Monday, August 29, 2016

በኢትዮጵያ ያለው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ነውን? ክፍል ሁለት


በክፍል አንድ አንድን ሥርዓት ህገ መንግሥታዊ ሊያሰኙት የሚበቁ በርካታ ጉዳዮችን ትተን በህገ መንግስቱ ላይም የሚነሱ ክርክሮችን አቆይተን ህገ መንግስቱ ባለው መልኩ እንኳን የማይከበር አንዳንድ አንቀጾቹም እስከመኖራቸው የማይታወቁ መሆኑ ብቻውን ሥርዓቱን ሕገ መንግሥተዊ ሊያሰኘው እንደማይችል ጠቅሻላሁ፡፡ ለዚህ መከራከሪያ ይሆናሉ ያልኳቸውን  ጭብጦችም  በማንሳት ከህገ መንግስቱ አንቀጾች የተወሰኑትን በማስረጃነት ለማቅረብ ነበር  የተሰናበትኩት፡፡
ህገ መንግሥቱ ከያዛቸው 106 አንቀጾች  ውስጥ መከበር  የተነፈጋቸውና እስከመኖራቸው የማይታወቁት  ሚዛን ይደፋሉ፡፡ በተለይ  ደግሞ በምእራፍ ሶስት የተገለጹት   መሰረታዊ መብቶችና ነጸነቶች  የተጻፉት ህገ መንግሥቱን አማላይ ለማድረግ ብቻ ነው፡፡  ጥቂቱን በቅደም ተከተል እንያቸው።
አንቀጽ 11 የመንግሥትና የሃይማኖት መለያየት፣
አንቀጽ “11/3 መንግሥት በኃይማኖት ጣልቃ አይገባም ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፣” ይላል፡፡ ጥያቄ ላስቀድም፤ዜጎች በመንግስት ታጣቂዎች ሲጨፈጨፉ የሀይማኖት አባቶች ግድያውንና ገዳዮችን ማውገዝ ቀርቶ ግድያ ይቁም ብለው ድምጻቸውን ቢያሰሙ በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ መግባት ይባላል? ከሆነስ የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን አውግዞ የመንግስትን ግድያ በመደገፍ ርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥል ብሎ መግለጫ ማውጣት መንግስት ከጣልቃ ገብነት በዘለለ እየተቆጣጠራቸው መሆኑን አያሳይም?
የመንግሥትን በሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ለማሳየት ብዙ ማስረጃዎች መዘርዘር ይቻላል፡፡ በዘመነ ወያኔ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ጳጳሶች ተሾመዋል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ከአሜሪካ፣ አቡነ ማትያስ ከእስራኤል ተጠርተው፡፡ሁለቱም ደግሞ ትግረኛ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ ይህ የሆነው እንደ ጀነራሎችና ቁልፍ የምኒስትር ቦታዎች ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ለሊቀ ጳጳስነት የሚመጥን ሰው ባለመገኘቱ ይሆን! አይደለም፣ አባ ደፋር አቦይ ስብሀት አቡነ ጳውሎስ ሞተው የጳጳስ ምርጫ ዝግጅት ሲደረግ  የምንፈልገው ጳጳስ ካልተሾመ እኛ ትግራይ ላይ የራሳችንን ጳጳስ እንሾማለን በማለት የተናገሩት ነው እውነቱ፡፡
የሙስሊሙንም ብንመለከት፣ ህገ መንግሥቱን አምነውና ተማምነው የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ ያቀረቡ ዜጎችን አሸባሪ ብሎ ማሰር፤የእምነቱ አባቶችን ምርጫ በቀበሌ ጽ/ቤት ማካሄድ፣ ዜጎች ያልፈቀዱትን  አስተምህሮ እንዲቀበሉ ማስገደድ ወዘተ፣ታይቷል፡፡ በሌሎች እምነቶችም እንዲህ ጎልቶ ባይወጣም ነጻ አለመሆናቸውን ከድርጊቶቻቸው መረዳት ይቻላል፡፡ በመሆኑም በሁሉም ሀይማኖቶች ውስጥ የሚታየው  የመንግስትን በሃይማኖት ጣልቃ መግባት ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠራቸው መሆኑን ነው ፡፡
አንቀጽ 16 የአካል ደህንነት መብት፣
“ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት አለው፤ ” ይህ አንቀጽ በግልጽ የሚያሳየው በሀገሪቱ ውስጥ ነዋሪ የሆነ ዜጋም ሆነ አልሆነ በማንም፣ በምንም፣ መቼምና በማናቸውም ቦታ ጉዳት እንዳይደርስበት የመንግሥት ጥበቃ አንደሚያገኝ ነው፡፡  በሀገራችን እየሆነ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒ ጥበቃ እንዲያደርግ ግዴታ የተጣለበት መንግሥት ጉዳት  አድራሽ መሆኑ ነው፡፡   ይህ ህገ ድርጊት  ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ የሚከተለውን በአንቀጽ 18/1 የተደነገገውንም የሚጥስ ነው፡፡
አንቀጽ 18 ኢሰብአዊ አያያዝ ስለመከልከሉ፤
“18/.1 ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት ኢሰብአዊ ከሆነ ወይንም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው፤ ” ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛ የተሰራጩት የግድያና የደብደባ ምስሎች ብቻ ለዚህ በቂ ማስረጃዎች ይሆናሉ፡፡ እናክል ከተባለም በማእከላዊ ምርመራና በየእስር ቤቶች በዜጎች ላይ (በተለይ በፖለቲካ አስረኞች ላይ) የሚፈጸሙ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ይጠቀሳሉ፡፡ ኢሰብአዊ ድርጊት ተፈጸመብን የሚል አቤቱታ የሚቀርብላቸው ፍርድ ቤቶች ሰምቶ ዝም ባይ መሆናቸውም ተጨማሪ ማስረጃ ይሆናል፡፡ እነዚህ ድርጊቶች አይደለም ህገ መንግሥታዊ ሥርዓት መንግስት የሚባል ተቋም እንኳ የለሌበት ባለሥልጣኖች ያሻቸውን የሚሰሩበት  ሥርዓት ነው የሚመስለው፡፡
አንቀጽ 20 የተከሰሱ ሰዎች መብት
“20/3 በፍርድ ሂደት ባሉበት ግዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር በምስክርነት እንዲቀርቡም ያለመገደድ መብት አላቸው፤” ይሄ አንቀጽ እስከመኖሩም የሚታወቅ አይመስለኝም፡፡ዜጎች ወንጀል ተፈብርኮላቸው ተይዘው ገና ማእከላዊ ሳይደርሱ  ባለሥልጣናት በመገናኛ ብዙኃን ብቅ እያሉ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር አውለናል ይላሉ፡፡  ፈጸሙዋቸው የሚሉዋቸውን የፈጠራ የወንጀል አይነቶች በመዘርዘርም በቂ መረጃና ማስረጃ አለን በማለት ይፎክራሉ፤ ነገሩ በዚህ ብቻ ሳያበቃ ዶክመንተሪ ፊልም  ተቀነባብሮ በኢቲቭ ይተላለፋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ታሳሪዎቹ ገና ሳይከሰሱ ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ሳይቀርብ  ከተያዙበት ቅጽበት  ጀምሮ ጥፋተኛ ይባላሉ፤ ፍርድ ቤቱም ይህንኑ ያጸድቃል፡፡ ታዲያ ይህን የሚያደርጉ ባለሥልጣኖች የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20/3 ድንጋጌን ያውቃሉ ማለት እንደምን ይቻላል?
አንቀጽ 25 የእኩልነት መብት፤
“ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው፣ በመካከላቸውም ማንኛውም አይነት ልዩነት ሳይደረግ በህግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል፤ በዚህ ረገድ በዘር፣በብሔር፤ ብሔረሰብ፤በቀለም፣በጾታ፣በቋንቋ በኃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ”ይሄ ተግባራዊ ስላለመሆኑ ለማስረዳት መሞከር ለቀባሪው ማርዳት ይሆናል፡፡
አንቀጽ 39 የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት፣
“39/.3 ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰብ ሕዝብ ራሱን የማስተዳደር መብት አለው፡፡ ይህ መብት ብሔር፣ ብሔረሰቡ ሕዝቡ በሰፈረበት መልክዓምድር ራሱን የሚያስተዳድርበት መንግሥታዊ ተቋማት የማቋቋም እንዲሁም በክልልና በፌዴራል አስተዳደሮች ውስጥ ሚዛናዊ ውክልና የማግኘት መብትን ያጠቃልላል፡፡” ሚዛናዊ ውክልና ያገኛል የሚለውን ብቻ እንኳን ለይተን ብናይ ይህ አንቀጽ አስታዋሽ የለሽ መሆኑን ነው የምንረዳው፡፡ሚዛናዊ ሲባል ቁጥር ብቻ አይደለም፣ይህን ያህል ሚኒስትር ከዚህኛው ብሔረሰብ አለ ማለትም ሚዛናዊ የሚለውን አያሟላም፡፡ የክልል መስተዳድር ማቋቋምም ብቻውን ራስን የማስተዳደር መብትን አያጎናጽፍም፣
