ለዚህች ጽሁፍ መነሻ ምክንያት የሆነኝ አቶ ግርማ ሰይፉ የዶ/ር መረራ የቡዳ ፖለቲካ እና መቀበል ያቃተው መራራ እውነት በሚል ርዕስ ያስነበቡን ጽሁፍ ሲሆን ርሳቸው ለጽሁፋቸው ምክንያት የሆናቸው ደግሞ “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች” የሚለው የዶ/ር መረራ መጽሀፍ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የቡዳ ፖለቲካ የሚለው ቃልም ከዚሁ መጽኃፍ የተገኘ ነው፡፡
ዶ/ር መረራ የቡዳ ሰፈር ሰዎች ብለው ምሳሌ ጠቅሰው የሀገራችንን ፖለቲካም ከዚህ ጋር አመሳስለው ሁሉም ፖለቲከኛ ሌላውን የወቅሳል፣ይወነጅላል እንጂ ራሱን አይመለከትም፣ የራሱን ድርሻ አይወስድም፣ተጠያቂነትን አይቀበልም በሚል ነው፡፡ይህ እውነት ነው፡፡ ነገር ግን አብዛኛውን እድሜአቸውን በፖለቲካ ያሳለፉት ዶ/ር መረራ የቡዳ ፖለቲካ ካሉት አስተሳሰብ የተላቀቁ ሆነው አይታዩም፡፡ ለዚህም ይመስላል አቶ ግርማ #የቡዳ ፖለቲካው ዋና ሰለባ ዶ/ር መረራ ነው$ ያሉት፡፡ ዶ/ር መረራን የቡዳ ፖለቲካ ሰለባ ያሉት አቶ ግርማም ቢሆኑ ከዚህ የራቁ አለመሆናቸውን ከዚሁ ጽሁፋቸው ብቻ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
ዶ/ር መረራና የቡዳ ፖለቲካ ፤
በራሳቸው በዶ/ር መረራ አገላለጽ የቡዳ ፖለቲካ እነርሱም እኛን ይላሉ እኛም እነርሱን እንላለን፤ሁሉም ጣቱን ወደ ሌላው ይቀስራል እንጂ ራሱን አይመለከትም ነው፡፡ከዚህ አንጻር ዶ/ር መረራን በጥቂቱ ብናያቸው የሚሉትን የሚያደርጉ፣ሌላውን በሚወቅሱ በሚከሱበት ጉዳይ የራሳቸውን ድርሻ የሚወስዱ ሆነው አይታዩም፡፡ሌላው ቢቀር እየተረገዘ ለሚጨነግፈው፣ እየተወለደ በአጭር ለሚቀጨው፣ የፓርቲዎች ትብብር ዋንኛ ተዋናይ ሆነው አንድም ግዜ ኃላፊነት ሲወስዱ ያልተሰሙ ወዘተ በመሆናቸው ሌሎችን ሊገልጹ የተጠቀሙበት የቡዳ ፖለቲካ ርሳቸውንም ይመለከታል፡፡ ነገር ግን ዶ/ር መረራ እንደሌሎቹ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ብቻ ሳይሆኑ የፖለቲካ ሳይንቲስትና እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ወጣቱን ትውልድ በአ.አ ዩኒቨርስቲ ሲያስተምሩ የነበሩ ናቸውና የርሳቸው የቡዳ ፖለቲካ ሰለባ መሆን ነቀፋና ትችቱ፣ ውንጀላና ተጠያቂነቱ እንዲከብድብቸው ያደርገዋል፡፡
