RADIO & TV

OPPOSITION PARTIES

NEWS & VIEWS

Monday, July 27, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ማይ-ሰገን አካባቢ በሰነዘረው ጥቃት በርካታ የወያኔ ታጣቂዎችን ሙትና ቁስለኛ አድርጓል

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ማይ-ሰገን በተባለው አካባቢ የሚገኙትን የኢህአዴግ የሰራዊት አባላት በአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በደረሰባቸው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ምክንያት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን ተገለፀ።Patriotic Ginbot 7 freedom fighters continue attacking TPLF
ባለፈው ቀናት በሑመራ አካባቢ ማይ ሰገን በተባለው ቦታ ላይ የግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በኢህአዴግ ሰራዊት ላይ ባደረሱት ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ብዛት ያላቸው ታጣቂዎች ከጥቅም ውጭ ማድረጋቸውን የገለጸው መረጃው በውጊያው ከተገደሉት ታጣቂ አመራሮችም መካከል፣
ኮማንደር ወልደሚካኤል ገብረእዝጊአብሄር የሃይል አዛዥ የነበረ፤ ካሕሳይ ነጋሽ በባዕኸር የሚልሻ አዛዥ የነበረ፤ ለግዜው ስሙ ያልታወቀው የሻምበል ማእርግ ያለው በ24ኛ ክፍለጦር የሓይል አዛዥ የሆነውና ሌሎች የሚገኙባቸው እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
እነዚህ የስርዓቱ ታጣቂዎች- በአካባቢው ሰላማዊ ህዝብ የተለያዩ ግፍ ሲፈፅሙ የቆዩ በመሆናቸው የተነሳ የግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በላያቸው ላይ እርምጃ መውሰዱን የተገኘው መረጃው አስረድቷል።
ምንጭ – ትህዴን

No comments:

Post a Comment