አንቀጽ 46 የፌዴራል ክልሎች፤
“46/.1 ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝብ አሰፋፈር ፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት ነው፣” ፈቃድ የምትለው ቃል ባለቤት የላትም፤ሆን ተብሎ ወይንስ ተዘንግቶ? ማነው ፈቃጁ? በምን መንገድስ ነው የሚፈቅደው ? ጥያቄው እንዳለ ሆኖ አሁን ያለው የፌዴራል አዋቃቀር ሲከናወን  በዚህ አንቀጽ የተገለጹት የሕዝብ አሰፋፈር ማንነትና ፈቃድ እስከነመኖራቸውም ተዘንግተው ቋንቋ ብቸኛ መስፈርት ተደርጓል፡፡ ደቡብ ክልል ሲታይ ደግሞ ይሄም አልሰራም፣ በአንድ ሀገር ሁለት አይነት የፌዴራል አወቃቀር፡፡
አንቀጽ 50 ስለ ሥልጣናት አወቃቀር፣
“50./ 8 የፌዴራል መንግስትና የክልሎች ሥልጣን በዚህ ሕገ መንግሥት ተወስኗል፡፡ ለፌዴራል መንግሥቱ የተሰጠው ሥልጣን በክልሎች መከበር አለበት፣ለክልሎች የተሰጠው ሥልጣን በፌዴራል መንግሥት መከበር አለበት፡፡ ”ክልሎች ይህን አንቀጽ የሚጥሱበት አቅምም ነጻነትም የላቸውም፡፡ የፌዴራል መንግሥቱ ግን የክልሎችን ሥልጣን ማክበር አይደለም ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎቹ ክልሎች ያሻውን ነው የሚያደርገው፡፡ የየክልሎቹን ባለሥልጣናት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚሾም የሚሽረውም እሱ በመሆኑ የክልሎች ሥልጣን ከወረቀት ያለፈ አይደለም፡፡
በዚህ አድራጎቱም የሚተላለፈው በህገ መንግሥቱ የሰፈረውን የክልሎች ሥልጣን ብቻ ሳይሆን ለፌዴራል መንግሥት የተሰጠውንም ሥልጣን ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ አሁን እየሆነ ያለ ተጨባጭ ማረጃ ላቅርብ፡፡ አንቀጽ 51 በንኡስ አንቀጽ 14 ላይ  “ከክልል አቅም በላይ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ሲያጋጥም በክልል መስተዳደር ጥያቄ መሰረት የሀገሪቱን የመከላከያ ሀይል ያሰማራል፣” በማለት ለፌዴራል መንግሥቱ ሥልጣን ይሰጣል፡፡ ነገር ግን በወረዳ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ህጻናት  ሰልፍ ወጡ ሲባል እንኳን የሚዘምተውና የሚገድለው የመከላከያ ሀይሉ ነው፡፡ ጸጥታ ሳይደፈርስ ክልሉ ከአቅሜ በላይ ነው ብሎ ሳይጠይቅ፡፡
ይህ ደግሞ ሌሎች የህገ መንግሥቱን አንቀጾች በተጨማሪነት የሚጥስ ተግባር ነው፡፡ የህገ መንግስቱ  አንቀጽ52/2/ሰ “ የክልሉን የፖሊስ ኃይል ያደራጃል፣ ይመራል፣ የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስጠብቃል፤”በማለት ሥልጣን የሰጠው ለክልል መስተዳድሩ ሆኖ ኮሽ ባለ ቁጥር መከላከያ ማዝመት የክልሎችን ሥልጣን መጣስ የፌዴራል መንግሥቱንም የሥልጣን ገደብ አለማክበር ነው፡፡ የዚህ  አድራጎት  ህገ ወጥነት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 87/3  የሰፈረውን “የመከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ከመጠብቅ በተጨማሪ በዚህ ህገ መንግሥት መሰረት በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል ፣”የሚለውንም የሚጨምር ነው፡፡ላለፉት ስምንት ወራት በኦሮምያ በቅርቡ በአማራ የተሰማራው የመከላከያ ሀይል በፌዴራል መንግሥቱ ማን አለብኝነት እንጂ  ወይ ክልሎቹ ጠይቀው ወይ የአስቸኳይ ግዜ ታውጆ አይደለም፡፡
ስለ መከላከያ ካነሳሁ አይቀር አንድ አንቀጽ ላክል፡፡ አንቀጽ  87/1 “የሀገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ ይሆናል፡” ይላል፡፡ሚዛናዊ ሲባል በአዛዥነቱም በታዛዥነቱም ቦታ ነው፡፡ሕገ መንግሥት ጥሳችሁ ጀነራል እናንተ ብቻ ሆናችሁ ሲባሉ በትግሉ ወቅት ልምድ ያካበትን ስለሆነ ምንትስ ምንትስ እያሉ የሚያሰሙት ጩኸት ይህን አንቀጽ ላለማክበር ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ በመጀመሪያው ክፍል በጠቀስኩት አንቀጽ 9/1 ሕገ መንግሥቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ ነው፣ማንኛውም ሕግ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግሥት አካል ወይም ባለሥልጣን  ውሳኔ ከዚህ ሕገ መንግሥት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈጻሚነት አይኖረውም” ተብሎ የተደነገገው አክባሪ ቀርቶ አስታዋሽ አላገኘም እንጂ አንዲህ አይነቱ የማን አህሎኝነት ድርጊት እንዳይኖር ነበር፡፡
አንቀጽ 89 ኢኮኖሚ ነክ ዓላማዎች፤
“89/2 መንግሥት የኢትዮጵያውያንን የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ለማሻሻል እኩል እድል  እንዲኖራቸው ለማድረግ ሀብት ፍትሀዊ በሆነ መንገድ የሚከፋፈልበትን ሁኔታ የማመቻቸት ግዴት አለበት፤” ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ የሚያስብል አንቀጽ ነው፡፡ የተጠቀሰው ሁሉ ቀርቶ ዝርፊያው በቆመ፡፡
“89/5 መንግሥት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን በሕዝብ ሰም በይዞታው ሥር በማድረግ ለህዝቡ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፤” ከዚህ አንቀጽ ተግባራዊ የሆነው መንግስት በይዞታው ስር ማድረጉ ብቻ ነው፡፡  መሬታቸውን የሚቀሙት  ዜጎች ተጎጂዎች ናቸው፡፡ አካባቢውም ሆነ አጠቃላይ ሀገሪቱ የሚያገኙት ጥቅም የለም፡፡ ተጠቃሚዎቹ በዝምድና ተሰባስበው፣ በጋብቻ ተሳስረው በፖለቲካ አስተሳሰብ አንድ ዓላማ ይዘው ሀገሪቱን እየገዙ ያሉት ጥቂት በጣም ጥቂት ሰዎች ናው፡፡
አንቀጽ 102 ምርጫ ቦርድ
“102/1 በፌዴራልና በክልል የምርጫ ክልሎች ነጻና ትክክለኛ ምርጫ በገለልተኝነት እንዲካሄድ ከማንኛውም ተጽእኖ ነጻ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል፤” ህገ መንግሥቱ ይህን ቢልም የነበረውና አሁንም ያለው ምርጫ ቦርድ ምን እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ወያኔ ያለ ምርጫ የሥልጣን ቡራኬ እንደማያገኝ፤በህገ መንግሥቱ በተደነገገው መሰረት ነጻ ምርጫ ቦርድ ቢቋቋም ደግሞ እያሸነፈ ሥልጣኑን ማስቀጠል እንደማይችል ስለሚያውቅ ፣የሚያዘውን ምርጫ ቦርድ አቋቋሞ በየአምስት ዓመቱ ምርጫ እያካሄደ ሥልጣኑን ያድሳል፡፡
ወያኔ ህገ መንግሥቱን አክብሮ ነጻ ምርጫ አስፈጻሚ  ማቋቋም ቀርቶ ምርጫ ቦርድ በነጻነት የሚሰራ ተቋም ሆኖ ይደራጅ ብሎ መጠየቅን ሕገ መንግሥታዊውን ሥርዓት በኃይል ለማፍረስ መንቀሳቀስ ነው ብሎ ይወነጅላል፡፡ ለዚህ ደግሞ የቅንጅቶችን የክስ ፋይል ማየት ይቻላል፡፡
ብዙ መጥቀስ ቢቻልም ህገ መንግሥቱ እየተከበረ ላለመሆኑና አንዳንዶቹ አንቀጾቹም ጭራሽ ከነመኖራቸው የማይታወቁ ስለመሆናቸው የቀረቡት በቂ ማሳያ ይመስሉኛል፡፡ በመሆኑም ህገ መንግሥታዊ ሊያሰኙት የሚችሉት ሌሎች መመዘኛዎች ቀርተው ራሱ ለራሱ አንዲመቸው አድርጎ የጻፈውንና በሻው መንገድ ያጸደቀውን ህገ መንግሥት የማያከብር መንግስት ያቋቋመው ሥርዓት  ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ሊባል አይበቃም፡፡ ስለሆነም ትግሉ ወያኔ እንደሚለው ህገ መንግሥታዊ ሥርዓት የማፍረስ ሳይሆን የአገዛዝ ሥርዓትን አስወግዶ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓትን የመትከል ነው፡፡
- See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/16843/#sthash.JUf7Hwml.dpuf