ዶ/ር መረራ ወደ መገናኛ ብዙኃን ብቅ ባሉ ቁጥር የኢትዮጵያ ተቀዋሚዎች ተባብረን መታገል እስካልቻልን ድረስ ለውጥ ማምጣት አንችልም ይላሉ፡፡አባባሉ መልካም ነው ጥያቄው ተግባሩስ የሚለው ነው፡፡ ርሳቸውና ዶ/ር በየነ በየተራ እየተፈራረቁ የመሩዋቸው ህብረቶች ለውጤት አልበቁም፡፡አባል ያልሆኑትን ማሰባሰብ ቀርቶ መስራቾቻቸውን ይዘው መዝለቅ አልቻሉም፡፡ዶ/ር መረራ የመተባበርን አስፈላጊነት እንደ መስበካቸውና እንደ ፓርቲ መሪነታቸው ከዚህም በላይ እንደ ፖለቲካ ሳይንቲስትነታቸው መተባበርን ከልብ የሚያምኑበት ከሆነ በመሪነት የተቀመጡበትን ህብረት ያፈረሰ ወይንም ለውጤት እንዳይበቃ ያደረገ ችግር ሌላ ህብረት ተመስርቶ ከመሪዎቹ አንዱ ሲሆኑ የደመው ችግር በኋለኛው ላይ እንዳይደገም የሚያስችል ስራ መስራት ነበረባቸው፡፡ ይህ ባለመሆኑ ግን የሚፈጠሩ ህብረቶች ሁሉ ርሳቸውንና ዶ/ር በየነን ተፈራራቂ ሊቀመንበር ከማድረግ የዘለለ ተግባር ሲያከናውኑ አይታይም፡፡ዶ/ር መረራም ለዚህ ስኬት አልባነት የድርሻ ተጠያቂነትን ሲወስዱ አልተሰምቶም፡፡ ቢያንስ ለመድረክ ተጠናክሮ አለመውጣት፡፡
በተጨማሪም ተወዶልኛል እስወድዶኛልም በሚል ይመስላል ለሁላችንም የምትሆን ኢትዮጵያ የሚሉት ከአፋቸው የማይለዩት ወርቃማ አባባል አላቸው፡፡ ነገር ግን በተግባር የሚያከናውኑት የሚሉት እውን እንዲሆን የሚያግዝ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስችል አይደለም፡፡ ለሁላችንም የምትሆን ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከአምቦ ወጣ ከኦሮሞነትም ሰፋ አድርጎ ማሰብ ማቀድና መስራት ያስፈልጋል፡፡ ርሳቸው ግን ሲጠብ ከሾኔ ሲሰፋ ከሀድያ ከማይዘሉት ዶ/ር በየነ ጋር የመሰረቱትን የፖለቲካ ጋብቻ አጥብቀው በተለያየ ግዜ የፓርቲዎች ህብረት የሚል እየመሰረቱ የፈረቃ ሊቀመንበር ከመሆን አልፈው ለሁሉም የምትሆን ኢትጵያን ለመመስረት የሚያስችል ፖለቲካ ሊሰሩ ቀርቶ ፓርቲዎችን ሊያሰባስብ የሚችል ህብረት መፍጠር ያልቻሉ ናቸው፡፡
እንደውም ዶ/ር መረራ ሀገራዊ ለሆኑ ድርጅቶች ቀና አመለካከት እንደሌላቸው በተለያየ ግዜ አሳይተዋል፡፡ ለዚህም ቅንጅት በተመሰረተ በአጭር ግዜ በመላ ኢትዮጵያ ሊባል በሚችል መልኩ ሰፊ ተቀባይነት ሲያገኝ የሰሜን ደቡብ ፖለቲካ በማለት ቅንጅትን ለማጣጣል መሞከራቸውን ማስታወስ ይበቃል፡፡ በጥቅሉ ዶ/ር መረራ ሌሎቹን ፖለቲከኞች ሲፈርጁና ሲወቅሱና ተጠያቂ ሲያደርጉ የራሳቸውን የድርሻ ተጠያቂነት እየወሰዱ ባለመሆኑ ራሳቸውም የቡዳ ፖለቲካ የሚሉት ሰለባ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡ ለማስረጃነት ይህን ጠቀስኩ እንጂ የዶ/ር መረራን የቡዳ ፖለቲካ ሰለባ መሆን ለማሳየት ከረዥሙ የፖለቲካ ህይወታቸው ብዙ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል፡፡
