RADIO & TV

OPPOSITION PARTIES

NEWS & VIEWS

Wednesday, April 22, 2015

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን ሰልፍ ለመበተን ፖሊስ ተኩስ ከፍቷል

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን ሰልፍ ለመበተን ፖሊስ ተኩስ ከፍቷል፣ አስለቃሽ ጭስም እየተጠቀሙ ነው፣ ወጣቶች በሰልፉ የተገኙ የወያኔ ባለስልጣናትን ንግግር በጩኸት ተቃውሟል
ምንጭ (ነገረ-ኢትዮጵያ እና ECADF)Addis Ababa protest, against the government and ISIS
የወያኔ አባላት በአውቶብሶች ተሞልተው ወደ መስቀል አደባባይ ያመሩ ሲሆን፣ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን እያሰሙ በእግር ነበር ወደ አደባባዩ እያመሩ ያሉት… ፖሊስ ወደ መስቀል አደባባይ የሚያስገቡ መጋቢ መንገዶችን ዘግቶ እነርሱ የማይፈልጉትን መፈክር የያዙትንና መፈክር የሚያሰሙትን እየደበደበ ለመመለስ ጥረት እያደረገ ነው። በአሁኑ ሰዓት ወጣቶች ከፖሊስ አምልጠው በቅርብ በሚገኝ ለቅሶቤት ተሸሽገዋል። ቀደም ብለው አደባባዩ የደረሱት መንግስትን የሚያወግዙ መፈክሮችን እያሰሙ በመሰባሰብ ላይ ናቸው።
ዘግይቶ በደረሰን ዜና፣ ፖሊስ የመንግስት ደጋፊ ሰልፎኞችን ከተቃዋሚዎች መለየት ስለቸገረው ሁሉንም በመደብደብ ሰልፉን ለመበተን ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
በአሁኑ ሰዓት ፖሊስ በሁሉም አቅጣጫ ሰላማዊ ሰልፈኛው ላይ እየተኮሰ ነው፣ አስለቃሽ ጭስም መጠቀም ጀምረዋል።
ወጣቶቹ አሁንም ተቃውሟቸው ቀጥለዋል! ‹‹ሌባ! ሌባ! ሌባ!››
በርካታ ሰው ጉዳት ደርሶበታል! ብሄራዊና ሌሎችም አካባቢዎች ወጣች ተቃውሟውን ቀጥለዋል! በርካቶች ታስረዋል፡፡ የልዩ ኃይል አባላት በርከት ብለው ተሰማርተዋል!

ለቀጥታ ዘገባ የፌስቡክ ገጻችንን ይጎብኙ…

Ethiopian police opened fire

No comments:

Post a Comment