Tuesday, August 9, 2016

(Al Jazeera)— Dozens of people have been killed in a new wave of anti-government protests in the Ethiopian city of Bahir Dar.
Two of the countries biggest ethnic groups in the states of Oromia and Amhara are leading the protests.
Amnesty International says 30 people were killed in the wider Amhara region and another 67 died in violence in Oromia in central western Ethiopia.
Oromo rights activist Hassen Hussein told Al Jazeera that the demonstrations could get more violent.

Ethiopia’s previously divided ethnic groups are unifying to protest against the government



(QUARTZ)— Ethiopia has experienced significant economic growth over the last 25 years, in part by embracing an authoritarian development model. But dissatisfaction with the government’s heavy-handed approach has mounted in recent months, culminating this weekend with thousands of demonstrators from two ethnic groups taking to the streets for the first time together to demand land reform, full political participation, and an end to human rights abuses in the country.
The Oromo and the Amhara making up more than 61% of the country’s population.
The Oromo and the Amhara making up more than 61% of the country’s population.
The demonstrations initially began in November last year in response to the government’s “Addis Ababa Integrated Master Plan,” which sought to expand the capital, currently home to more than 4.6 million people, into neighboring towns and villages inhabited by the Oromo, the country’s largest ethnic group. The Oromo said the plan would displace farmers and stymie the growth of their culture and identity.
The Ethiopian government reacted with brutal force. Human Rights Watch estimates around 400 protesters were killed, many of them students under 18 (the government disputes that number). Thousands were arrested, and Oromo community and government leaders were charged under the country’s harsh counterterrorism laws. Many have since gone on hunger strike to protest the conditions they are facing in prison. Despite this crackdown, the government bowed to pressure created by the protests, canceling the project in January.
Inspired by this mobilization, the country’s second most populous ethnic group, the Amhara, also began protesting against the government on land-related issues in July. The Oromo and the Amhara have a contentious history, but both feel they are politically and economically marginalized, despite making up more than 61% of the country’s population. And over the last few weeks, activists from both groups have expressed solidarity with each other’s protests, in the hopes that together, they can apply pressure on the government to reform.
In response, the Ethiopian government on Friday banned any types of demonstrations and blocked social media. People came out to protest anyway, and at least 97 people from both groups were believed killed by Ethiopian security forces, Amnesty International reported.
“I think we are reaching a tipping point,” says Mohammed Ademo, a Washington DC-based freelance journalist and founder of OPride.com, a website about Ethiopia, and the Oromia region in particular. “In my entire life, as a one-time protestor and organizer myself, I have never seen demonstrations taking place across the country in one day.”
Ethiopia’s government is dominated by the ethnic Tigray, who make up six percent of Ethiopia’s population of 99 million people. The ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) has been in power for 25 years, and the country’s parliament has no single opposition member.

Sunday, August 7, 2016

Ethiopia: TPLF is Killing Innocent Amharas

The minority regime in Ethiopia, led by the TPLF has already started responding violently to the peaceful demands of Amharas who demanded the “Wolekite Committee” leaders who have been abducted two weeks before to be released immediately and their identity as Amhara to be recognized according to the constitution.
Gondar unrest renewed (ESAT Breaking News)
Two dead as land protest hits ancient Ethiopian city Gondar
Following today’s spontaneous support rally at the court where Colonel Demeke Zewdu, one of the Committee members who successfully thwarted his abduction by the TPLF, appeared was violently dispersed by security forces. Two persons identified by their first name as Solomon and Sintayehu were shot dead and many more sustained wounds from bullets, reliable resources indicate.
TPLF since its creation is a narrow ethno-nationalist party that struggles to secede part of Tigray from Ethiopia. In an effort to establish the Tigrian Republic the party in its manifesto of 1967 E.C has declared parts of the current Amhara, Eritrea and Afar regions to be annexed to give the new republic an international border and fertile land to sustain itself. These are the real motives to annex the Wolkite and Tslemt areas of the Amhara people.
Before 1991 TPLF, with the aim to change the demographic composition of these regions, has carried out several untold atrocities against the Amharas who inhabited the areas. In addition to the extrajudicial killing and disappearance and arranged forced marriages of Amhara women with Tigrians, a recent study by human rights activist in the region has exposed the crime that the regime used modern medicines to cause infertility among the Amhara women to reduce demography of the Wolkite natives and the Amhara people in general.TPLF is Killing Innocent Amharas
They have also resettled more than a million ex-combatants who are fully armed to control the area under their hegemony. These has created a strong resentments among the Amharas who lost their properties and becomes a second citizen in the land of their ancestors. They are forced to denounce their identity in order to get services provided by the regional government of Tigray. Such gross violation of Human and Democratic rights have inspired the Wolkite people to demand their identity as Amhara should be recognized and be reunited with the Amhara region.They have the mandate from the people to signed a petition to the House of Federation to look in to the matter.
The people of Amhara have staged massive protest to request the Government to peacefully settle the issue. Despite several attempts to follow all legal means by involving the parliament and House of federations, an institution deals with identity and inter regional border issues, the regime considered the questions raised by the Wolkite Committee as an attempt to destabilize the federation. Such horrendous labeling of protesters as a terrorist act inspired by Eritrea is the regime’s old tactic for externalizing domestic problems. The Wolkite Committee members are a well known and highly respected members of the society that are tasked to present the people’s grievances to the government.
The regime which is fractured by gargantuan corruption and popular discontent and pressures from various ethnic groups have increasingly depended on security and military forces. Such isolation and loss of legitimacy have created a persistent fear in the minority that eventually may lead to civil war.
EPRDF, a coalition of four regional parties is dominated by the TPLF who have created its three surrogates after its own like. The three parties, according to complies from the other coalition members, are run by individuals assigned from TPLF.

