FREEDOM OF EXPRESSION FOR ALL ETHIOPIANS
RADIO & TV
(Move to ...)
ESAT tv
▼
OPPOSITION PARTIES
(Move to ...)
Ginbot7
OLF
Andinet (UDJ)
Semayawi (blue) party
▼
NEWS & VIEWS
(Move to ...)
Ze Habesha
ECADF
Ethiomedia
The Maleda Times
Ayyaantuu News
Bilisummaa
▼
Monday, December 15, 2014
በቅስቀሳው ወቅት የታሰሩት አመራሮችና አባላት አሁንም አልተፈቱም
ነገረ ኢትዮጵያ
ለ24ቱ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ እያሉ የታሰሩት ማቲያስ መኩሪያ የሰማያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ ህዝብ ግንኙነትና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ፣ ባህረን እሸቱ የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ኃላፊ እንዲሁም ሲሳይ ዘርፉ እስካሁን ድረስ አልተፈቱም፡፡ ባህረን እሸቱና ማቲያስ መኩሪያ ከ30 በላይ እስረኞች ሶስት በአራት በሆ
ነ ክፍል ታጭቀው በሚታሰሩበት ወረዳ 9፤ እንዲሁም ሲሳይ ዘርፉ ላዛሪስት በሚባል እስር ቤት ታስረው የሚገኙ ሲሆን ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ተገልጾአል፡፡
ሶስቱም ታሳሪዎች ‹‹ለህገ ወጥ ሰላማዊ ሰልፍ በመቀስቀስ›› በሚል ክስ ቀረበባቸው ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የታሰሩት አመራሮች፣ አባላትና ተሳታፊዎች እነዚህ እስረኞች ላይ ከቀረበው በበለጠ ‹‹ህገ መንግስቱን በመናድ›› በሚል ክስ ተከሰው 14 ቀን ቀነ ቀጠሮ ከተሰጠባቸው በኋላ ቀድመው መፈታታቸው ይታወቃል፡፡
በአዳር ሰልፉ ወቅት ከፍተኛ ድብደባ ከደረሰባቸው መካከል የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ቡልቻ አባ ኑራ አንዱ ነው፡፡ ይህ ከተደበደበ ከ8 ቀን በኋላ የተነሳ ፎቶ ግራፍ ነው፡
No comments:
Post a Comment
‹
›
Home
View web version
No comments:
Post a Comment