RADIO & TV

OPPOSITION PARTIES

NEWS & VIEWS

Monday, October 19, 2015

ትንሽ የፈንጅ ማምከኛ ስለሆነው የህወሃት ሠራዊት (አንተነህ ገብርየ)

በህወሃት የመከላከያ ሰራዊት ዙርያ በተደጋጋሚ ጹሑፍ ለአንባብያን ማቅረቤ ይታወሳል ዛሬም በዚሁ ዙርያ በማህበራዊ ገጾችና በመገናኛ ብዙሃን ከሰማኋቸውና ከተመለከትኳቸው ተነስቼ ትንሽ እንድል አስገደደኝና ይህችን መጣጥፌ እንድታነቡልኝ አቀረብኩ።ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ሠራዊቷን ወደ የተለያዩ አገሮች በመላክ ወታደራዊ እርዳታ ታደርግ እንደነበር ታሪክ ይዘክራል።የሚላኩት ወታደሮችም ግዳጃቸውን ፈጽመው በክብር ይመለሳሉ ሲመለሱ የአገሪቱ መንግሥትም የክብር አቀባበል ያደርግላቸዋል።ይህ ከጥቅም ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው የወዳጅነት ትብብርም አገራችን በክብር ቦታ እንድትቀመጥ አድርጎ ቆይቷል።ለምሳሌ በቅርቡ የኮርያ መንግሥት ወደ ኮርያ ዘምተው ለነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ድጎማና የጡረታ ክፍያ እንዲያገኙ አድርጓል።ሲሄዱ በክብር ሲመለሱም በክብር መሆኑ ደግሞ ለዘማቾቹ ለዘማች ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ እሴት ነው።Ethiopian soldier in Somalia
የዛሬዎቹ ገዥዎቻችንም ለመንግሥታዊ ሥልጣናቸው እድሜ ማራዘሚያ የጀርባ አጥንት የሆነውን ሠራዊታቸው ወደ የተለያዩ አገሮች በመላክ ሰራዊቱን ትልቅ የገቢ ምንጭ ማድረጋቸው በግልጽ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። በጣም የሚያሳዝነው ነገር ግን በአንድ ጎሣ የበላይነት የሚመራው ይህ ሠራዊት ሲታመም መታመሙን ሲሞት መሞቱን እንዳይጋለጥ በማፈን በምስጢር በመያዝ ሠራዊቱ ምን ያህል እየተሰቃየ እንደሚኖር የአፈናውን ኬላ ሰብረው የወጡ ማስረጃዎች በግልጽ እንድናያቸው አድርጓል።
ከነዚህም አንዱ ከአልሸባብ ጋር በተካሄደ ጦርነት አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸውን የመለከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ኬኒያ ወስዶ በአንድ ሆስፒታል የጣልው ህወሃት ቁስለኞቹ ወይም የአካል ጉዳት የደረሰባቸው የሠራዊት አባላት ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰባቸውና ጠያቂም እንዳያገኙ(እንዳይኖራቸው) በማድረግ አፍኖ ለማስቀመጥ ያደረገው ጥረት ምስጢር ሆኖ ሊቆይ አልቻለም።ምሥጢሩ ተጎልጉሎ እንዲወጣ እየተደረገ ነው እናት በድባብ ትሂድ እንጅ እንደወያኔ(ህወሃት) አያያዝማ ቢሆን ኖሮ አይናቸው ያልወደደውን ወይም በደፈረሱበት ወቅት የተገኘውን ሰላማዊ ሕዝብ ሁሉ ተራበተራ እየገደሉ መርዶ ነጋሪና አብረው እያላቀሱም ሊጨርሱት እንደሚችሉ በዙ መገለጫዎችን ማስቀመጥ ይቻላል።