አቶ ግርማ ሰይፉና የቡዳ ፖለቲካ ፤
አቶ ግርማ የዶ/ር መረራን የቡዳ ፖለቲካ ሰለባነት ለማሳየት ባቀረቡት ጽሁፍ ያነሱዋቸው አንዳንድ ጉዳዮች የርሳቸውንም ሰለባነት ያረጋገጡ ናቸው፡፡ በመሆኑም ሌላ ማስረጃ መፈለግ ሳይጠይቅ ከጽሁፋቸው በመጥቀስ ብቻ የአቶ ግርማን የቡዳ ፖለቲካ ሰለባነት ላሳይ፣ ጥያቄዎችንም ላንሳ፡፡
1) እኔ በመሪነት ሁሉ የተሳተፍኩበት አንድነት ፓርቲን በአማራ ልሂቃን የሚመራ ተብሎ ተፈርጇል፡፡
በምርጫ 2002 ወቅት አቶ ግርማ አንድነት ውስጥ የነበራቸውን የኃላፊነት ቦታ ባላውቅም የምክር ቤት አባል ነበሩ፡፡ ታዲያ በዛን ወቅት መድረክ በደቡብ በእነ ዶ/ር በየነ ድርጅት፤ በኦሮምያ በዶ/ር መረራና በአቶ ቡልቻ ድርጅቶች፣ በሶማሊያም እንደዚሁ የመድረክ አባል በሆነው የሶማሌ ድርጅት (ስሙን በትክክል ባለማወቄ ነው) በትግራይ በአረና በአማራ ደግሞ በአንድነት እንደሚወከል በይፋ ይነገር ነበር፡፡ በተለይ ዶ/ር መረራ እና አቶ ቡልቻ በተደጋጋሚ ነበር የተናገሩት፡፡ከዚህ ታልፎም አንድነት በኦሮምያና በደቡብ እጩዎችን እንዳያቀርብ ተከልክሎ ውዝግብ መፈጠሩ ይታወቃል፡፡ይህን የተቃወሙ ሰዎች አንድነት አንዴትና በምን ምክንያት ነው የአማራ ተወካይ የሚባለው፤ የአንድነት አመራሮችስ በዚህ ተስማምታችኋል ወይ ወዘተ በማለት በግል ጋዜጦች የጻፉትን አንብበናል፡፡ አቶ ግርማ ያኔ ምን ብለው ነበር; ወይንስ ይህን አያውቁም ;ያን ግዜ እንዲታረም ቢደረግ ዛሬ ዶ/ር መረራ ያውም በመጽሀፍ ይጽፉት ነበር; ታዲያ አንድነት የአማራ ፓርቲ ተደርጎ በመገለጹ አቶ ግርማ ድርሻ የላቸውም ማለት ይቻላል;
2) አሁን ከመድረክ ጋር ለመስራት ሽር ጉድ የሚለው ሰማያዊ ፓርቲ መስራቾች ከአንድነት የወጡበት ምክንያቱ አንዱ የመድረክ ጉዳይ ነበር፡፡
በአቶ ግርማ የተጠቀሱት ወጣቶች በወቅቱ መርህ ይከበር ዝም እንልም በሚል ተቃውሞአቸውን በተለያየ መንገድ በጽሁፍ ያሰራጩ ስለነበር አብዛኛውን ለማየት ችያለሁ፡፡አንድነት መድረክ የገባው ታስቦበት ተመክሮና ታቅዶ ሳይሆን በሁለትና ሶስት ሰዎች ግፊት ነው፡፡ በመሆኑም አካሄዱ ለአንድነትም ለመድረክም አይበጅም የሚል ነበር፡፡አንደ አልበጀ ደግሞ በተግባር ታይቷል፡፡የአቶ ግርማም ጽሁፍ ነግሮናል፡፡ ዛሬ የአንድነት አባላት መድረክ ሲታዘል ተንጠልጥሎ የቀረ ሰለሆነ ከጫንቃችን ይውረድ ብለው ወስነዋል፡ በማለት