Thursday, August 4, 2016

ጠላትን አሳንሶ ማየት የተቃውሞው ጎራ ድክመት

በዚህ ሳምንት በወጣ በአንድ ድርጅት  መግለጫ ውስጥ የተመለከትኳት ወያኔ የበሰበሰ የሳር ጎጆ ነው የምትል ቃል ከአመታት በፊት አንድ ወዳጄ ያጫወተኝን አስታወሰችኝ፡፡ ወዳጄ ብሔራዊ ወታደር ሆኖ ያሳለፈ ነው፡፡፡ እንደ እድል ሆኖ  በሰለጠነበት ማሰልጠኛ ውስጥ ተመርጦ ቀርቶ እዛው ነው የአገልግሎት ግዳጁን የተወጣው ደዴሳ፡፡
“ማሰልጠኛ ማእከሉ ውስጥ  ከአነጋገር ክህሎቱ ድፍረቱ የሚማርክ መቶ አለቃ የፖለቲካ ሰራተኛ ነበር፡፡በዛን ግዜ ሊነገር ቀርቶ ሊታሰብ የማይችልን ነገር እሱ እያዋዛ በድፍረት ያውም በሚያስተምራቸው የጦር አባላት ፊት ስለሚናገር እሱ ነው ዛሬ የሚያስተምረው ሲባል ፖለቲካ ሲባል የሚያመው ሁሉ ሳይቀር ነበር የሚገኘው፡፡
በወቅቱ ኢምፔሪያሊዝም የተነፈሰ ጎማ ነው የሚል መፈክር ይስተጋባ ነበር፡፡ ታዲያ ይህ መቶ አለቃ ሲያስተምር አጋጣሚ እየፈለገ እውን ጎበዝ ኢምፔሪያሊዝም የተነፈሰ ጎማ ነው አይንቀሳቀስም፣አረ ተዉ እንደውም በደንብ አየር የተሞላ በፍጥነት የሚንቀሳቀስ ጎማ ነው እንጂ ወዘተ ይል ነበር፡፡” ወዳጄ እንዳጫወተኝ፡፡
ከዛ በኋላ የሆነውን መናገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ፎካሪው ሶሻሊዝም በነበረበት እንኳን መቆም ተስኖት አይሆኑ ሲሆን የተነፈሰ ጎማ ሲባል የነበረው ኢምፔሪያሊዝም ግን አለምን ተቆጣጥሮ ቀጥሏል፡፡
ለበርካታ ዓመታት ወያኔን አሳንሰው አቅለውና ደካማ አድርገው የሚገልጹ ንግግሮችን አድምጠናል ጽሁፎችን አንብበናል መግለጫዎችን ሰምተናል፡፡ ወያኔ ግን አለ፣ ሀያ አምስት አመት ገዝቶን ለሌላ ሀያና አርባ አመት እየተመኘ ነው፡፡ ጠላትን አሳንሶ ማየትም ሆነ አግዝፎ መመልከት ሁለቱም ጉዳት አላቸው፡፡የመጀመሪያው ለዝግጅት ማነስ ሁለተኛው ለሥነ-ልቦና ሽንፈት ይዳርጋሉ፡፡
ወያኔ በዚህ በኩል ቀልድ አያውቅም፡፡ የበርሀ ትግሉን በአሸናፊት መወጣት፣  የቤተመንግስት ቆይታውንም በበላይነት ማስጠበቅ የቻለው አይደለም  ጠላቴ የሚለውን ድርጅት አንድ ግለሰብን እንኳን በንቀት የማያይ፣ በቸልታ የማያልፍ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ አድራጎቱም የሚቃወሙትን ብቻ አይደለም ሊቃወሙኝ ይችላሉ በሚል ግምት ብዙ ኢትዮጵያውያንን በየዘመናቱ ያጠፋ ድርጅት ነው፡፡ ለሱ ከሥልጣን የሚቀድም ምንም ነገር ባለመኖሩ ሥልጣኑን ለማስጠበቅ ሰው መግደል አይደለም ሀገርን ማፈራረስም ቢሆን ከመፈጸም ወደ ኋላ እንደማይል በሀያ አምስት አመት ድርጊቱ  አሳይቶናል፡፡
ተቀዋሚው ግን የወያኔን ጥንካሬ አምኖ ጠንካራ ጎኑን ለይቶና የጥንካሬውን ምንጭ ተረድቶ ለመገዳደር የሚያስችል አቅም ገንብቶና ስልት አውጥቶ ከመታገል ይልቅ  የወያኔን ደካማነት የሚገልጽበት አዳዲስ ቃላት እየፈጠረ ሲደሰኩር እንደ  ሶሻሊዝም ከምድረ ገጽ ባይጠፋም በ “አልሞትኩም ብዬ አልልም” አይነት ይኖራል፡፡ በርግጥ ወያኔን አሳንሰው የሚገልጹትና በባዶ ሜዳ የሚፎክሩት ሰዎች ምንም ሲሆኑ አላየንም፣ሊሆኑም አይችሉም፡፡ የሚሞተው፣ የሚታሰረው፣ በየማጎሪያ ካምፑ የሚሰቃየው፣ የሚሰደደው ሌላው ዜጋ ነው፡፡
ምርጫ በመጣ ቁጥር የምንሰማውን አንድ ነገር ላንሳ፡፡ ምንም አቅም ሳገነቡ አናሸንፋለን እያሉ ሲፎክሩ ይቆዩና ወያኔ የሚያሸንፈው ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ባለመሆኑ ነው ይላሉ፡፡ ይህ  በየምርጫዎቹ ከሁሉም ፓርቲ ተብየዎች የምንሰማው ነው፡፡ በርግጥም በህዝብ ድምጽ ወያኔ ማሸነፍ አለመቻሉ የሚያከራክር አይደለም፡፡ ጥያቄ የሚሆነው ወያኔ በድምጽ ማሸነፍ አለመቻሉን ስለሚያውቅ ምርጫ ቦርድን ምርኩዙ ካደረገ፤ ያለምርጫ ቦርድ ምርኩዝ ወያኔ ምርጫ ማሸነፍ የማይችል “ደካማ”መሆኑን የተረዱት ፖለቲከኞች ከመናገር ባለፈ ምርኩዙን ለማሳጣት ምን ሰሩ? ካልቻሉ ደግሞ ወያኔ ምርጫ ቦርድን ምርኩዝ እስካደረገ ድረስ አንደማይሸነፍ እያወቁ ለምን አጃቢ ይሆናሉ? ለምን በምርጫ ስም ሰው ያስገድላሉ? የሚለው ነው፡፡
እውን ወያኔ የበሰበሰ የሳር ጎጆ ነው? አረ በፍጹም! በራሱ ሰዎች ቁጥጥር ስር ያዋለው የመከላከያ ኃይል ያለው፤የዘራው የጎሰኝነት ዘር አፍርቶ አብዛኛው ሰው በጎንዮሽ ትግል ተጠምዶ  ክንዱን ወደ እርሱ እንዳይሰነዝር ማድረግ የቻለ፤ ብዙዎችን በተለያየ ጥቅማ ጥቅም በጉያው አስገብቶ በህዝብ ላይ የሚያዘምት፤አዳዲስ አጀንዳ እየፈጠረ የትክረት አቅጣጫ የሚያስቀይር፤ አንዳንድ አገልጋዮቹን የጭዳ ዶሮ ከማድረግ ይቅርታ አስከመጠየቅ በሚደርስ የማስመሰያ ርምጃ የየዋህኖችን ልብ ማማለል የሚችል፤ በሴራም በስራም፣ በህግም በጉልበትም ዓላማውን ተግባራዊ እያደረገ ከመንገዱ ፈቀቅ ሳይል መጓዝ የቻለ ወያኔ እንዴት ቁንቁን የበላው፣ እንዴት የበሰበሰ የሳር ጎጆ፣ እንደምን አንድ ሀሙስ የቀረው ወዘተ ይባላል፡፡ ኢምፔሪያሊዝም የተነፈሰ ጎማ ነው ይባል እንደነበረው መሆኑ ነው፡፡ ራስን መደለያ፡፤
ይህ በየግዜው በተለያየ መልክ የሚሰማው ወያኔን አሳንሶ የመግለጽና በንቀት የመመልከት ነገር በብዙዎቹ ፖለቲከኞች ዘንድ ያለ ነው፡፡ እነዚህ ፖለቲከኞች ግን ህዝብ መስዋዕትነት የሚከፍልበት ትግል ብልጭ ባለ ቁጥር እየተሯሯጡ መግለጫ ከማውጣት ባለፈ ይህ ነው የሚባል ተግባር የማይታይባቸው ናቸው፡፡ በተግባሩ ሳይኖሩበት ወያኔን ሲያናንቁና ሲፎክሩ  ሀያ አምስት አመታት ተቆጠሩ፡፡ እነርሱም ተምረው የተግባር ሰው አይሆኑ፣ ወያኔም ተምሮ ከዴሞክራሲ ጋር አይታረቅ፣ በዚህ መሀል ጭቆና ያንገፈገፈው፣ አገዛዝ ያስመረረው ሕዝብ አደባባይ እየወጣ ሲያልቅ ይቆጫል ያንገበግባል፡፡