ይዋል ይደር እንጅ የዚህን ዋጋ እንደሚከፍሉም ያውቃሉ። ይህ የምታዩት ምስል በሶማሌ የህወሃት መከላከያ ሠራዊት ከተገደለ በኋላ እግሩን በገመድ አስረው ሲጎትቱት የሚያሳይ ፎቶ ነው ይህንም ከሃዲነት መገለጫቸው የሆነው የህወሃት ዘመናውያን ሊክዱን ይከጅላቸው ይሆናል።ሶማሌዎቹን ለምን እንደዚህ አደረጋችሁ ለማለት አንድም መብት ያለው ኃይል ሊኖር አይችልም።ህወሃት ወደ ሶማሌ ጦር ሲያዘምት ከኢትዮጵያ ደህንነት ለሉዓላዊነቷ ታስቦ እንዳልሆነ ይታወቃል ሶማሌን ሊያለሙም አይደለም የሄዱት።ጉዳዩ በዚህ ሰራዊት ከሚገኘው ገቢ አንጻር እንጅ ከፍ ብየ ጠቀስኩትን ለማድረግማ ህሊናቸው አይፈቅም ሞራሉም የላቸውም።በነገራችን ላይ የሚሞቱትም ከሌሎች የማህበረሰቡ ክፍል(በተለይም ከኦሮሞውና አማራው) ተመልምለው የሄዱት እንጅ ከወርቃማው የትግራይ ሕዝብ የተፈጠሩ የትግራይ ተወላጆችና የመከላከያ ሰራዊት አዛዦችና መኮንኖችማ እንኳን እርሳስ ሊነካቸው የጥይት ድምጽም አይሰሙም።ያካበቱትን ሀብት ማን ሊበላው? «እዚህ ላይ የአሜሪካውን ፕረዘደንት ቃል ልዋስና አሜሪካ ወታደሮቿን ወደ ሶማሌ አታዘምትም የሚዘምት ወታደር እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ እያለን ለምን ?ነበር ያለው።» ስለዚህ ህወሃትም ሌሎችን እየላኩ ማስገደል እንጅ የትግራይ ተወላጅ የሆነማ ለምን? 1/ምርጥ የሰው ዘር ስለሆኑና 2/አዋጊ እንጅ ተዋጊ ባለመሆናቸው አይሞቱም።
እንደ አለመታደል ሆኖ ከዚሁ ሠራዊት ጋር በሰላም አስከባሪነት ወደ ሶማሌ እንዲዘምቱ የተደረጉት የዩጋንዳ ወታደሮች ሲሸኙ በክብር ነው በጦርነት ሲሞቱም የአገራቸው ሕዝብና መንግሥት በአገር አቀፍ ደረጃ የሀዘን ቀን ተደርጎላቸው ሰንደቅ ዓላማቸው በሀዘኑ ምክንያት ስቅ ብሎ እንዲውለበለብ ፤ ቤተሰቦቻቸው እንዲጽናኑ ተደርጎ ነው።የህወሃት መሳፍንቶች ግን እኛ ባስጨረሱት ሠራዊት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እያልን ስንጮህ እነሱ ደግሞ፦የፊት የፊቱ ያስተፋታል በላይ በላይ ያጎርሳታል እንዲሉ ደርግ ያደርግ እንደነበረው መጠነሰፊ የሆነ ምልመላ እያካሄደና በኃይል አስገድዶ ለማዝመትና ለማስጨረስ ከፍተኛ ሁከት መፍጠሩ የሰሞኑ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ይገኛል።እዚህ ላይ ምን አልባት ወጣቱን ጦርነት ውስጥ ማግዶ ራሱ ህወሃት ሊጨርሰው ፈልጎ ካልሆነ በስተቀር ከዚህ ቀደም ያሰለፈው ሠራዊት እራቁቱን እያስቀረውና ክዳቱን ለማስቆምም እስራትን እንደ አንድ መፍትሔ ወስዶ የመከላከያ ሠራውት አባላቱ እንደ ሌላው የፖለቲካ አክቲቭስት ፤ጋዜጠኛ፤ ጦማሪና የፖለቲካ መሪዎች ለእስር እየተዳረገ እንደሚገኝ የተለያዩ የብዙሃን መገናኛዎች እየዘገቡት ይገኛል።እንግዲህ ይህን ሁሉ እያወቀ ክፍት የሥራ ቦታ አግኝቻለሁ ብሎ የህወሃትን የመከላከያ ሠራዊት የሚቀላቀል« ያላረፈች እጅ…»እንደሚባለው ይሆናል ማለት ነው።

No comments:

Post a Comment