መድረክን አሳንሰው የነገሩን ከዚህም አልፈው ከመድረክ ባንወጣ አንድነት ሳይፈርስ እንደሚቆይ እንረዳለን፡ በማለት የመድረክ ግንኙነት ለአንድነት መፍረስ አንዱ ምክንያት መሆኑን ያረዱን አቶ ግርማ ከመነሻው አንድነት መድረክ የገባበትን ሁኔታ መደገፋቸው ስህተት እንደበረ ለዚህም የተጠያቂነት ድርሻ እንዳለባቸው ሊገልጡ አልደፈሩም፡ ነገሩ የቡዳ ፖለቲካ ነውና፡፡
በአቶ ግርማ የተጠቀሱት ወጣቶች በወቅቱ መርህ ይከበር ዝም እንልም በሚል ተቃውሞአቸውን በተለያየ መንገድ በጽሁፍ ያሰራጩ ስለነበር አብዛኛውን ለማየት ችያለሁ፡፡አንድነት መድረክ የገባው ታስቦበት ተመክሮና ታቅዶ ሳይሆን በሁለትና ሶስት ሰዎች ግፊት ነው፡፡ በመሆኑም አካሄዱ ለአንድነትም ለመድረክም አይበጅም የሚል ነበር፡፡አንደ አልበጀ ደግሞ በተግባር ታይቷል፡፡የአቶ ግርማም ጽሁፍ ነግሮናል፡፡ ዛሬ የአንድነት አባላት መድረክ ሲታዘል ተንጠልጥሎ የቀረ ሰለሆነ ከጫንቃችን ይውረድ ብለው ወስነዋል፡ በማለት መድረክን አሳንሰው የነገሩን ከዚህም አልፈው ከመድረክ ባንወጣ አንድነት ሳይፈርስ እንደሚቆይ እንረዳለን፡ በማለት የመድረክ ግንኙነት ለአንድነት መፍረስ አንዱ ምክንያት መሆኑን ያረዱን አቶ ግርማ ከመነሻው አንድነት መድረክ የገባበትን ሁኔታ መደገፋቸው ስህተት እንደበረ ለዚህም የተጠያቂነት ድርሻ እንዳለባቸው ሊገልጡ አልደፈሩም፡ ነገሩ የቡዳ ፖለቲካ ነውና፡፡
3) አንድነት ከመድረክ ወጥቶም በግዛቸው ሸፈራው መሪነት ቢቀጥል መንግሰት ይህን አሳፋሪ እርምጃ አይወስድም ነበር፡፡ ምክንያቱም ባለበት የሚረግጥ ፓርቲ ማንም አይፈራውም፡፡
በአቶ ግርማ ከተገለጸው ሁሉ በእጅጉ ያስገረመኝና በዝምታ ለማለፍ ያላስቻለኝ ይህኛው ነው፡፡የአንድነትን ሊቀመንበርነት ከኢ/ር ግዛቸው ወደ ዶ/ር ነጋሶ ያስተላለፈውና አቶ ግርማንም ለም/ል ሊቀመንበርነት ያበቃው ጉባኤ ላይ ኢ/ር ግዛቸው ወኔየ ተሟጧል ሞራሌ ሞቷል ከአንግዲህ በአመራርነት አይደለም በአባልነትም አልቀጥልም ብለው ተሰናብተው ሳለ በቀጣዩ ጉባኤ ተለምነውና ደጅ ተጠንተው ለሊቀመንበርነት ተወዳደሩ፡፡ ተወዳዳሪዎቻቸውን በከፍተኛ የድምጽ ልዩነት አሸንፈው ሊቀመንበር መሆናቸውም ታወጀ፡፡ (አንዱ ተወዳዳሪ አቶ ግርማ ነበሩ፡፡) አንድነትን ባለበት እንዲያስረግጡ ነበር ተለምነው የመጡት;