Blocking Social Media in Ethiopia: New Perspectives on Human Rights Violations

Earlier this month, the government of Ethiopia blocked multiple social media sites–Facebook, Twitter, Instagram and Viber–for days on end during the course of annual university entrance exams. The government initiated the shutdown in order to prevent students from sharing answers or otherwise cheating on the exams but went on to claim that it had blocked the sites because they were “a distraction” for students. It is not entirely clear from where the order to launch the shutdown came. Daniel Berhane, editor of Horn Affairs magazine, tweeted that there was no transparency regarding who made the decision and that the government issued no statement on how long social media would be blocked for. The ban on social media ultimately only lasted for a handful of days, as long as the examinations were held, but even though the duration of the ban was relatively short, its scope is troubling.Blocking Social Media in Ethiopia
Ethiopia is not the first nation to block social media during exams–Algeria and Iraq took the same measures this spring after students published exams online. However, this could set a troubling precedent for government control of the web. The UN has defended the internet as a basic human right and has passed a resolution (albeit non-binding) that condemns nations that intentionally disrupt citizens’ internet access. Internet shutdowns have frequently been used in times of violence or impending violence–like during the terrorist attacks on Istanbul, during protests in Bahrain, Venezuela and across sub-Saharan Africa. There are arguments to be made that preventing people from sharing their location on social media can protect innocent people from being attacked if they are in imminent danger, but social media blocking is more often used to disenfranchise “troublesome” populations. Imagine if social media had been efficiently blocked for the entirety of the Arab Spring. Without social media access, populations cannot share their stories beyond the immediate, local level. In 2015, Freedom House reported that Ethiopia was blocking critical opposition websites, including international news outlets–outlets such as the BBC were jammed by the government. There was presumably no threat to the general populace if BBC ran its stories, there was only a threat to the government’s control of information voters were exposed to going into the election.
The UN resolution was a step in the right direction but its non-binding nature means that the council that signed off on it–which included multiple countries that have launched internet shutdowns against their own populace–has no imperative to truly monitor whether the internet is being denied without cause to certain populations. Activist organizations like Access Now work to protect freedom of expression online but short of drawing attention to the problem and encouraging pushback, there is relatively little they can do to block an internet shutdown. VPNs (Virtual Private Networks) have let users in China access Google, Facebook and other blocked websites for years but the VPNs are no longer a secret that governments are unaware of–they are well-publicized tools. As the methods by which the populace circumvents an internet blockage expand, governments are not falling behind. In nations such as Ethiopia where blanket control of social media is a task well within the reach of the government, there is no number of VPNs or new apps that can effectively prevent the disruption of personal expression online.

