been sleeping with 20 suspects in 4X3 meter square cells. He with his cellmates was not allowed to see the sun light for more than 15 munities a day. He was also interrogated in evenings. They have been insulting and intimidating him to get a confession. While he was in the dark room he was not allowed to be visited by his families, friends and his legal advisor.
Now Getachew is transferred in comparatively better cells even though he does not still have access for books. He is still on pretrial detention and no official charges are filed on him even though the legally given interrogation time by the court has expired.