ከዚህ በኋላ የመኢአድ አንድነት ውህደት ይሳካ አይሳካ ገና ሳይረጋገጥ ለውህዱ ፓርቲ ሊቀመንበርነት በኢ/ር ግዛቸውና በአቶ በላይ በፍቃዱ ደጋፊዎች መካከል ለአደባባ የበቃና ማህበራዊ ድረ-ገጾችን ያጣበበ አተካሮ ተፈጠረ፡፡ ኋላም የምርጫ ቦርድ ህገ ወጥ ተግባር ምክንያት ሆኖ ውህደቱ ሲጨናገፍ ትግሉ መልኩን ቀይሮ ኢ/.ር ግዛቸው በከፍተኛ ድምጽ ተመረጡ የተባሉበትን ግዜ ሳያጋምሱ ሥልጣን እንዲለቁ አበቃቸው፡፡ኢ/ር ግዛቸው ከሥልጣን የተሰናበቱት በዚህ መልክ መሆኑን ነበር የሰማን ያነበብነው፡፡ ኢር ግዛቸው አንድነትን ባለበት የሚያስረግጡ ከሆኑ ለምን ተለምነው ወደ ፓርቲው እንዲመጡ ተደረገ; ለምንስ ተመረጡ; በወቅቱ አቶ ግርማ ም/ል ሊቀመንበር ነበሩና ምን አደረጉ; የኢ/ር ግዛቸው ድክመት ለአቶ ግርማ የታያቸው ከተሸነፉ በኋላ ይሆን; ( የነበረውን ሁኔታ ለመግለጽ እንጂ ኢ/ር ግዛቸው ብቃት ያላቸው መሪ ነበሩ እያልኩ አይደለም)
ከዚህ በኋላ የመኢአድ አንድነት ውህደት ይሳካ አይሳካ ገና ሳይረጋገጥ ለውህዱ ፓርቲ ሊቀመንበርነት በኢ/ር ግዛቸውና በአቶ በላይ በፍቃዱ ደጋፊዎች መካከል ለአደባባ የበቃና ማህበራዊ ድረ-ገጾችን ያጣበበ አተካሮ ተፈጠረ፡፡ ኋላም የምርጫ ቦርድ ህገ ወጥ ተግባር ምክንያት ሆኖ ውህደቱ ሲጨናገፍ ትግሉ መልኩን ቀይሮ ኢ/.ር ግዛቸው በከፍተኛ ድምጽ ተመረጡ የተባሉበትን ግዜ ሳያጋምሱ ሥልጣን እንዲለቁ አበቃቸው፡፡ኢ/ር ግዛቸው ከሥልጣን የተሰናበቱት በዚህ መልክ መሆኑን ነበር የሰማን ያነበብነው፡፡ ኢር ግዛቸው አንድነትን ባለበት የሚያስረግጡ ከሆኑ ለምን ተለምነው ወደ ፓርቲው እንዲመጡ ተደረገ; ለምንስ ተመረጡ; በወቅቱ አቶ ግርማ ም/ል ሊቀመንበር ነበሩና ምን አደረጉ; የኢ/ር ግዛቸው ድክመት ለአቶ ግርማ የታያቸው ከተሸነፉ በኋላ ይሆን; ( የነበረውን ሁኔታ ለመግለጽ እንጂ ኢ/ር ግዛቸው ብቃት ያላቸው መሪ ነበሩ እያልኩ አይደለም)
4) አንድነትን ለማፍረስ የተሰለፉት ሆዳሞች ደግሞ ከሁሉም ሰፈር የተሰበሰቡ ናቸው፡፡
አቶ ግርማ አንድነት የፈረሰው ፓርቲው ውስጥ በነበሩ ሆዳሞች እንደሆነ በድፍረት ጽፋዋል፡፡ነገሩ የቡዳ ፖለቲካ ነውና የርሳቸው ድርሻ የለበትም፡፡በወቅቱ የአንድነትን ነገር በቁጭት የተከታተለ ሁሉ እንደሚያስታውሰው ምርጫ ቦርድ ከእኛ ጋር ተስማምተው ለሚሰሩ በማለት በአደባባይ ተናግሮ አንድነትን ለሌሎች ለመስጠት የበቃው እነ አቶ ግርማ በከፈቱለት በር ገብቶ ነው፡፡
የኢ/ር ግዛቸውን የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄ የተቀበለው ምክር ቤት በዚህ ሳይቆም ተጣድፎ አቶ በላይን ሊቀመንበር አደረገ፡፡ አቶ በላይም ወዲያው ካቢኔያቸውን አቋቋሙ፡፡አቶ ግርማም ምክትል ሊቀመንበር ሆኑ፡፡በአሸናፊነት ስሜት የተዋጡት የአቶ በላይ ደጋፊዎች እየተሰራ ያለው ነገር ምን