Tuesday, August 2, 2016

ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ እና እንድምታው

በሰሞነኛው የአዲስ አቤ ቀልድ ልጀምር። ወጣቱ፣ ሱሪ ለመግዛት ወጥቶ አንድ የልብስ ሱቅ ወስጥ ገባ። ባለ ሱቁ ጠየቀው። “የቻይና ይሁንልህ ወይንስ የአውሮፓ ሱሪ?”  ወጣቱም መለሰ። “የለም የለም… የጎንደሩን ሱሪ ነው የምፈልገው።”
GondarProtest107
ታሪካዊው የጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ
እስረኞችን የማስፈታቱ ሰላማዊ ጥያቄ የእብሪት መልስ ሲያገኝ፤  ጨዋታውም ተቀየረ።   “እንዲያውም አናውቅህም። ከህዝብ ጫንቃ ላይ ወረድ” ሲል ነበር የጎንደር ሕዝብ ብረትን ሰብሮ ዙፋኑን የነቀነቀው። “ወንዱን በምርቃና ሴቱን በቃና አደንዝዘን ይዘነዋል!” ያሉት ሕዝብ ከቶውንም እንዳልተዘናጋ አሳየን….  የመናገር እና ሃሳብን ያለፍርሃት የመግለጽ መብትን ህወሃት ሲፈልግ የሚሰጥ ሲያሻው ደግሞ የሚነፍገው የግል ሃብቱ አድርጎ ለ25 አመታት ሰንብቶ ነበር። ይህ መብት በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አሸብርቆ ጎንደር ላይ ተከበረ። በባህርዳር፣ በደሴ፣ በኦሮምያ፣ በመቀሌ…. ላይም ይቀጥላል..
ከአርባ አመት በፊት የቬትናም ህዝብ ባዕዳን ያነገሱትን አሻንጉሊት መንግስት በሃይል ሲነቀንቀው፤ አሻንጉሊቱ ስርዓት ለሕዝብ እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አልነበረውም። የህዝብ ያልነበረው ይህ መንግስት ወደ አመሻሹ ላይ ካመሸገበት የአይጥ ጉድጓድ ሆኖ መግለጫ ሰጠ። እንዲህ ሲል፣
“ስልጣኑን ለህዝብ ለማስረከብ ከንጋት ጀምሮ እየጠበቅኩ ነው።…“
የሰሜኑ ህዝብም ምላሽ የተጠበቀው ነበር፣  “ይህን ለማድረግ ትንሽ ዘገየህ።… የሌለህን ስልጣን እንዴትስ ልታስረክብ ትችላለህ?…“
ይህ ተላላኪ መንግስት ወድቆ የነበረው ከህዝባዊው አመጽ እና እንቢተኝነት በፊት መሆኑን አላስተዋለውም። ስርዓቱ የወደቀ ራሱ ያወጣውን ህግ ራሱ ሲሽረው ነበር። ሕዝብ “መንግስት የለም!” ማለት የጀመረው ለአፋኝ አዋጆች አልንበረከክም ብሎ አደባባይ በወጣ ግዜ ነበር።  ይህ መንግስት የተወገደውም ለዜጋው የመብት ጥያቄ የጥይት ምላሽ በሰጠ ግዜ ነው።
“የዘመናችን ትልቁ ክስተት!”  ብሎታል የኩባው ፊደል ካስትሮ።
ባለፈው እሁድ በጎንደር የታየው የሕዝብ እንቢተኝነትም የዘመናችን ትልቁ ክስተት ነበር። ሕዝብ የተፈጥሮ መብቱን ተነጥቆ በጫንቃው ላይ ተጭኖ የነበረውን ቀንበር ያስወገደበት ክስተት!  ስልጣን የህዝብ እንጂ የጥቂቶች መፈንጫ አለመሆኑ የታየበት ክስተት። በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ወርቃማ አሻራ ጥሎ ያለፈ፤ ለሀገር የፍቅር፣ ለዜጎች የፍትህ እና የህብረት ሃውልትን የተከለ ክስተት። የማይቻል የሚመስለውን ተራራ ደርምሶ የናደ ሃይል ስለነበር ታሪክ ይህንን ሰልፍ ይዘክረዋል።
ግዙፉ የጎንደር ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተተናቀቀ፣ የህወሃት መገናኛ ብዙሃን የሆነው ፋና ራዲዮ ሲዘግብ፤
“የጎንደሩ የተቃውሞ ሰልፍ በሰላም ተጠናቀቀ።…” ነበር ያለው። “ጋዜጠኛው” ከምጥ እንደተገላገለች ሴት በረጅም ተነፈሰ።   በስፍራው ያልነበረው መገናኛ ብዙሃን በስፍራው የነበረውን ክስተት ሲደሰኩር፣ ለሰላማዊ ሰልፍ ፍቃድ የተከለከለ ህዝብ በራሱ ፈቃድ መውጣቱን፤ በሰልፉም ላይ እነሱ የከለከሉትን ባንዲራ ብቻ መያዙን ጨምሮ አበሰረ።
ይህንን የዜና እወጃ ያዳመጠው የጎንደር ሕዝብ  “ይህን ለማድረግ ትንሽ ዘገየህ።… “  ሳይለው አልቀረም።  ልክ እንደ አሻንጉሊቱ የቬትናም መንግስት፣ የህወሃት የአፈና ግዜ ማብቃቱን እያረጋገጡት ይመስላል። አንድ ስርዓት መንግስትነቱ የሚያከትመው ራሱ ያወጣውን ህግ ራሱ ሲረግጠው እና ሕዝብም ለሱ አዋጅ ተገዥ አለመሆኑን ሲያሳየው ነው።  አላስተዋልነው ይሆናል እንጂ ህወሃት እድሜውን ጨርሶ በባከነ ሰዓት እንደሚንገዳገድ “የልማቱ” ተጠቃሚዎች ሳይቀሩ ነግረውን ነበር።  እነ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ እና አበበ ተ/ኃይማኖት (ጆቤ) ከማጀታቸው ወጣ ወጣ ብለው አገሪቱ እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ፣ መንግስት በሚባለው እና በፓርቲ መሃል እንኳን ልዩነት እንደጠፋባቸው ነግረውናል።  ይህ ጉዳይ ጻድቃንን ግራ ካጋባው ሌላው ምን ይበል? ጆቤ የህወሃት ሙስና እና የፍትህ እጦት ካስፈራው ተራው ህዝብ ምን ይሰማው?  የሚገርመው ነገር፣ እያየነው ያለው ቀውስ  የነ ፃድቃን እና የነ ጆቤ “ሌጋሲ”ም ጭምር መሆኑ ነው።
የጎንደሩ አመጽ ሁለት አበይት ነገሮችን ጥሎልን አልፏል። አንደኛው መተባበር እና መደጋገፍን ማስተማሩ ነው::  አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል እንዲሉ፤  በተለይ የኦሮሞ ወገናችን ደም የሁላችንም ደም ነው ማለታቸው የህወሃትን ከፈፍሎ መግዛት እቅድ የሚያፈርስ መፈክር ነበር።  የአኙዋክ መገደል ከአማራው መገደል ተለይቶ አለመታየቱን፣ የሲዳማው ሰቆቃ.. የሁሉም ወገን ስእቆቃ እንደሆነ… የሚያሳይ ትእይንት ነበር። በማን አለብኝነት የሚጫኑ አዋጆችን መስበር መቻሉ ደግሞ ስልጣን ዛሬ በህዝብ እንጂ በአንባገነኖች እጅ አለመሆኑን አሳይቶናል። ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ለመብቱ ፈቃድ እንደማያስፈልገው ብቻ ሳይሆን ይልቁንም ጥንት አባቶቹ  በአደራ ያስረከቡትን ባንዲራ ይዞ በመውጣቱም የስርዓቱን ማክተም አሳይቶናል።
የማይነካ የመሰለው ጉልበቱ ሲፈታ፣ የማይሰበር የመሰለው ሃይል ሲሰበር ይህ የመጀመርያው አይደለም። በዘረፉት ሃብት እና በሰራዊታቸው ጉልበት ብቻ እየተማመኑ የገዛ ወገናቸውን ሲበድሉ የኖሩ አንባገነኖች ከቶውንም መቶ አመት ሲቆዩ አላየንም። በአለማችን የተነሱ ብርቱ የሚባሉ አንባገነኖች በህዝብ ሃይል እየተዋረዱ መውደቃቸውን የታሪክ መዛግብት ይመሰክራሉ።
የማያልቅ መንገድ እና የማይነጋ ጨለማ የለም። በአንጻሩ የማይመሽ ቀን የለም። የብዙዎ አንበገነኖች ችግር በጉልበታቸው ብቻ በመተማመን ዙፋናቸውን ዘላለማዊ ለማድረግ ማሰባቸው ነው።   በዚህች ተለዋዋጭ አለም ውስጥ ለውጥ  የሰው ልጅ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ግደታም ነው። ዘገምታኛም ይሁን ቅጽበታዊ፣ እኛም በተራችን ለውጥን የምናይበት ወቅት ላይ ደርሰናል።
ይህ ሊሆን ግድ ነው። ጽዋ እስኪሞላ የሚጨመርለትን ሁሉ ይሸከም እና ከሞላ በኋላ መፍሰሱ ሳይንሳዊም፤ ተፈጥሯዊም ህግ ነውና ከአቅሙ በላይ ሲሞላ ሁሉም ነገር ይፈስሳል። ከየአቅጣጫው ሕዝቡን ገፍተው እዚህ አደረሱት። እነሆም የሕዝብን የቁጣ ወላፈን ትላንት በኦሮሞ ወንድሞቻችን፣ ዛሬ ደግሞ በጎንደር አዩት። ነገ በደቡብ፣ ከዚያም በምስራቅ እና በምእራብ ይቀጥላል። ይህ ቁጣ የመጀመርያው እንጂ የመጨረሻው አይደለም።
“የዚህን መንግስት ያህል በህዝብ ክፉኛ የተጠላ ስርዓት በህይወት ዘመኔ አይቼም ሆነ ሰምቼ አላየሁም።” ሲሉ አንድ ከፍተኛ የኢህአኤግ ባለስልጣን ሲናገሩ አድምጫለሁ። ከውስጣዊ ሰዎች  እንደምንሰማው ከሆነ 90 በመቶ የሚሆኑት የኦህዴድ እና የብአዴን አመራር አባላት ከህወሃት ጋር ሆድና ጀርባ ከሆኑ ሰንበትበት ብለዋል፤ የህዝቡ በደል አንገሽግሿቸው ህዝባዊውን አመጽ ለመቀላቀል በመጠባበቅ ላይም ናቸው።  በራሱ በአገዛዙ ውስጥ ያሉ ሁለተኛ ረድፈኞች ሳይቀሩ እንደሚመሰክሩት፤ የህወሃት ወንጀል ደርግ ከሰራው ወንጀል እንኳን ሊወዳደር አይችልም። የበደሉን ብዛት እና የዝርፊያውን ግዙፍነት የሚመሰክሩት ሁሉ ይህ ስርዓት በቅርጽ እንጂ በይዘት እንደሌለ ነው እየመሰከሩ ያሉት። “በአሁን ሰዓት በመንግስት ስም የሚነግድ የማፍያ ቡድን እንጂ መንግስት የለም!” ነው ያለው አንድ ከፍተኛ የብአዴን ሰው።
ሕዝቡ ይህንን ሰርዓት ለምን አይጥላው? ሁሉም ስለታፈነ ሕዝብ ነው የሚናገሩት።  አንድ ለአምስት ተጠረንፎ የተያዘ ሕዝብ፣ እስከውስጥ ገመናው በኢህአዲግኛ መስፈርት እየተገመገመ የሚሰቃይ ሕዝብ፣ ሌት ተቀን በሙስና እንደመዥገር እየተበዘበዘ ያለ ሕዝብ። ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል እንኳን ለመጥራት እየተጸየፉ፣ ሀገርን እና ታሪካዊ ባንድራዋን እየጠሉ፣ … እንዴት ሊቆዩ ይችላሉ?
ለችግሮች ሁሉ መፍትሄያቸው ጠመንጃ ነው። የጎንደሩንም ችግር በጠመንጃ ለመፍታት እየመከሩ ይገኛሉ። በመጀመርያ ከህዝቡ መሳርያ መንጠቅ። ከዚያም እንደ በኦሮሞ ወጣቶች እንዳደረግነው በአልሞ ተኳሾች አማጺውን መልቀም ይኖርብናል ሲሉ ዶ/ር ደብረጽዮን መናገራቸው እየተሰማ ነው። ከ500 ያላነሱ የኦሮሞ ወገኖቻችንን ጨርሰው ሲያበቁ፤ እርምጃው ተመጣጣኝ እና ፍትሃዊ ነው ሲሉ ቀለዱብን። ለመሆኑ ከአንድ ሰብዓዊ ፍጡር እንደዚህ አይነት ፍጹም አረመኔያዊ ነገር ይሰማል?  የጭካኔ ጣርያው የት ድረስ ነው?…
መገናኛ ብዙሃን ላይ እየወጡ በህዝብ ላይ የሚያላግጡት ነገር ደግሞ እጅግ ያሳምማል።  ለጥያቄዎች ሁሉ አንድ መልስ ነው ያላቸው። መልሱም “ሻዕቢያ” የሚባል ግዑዝ ነገር። የኦሮሞ ሕዝብ ሰቆቃ ይቁም ብለው የተነሱት ወጣቶች በሙሉ “የታጠቁ እና የተደራጁ የሻዕቢያ ቡድኖች ናቸው” ተባልን። የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ያነሱት ወገኖች ሁሉ ያሻዕቢያ ተላላኪዎች እንደሆኑ ነገሩን። የታገልነው ለነጻነታችን እንጂ ትግሬ ለመሆን አይደለም ያሉት ከራሳቸው ውስጥ ያሉ ታጋዮችም የሻዕቢያ መልዕክተኞች ናቸው።  የችግሮቻቸው ሁሉ መንስኤው ሻእቢያ ነው። ይህ ሊሆን ይችላል። 10 ሰው የሻዕቢያ ተላላኪ ሊሆን ይችላል። 100 ሰውም የሻዕቢያ ተላላኪ ሊሆን ይችላል። 1000 ሰው የሻዕቢያ ተላላኪ ሊሆን ይችላል። አንድ ሚልየን ህዝብ የሻዕቢያ ተላላኪ ከሆነ ግን ከነጻነት ትግሉ ጀርባ ሻዕቢያ እንዳለ ነው እየነገሩን ያሉት።  ፖለቲካን እንደ ማስንቆ እየቃኘ የሚጫወትበትን ህዝብ፣ እነሱ የሚናገሩትን ሁሉ እንደ ስንዴ እየፈለፈለ እንደሚያበጥረው እንኳን አይገነዘቡም።
የምስራቁ ፈላስፋ ኮንፋሽየስ “ትልቁ እውቀት የራስን የድንቁርና መጠን ጠንቅቆ ማወቅ ነው“ ይለናል። ይህንን ሁሉ ህዝብ የሻዕቢያ ተላላኪ ሲሉ በድፍረት መናገራቸው የድንቁርናቸው መጠን ምን ያህል የወረደ መሆኑን ያመላክተናል።  “በወልቃይት ጠገዴ ስቃይ እና እስር ይብቃ!“ የሚለው መፈክር የሻዕቢያ ከሆነ ሻዕቢያ ለወልቃይት ህዝብ መብት በመነሳቱ ሊወገዝ ሳይሆን ይልቁንም ሊወደስ ይገባዋል። እንደ ጣዕረ-ሞት እየተከተለ እንቅልፍ የሚነሳቸው ሻዕቢያ “ለሱዳን የተሸጠው ድንበራችን ባስቸኳይ ይመለስ!“ የሚል መልዕክት ይዞ ህዝብን ማሰለፍ ከቻለ ወዳጅ እንጂ ጠላት አይሆንም።
ሁሌም ህዝብን ማታለል የሚችሉ ይመስላቸዋል። ትላንት የተጫወቱበትን ካርታ ሳይቀይሩ ዛሬም ለመጫወት ይሞክራሉ። በኮብልስቶን፣ በአንሰተኛና ጥቃቅን… ወዘተ የተያዘ ወጣት ሁሉ ፣ በደል ያላመረረው፣ ንቀት ያላስቆጣው መሆኑን አሁን ማረጋገጥ ይችላሉ።
ካሁን በኋላ እነሱ ሊያደርጉ የሚችሉት አንድ አስፈሪ ነገር ቢኖር፤  የትግራይን ህዝብ ከወንድሙ የአማራና ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ደም ማቃባት ብቻ ነው። እዚህ ላይ ነው ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ የሚገባው። የትግራይ ህዝብ የዚህ አናሳ ቡድን እዳ ከፋይ መሆን የለበትም።  የትግራይ ሕዝብም በቡድን-በቡድን ተከፋፍሎ የሚሰቃይ መሆኑን መረዳት ይኖርብናል። የተገመገመ፣ የሚገመገም እና ለት ተቀን የሚገመግም ቡድን!  ይህ ሕዝብም ነጻ መውጣት አለበት።