ሊያስከትል ይችላል ብለው ለማገናዘብ አልቻሉም፡፡በአንጻሩ የኢ/ር ግዛቸው ደጋፊዎች፤ ሂደቱ ደንብ የጣሰ ነው በማለት ለህግ መከበር የቆሙ እንደሆነ የተናገሩ፣ እንዲሁም የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት አመች አጋጣሚ ሆኖ የታያቸው ተቃውሞአቸውን አጠናከሩ፤ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ጀመሩ፤ በኢትዮጵያ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ እስከመስጠት ደረሱ፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን አድፍጦ ሲያዳምጥና ሲመለከት የቆየው ምርጫ ቦርድ በሚፈልገው ሰአት ካርዱን መዘዘና የአቶ በላይ ምርጫ ህገ ደንብ የተከተለ አይደለም፤ ስለሆነም ሁለታችሁም በጋራ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርታችሁ ካላስወሰናችሁ አልቀበለም አለ፤በጋራ ጠቅላላ ጉባኤ መጥራቱ ደግሞ የማይቻል ሆነ፡፡ይህም ለምርጫ ቦርድ በሩን ወለል አድርጎ ከፈተለትና ከመጀመሪያው አባል እንኳን መሆን ላልነበረበት ለአቶ ትእግስቱ አዎሉ አንድነትን ለማስረከብ በቃ፡፡ አንድነት ወደ መፍረስ እየሄደ መሆኑ በግልጽ እየታየ ባለበት ግዜ እንኳን አንዱ ሌላኛውን ይወነጅል፣ይፈርጅ ነበር እንጂ እኔስ፣ እኛስ ብሎ መጠየቅና ሰከን ብሎ ግራና ቀኝ ማስተዋል አልነበረም፡፡ ፓርቲው ከፈረስም በኋላ አንደኛው ሌላኛውን ወገን ተጠያቂ ያደርጋል፣ ይወነጅላል ይፈርጃል እንጂ የራሱን ድርሻ ለመውሰድ የሚደፍር አልታየም፡፡ ምክንያቱም ፖለቲካው የቡዳ ፖለቲካ ነዋ!
አቶ ግርማ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩበት አንድነት የፈረሰው በዚህ መልኩ ሆኖ ሳለ በሁሉም ሰፈር የተሰባሰቡ ሆዳሞች ያሉዋቸውን ተጠያቂ ሲያደርጉ የርሳቸውን ቦታና ድርሻ ግን ለመናገር አልደፈሩም፤ወይንም ከደሙ ንጹህ ነኝ የሚሉ ይመስላል፡፡አዬ የቡዳ ፖለቲካ!
የቡዳ ፖለቲካ የዶ/ር መረራና የአቶ ግርማ ወይንም የፖለቲከኞች ብቻ ችግር አይደለም፤ አብዛኛዎቻችን (ሁሉም ለማለት ይቻላል) ጣታችንን ወደ ሌላ መቀሰር እንጂ መስተዋቱን ወደ ራሳችን ለማዞር ድፍረቱ የለንምና የቡዳ ፖለቲካ የሚል ስያሜ የተሰጠው አስተሳሰብ ሰለባዎች ነን፡፡ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ደግሞ ከዚህ መላቀቅ ወሳኝ ነው፤ ግን እንዴት ሆኖ?
No comments:
Post a Comment