የፍርሃት ከፈን፤ በጎንደር ተቀደደ፤ የጎሕ ብርሃን በኢትዮጵያ ፈነጠቀ! (የጎንደር ሕብረት፣ ልዩ መግለጫ)

በቅድሚያ የአምባ ገነኖችን ፉከራ ደፍሮ፤ ከፊት ለፊቱ የተደገነውን መሳሪያ ተረማምዶ፤ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ላዉለበለበዉ ጀግናዉ የጎንደር ህዝብ ያለንን አድናቆት በደስታ እና በከፍተኛ ክብር ልንገልጽ እንወዳለን። የትግራይ ነፃ አዉጭ ግንባር በማስፈራራት ለዘመናት ቀፍድዶ የያዘውን የፍህራት ጨለማ ዘመነ ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ/ም በጎንደር ህዝባዊ ሃይል ተገፈፈ። ትግራይ ላይ ተወልዶ፤ የሕዝብ ደምን በከንቱ እያፈሰሰ፤ ጎንደር ላይ አድጎ፤ ምኒልክ ቤተ መንግሥት የገባው የወያኔን ሥራዓት የዉድቀት፤ ግባ ከመሬቱ ጎንደር ላይ ተቆፍሮ፤ ሊቀበር የአንድ ጀምበር ያክል ጊዜ ቀርቶታል። ወያኔ ቀበርኩት ያለው አንድነታችን፤ በዳግማዊ ቴውድሮሶች፤ ዛሬም እንደገና ሁለተኛውን ምእራፍ በጥንታዊት ጎንደር ከተማ ላይ መፃፍ ጀምሯል። ከህዝቡ አብራክ የወጣው መደበኛ ሰራዊት፤ ፖሊስና ልዩ ሃይል፤ ህዝባዊ ሚሊሻ የህዝቡ ደስታ ተካፋይ መሆኑን፤ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ሥንታዘብ ደግሞ፤ የአገራችን ኢትዮጵያ ታሪካዊ ክብር ቀጣይነትና፤ የነ ስብሐት ነጋ “እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” ከንቱ ቅዠት መሆኑን እና ለዉጥ የተጠማዉ የህዝብ አንድነት አስተማማኝ ደረጃ መድረሱን ስናረጋግጥ ደስታችን መጠን የለዉም። ትግሉ ያለማቋረጥ ይቀጥላል። “የነብርን ጅራት አይዙም፤ ከያዙም አይለቁም” እንዲሉ ከዚህ በኋላ፤ ለዚህ ዘረኛ እና ቂመኛ ቡድን ጊዜ መስጠት እጅግ አደጋ ነዉ።
Enough of the TPLF Dominance! Protesters in Gondar
Enough of the TPLF Dominance! Protesters in Gondar
በመሆኑም፤ የወያኔው ቡድን በተፈጥሮው፤ እውነትን መቀበል የማይችል፤ ከራሱ ጥቅም በቀር ለኢትዮጵያችን የሚያስብ ቡድን ሥላልሆነ፤ ሁሉም የትዮጵያ ህዝብ የጎንደር ወንድም /እህቱን የትግል ቆራጥነት ፈለግ ተከትሎ ሳይዉል ሳያድር፤ በመላ አገራችን፤ ከዋና ከተማ እስከ ወረዳ እና ቀበሌ ድረስ በአን ድምጽ ለህዝባዊ ትይንት በመዉጣት ከመለዮ ለባሹ ጋር ተባብሮ ይህን ዘረኛ መንግስት ለደቂቃ ያህል ፋታ ሳይሰጥ፤ የጥፋት እጆቹን በመቁረጥ፤ አዲሱን ዓመታችን፤ ሁሉም ዜጋ በነፃነቱ፤ ኮርቶ እና ተከባብሮ የሚኖርባትን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንድንመሰርት፤ ጥሪያችን እናስተላልፋለን። ከአሁን በፊት በተግባር፤ እንዳየነው፤ የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ጊዜ ለመግዛት የእርቀሰላም ጨዋታ ሊጠይቅ ይችላል። ብዙ ድርጅቶችንም በመድረክ ወጥታችሁ አረጋጉ፤ ካሃናትንም ይህን ጨዋ ህዝብ አስታርቁን፤ ገዝቱልን ማለቱ አይቀርም። የኢትዮጵያ ህዝብ የተማመነበት አንድ ሃቅ ግን አለ። ያም! ወያኔ ሰላም የሌለዉ፤ ሊጠገን የማይችል፤ የበሰበሰ የሳር ጎጆ መሆኑን ብቻ ነዉ። ይህን ቂመኛ ቡድን አምኖ የሚደራደር ሁሉ፤ በአንገቱ ላይ ገመድ እንደማስገባት የሚያስቆጥር ሲሆን፤ ለማደራደር፤ የሚሞክሩ ደግሞ ኢትዮጵያዊነታቸውንም ሆነ፤ ኢትዮጵያችን ቆፍረው እንደቀበሩ ይቆጠራል። የወያኔ ሥርዓት የህዝብ አመኔታ አቶ ያከተመ ዘረኛ ስርዓት ነዉ። በየአካባቢ ተደራጅተህ ጀግና መሪህን መርጠህ ኢትዮጵያዊነትህን እና ታሪካዊ ፍቅር ያለህ ህዝብ መሆንህን አሳይተሃል እና ማንም ዓላማህን ወደኋላ እንዳይጎትት በቆራጥ ጀግንነትህ አረጋግጥ። በጎንደር አደባባይ ያውለበለብከውን፤ የኢትዮጵያዊነት ምልከት የሆነዉ ሰንደቅ ዓለማንን በሌሎች ሁሉም የኢትዮጵያ አደባብዮች፤ አዉለብልብ። ወያኔን አስወግደን ህዝባችን መክሮ ያመነበት መንግስት በእርግጠኛነት ይቋቋማል። በመቶ የሚቆጠሩ ድርጅቶች ባንዲራ አንግቦ “እኛን ተከተሉን መሪያችሁ ነን” ማለት ለ82 ነገዶች ለተዋበችው ብርቅየ ኢትዮጵያችን ምንም አይነት ፋይዳ የለዉም። መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተባብሮ እጅና ጓንት ሁኖ ሳይዉል ሳያድር የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባርን ስርዓት ለማስወገድ በቆራጥነት የጎንደር ህዝብን ተጋድሎ አጋዥ መሆን ችላ የማይባል የትግል ጥሪ ነዉ። በዚህ የነጻነት ትግል መሃከል ለስልጣንና የግል ጥቅማቸውን ለማራመድ የሚስበደበዱ ሁሉ፤ የትግሉ አጋር አይደሉም እና በመንገድህ ላይ ደንቃራ እንቅፋት እንዳይሆኑህ፤ እየጠራርክ፤ ወደ ድል አጥቢያህ ገሥግሥ።
በሌላ በኩል፤ የትግራይ ተወላጆች፤ በወያኔ ግዳጅም ይሁን፤ ነገርን አርቆ ካለማዬት፤ ከእውነት በራቀ ድርቅና፤ የወልቃይት መሬት የኛ ነው በሚል፤ የምታደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ እና ወያኔያዊ ድጋፍ፤ አገራችንን ወደ ባሰ ቀውስ የሚከት ከመሆኑም በላይ፤ በመላ አገሪቱ ኮራ እና ዘና ብለው፤ ሰርተው ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች፤ ችግር እየፈጠራችሁ መሆኑ ተገንዝባችሁ፤ በአስቸኳይ፤ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንድትቆሙ፤ ልናሳስብ እንወዳለን።
አስቸኳይ አገራዊ ጥሪ፦
አገር ውስጥ ያላችሁም ይሁን፤ ውጭ አገር ያላችሁ፤ ለአገራችሁ አንድነት፤ ለሕዝባችሁ መብት የቆማችሁ፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ የስባዊ መብት ተከራካሪ ብዙሃን ድርጅቶች፤ የሃይማኖት እና የሙያ ተቋማት፤ ለአገር ተቆርቋሪ የሆናችሁ ሁሉ፤ ያላችሁን ጥቃቅን ልዩነቶች ወደ ጎን ትታችሁ፤ ኢትዮጵያችን ካለችበት ተረክበን፤ በተረጋጋ ሁኔታ እንድናስቀጥል፤ በፍጥነት፤ ወያኔን ሊተካ የሚችል፤ ብሄራዊ እርቅን መሰረት ያደረገ የሽግግር መንግሥት እንድታቋቁሙ፤ በኢትዮጵያ አምላክ እንማፀናለን።
በመጨረሻም፤ እ. ኢ. አ በ07/24/2016 ዓ.ም በጎንደር ከተማ በተደረገው፤ ሰላማዊ ሰልፍ፤ እናቶች ለተሰላፊው ውሃ በማቅረብ፤ መለዮ ለባሹ፤ ከአብራኩ ለወጣው ህዝብ ያሳየውን ክብር፤ ተሰላፊው፤ ያሳየውን ጨዋነት እና አገራዊ ፍቅር፤ ያነገባቸው መፈክሮች እና የተሸከመው ዓላማ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት፤ ከመሆኑም በላይ፤ ወያኔን ከትግራይ ወገኖቻችን ለይቶ ማየቱን፤ እያደነቅን፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ሊከተለው የሚገባ ቀጣይ ፈለግ መሆኑን ልናሳሥብ እንወዳለን።
የዘረኛው ሥራዓት በሕዝባዊ ኃይል ይደመሰሳል!
የኢትዮጵያ አንድነት እንደገና ይገነባል!!
ጎንደር ሕብረት